BM Engineering Academy
16/01/2023
የሚሸጥ አስፓልት ሬንጅ አለን 80/100 ፣ጠቅላላ 200 በርሜል
ዋጋ 15500 ብር በበርሜል።
16/03/2022
👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር??...
* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques
A) ሜካኒካል ውስጥ :-
1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::
2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን
3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር
coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት
ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር
ፀባይ ማግኘት እንችላለን
B) ኬሚካል :-
1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው
ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ
plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው
በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡
2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete
pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል
ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡
3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive
አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ
B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡
C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-
1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም
ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው
2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው
3. Dynamic Stabilization
ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::
ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት
አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡
4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም
በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground
water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡
የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
👉For More Updated Con information
https://t.me/addisengineers
07/03/2022
"
🏗አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው። በመሆኑም ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ፦
🏗The reasons a building collapses can be due to
🔸poor structural design,
🔸poor compliance with specifications
🔸poor quality control
🔸Faulty construction methodology foundation failure
🔸Extraordinary loads and corruption. A natural disaster is also identified as a cause of building collapse.
🏗በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል
👉poor structural design
👉faulty construction
👉poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።
🏗አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??
ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1, በ Fatigue ና
2, በ Creep ነው
1,Fatigue
👉ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡
2,Creep
👉አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡
25/02/2022
🏗አራት መአዘን ቅርፅ ያለው ለአነስተኛ ቤተሰብ የሚውል የውሃ ታንከር እንዴት ዲዛይን እናደርጋለን❓
እንደ አለማቀፋዊው የIS ኮድ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ለተለያየ አገልግሎቶች የሚጠቀመው የውሃ መጠን 135 liter ነው።
ይህ ኮድ
*ለመጠጥ - 5 ሊትር
*ለማብሰል- 5 ሊትር
*ለመታጠብ እና ፍሳሽ ለማስወገድ - 85 ሊትረ
*ልብስ እና እቃዎችን ለማጠብ - 30 ሊትር
*ቤት ለማፅዳት - 30 ሊትር ውሃ መጠቀም እንዳለብን ይጠቁማል።
▶ይህን የIS ኮድ ይዘን 4 አባላት ላሉት አንድ ቤተሰብ እንደ Hydraulic ኢንጂንየርነታችን አራት መአዘን ቅርፅ ያለው የውሃ ታንከር ዲዛይን እናርግ።
4 አባላት (ሰዎች) ላሉት የቤተሰብ አባል ተፈላጊ የውሃ መጠን በliter
135×4 = 650 liter (ለአንድ ሰው በቀን 135 liter )
የውሃ ታንከሩን መጠን ለማወቅ ከርዝመቱ (length ) ከየጎን ስፋት (width ) እና ከቁመቱ/ጥልቀቱ( depth) አንዱን ማወቅ አለብን ።
▶ከ Volume ቀመር እንደምንረዳው
1cu.m = 1000liters
1liter = 0.001 cu.m ነው ስለዚህ
650liter = 0.65 cu.m
የታንከራችንን ቁመት 0.6m ብናደርገው የታንከራችን ስፋት (area ) እንዲ ማግኘት እንችላለን
Area= 0.65÷0.6 = 1.083 sq.m ስፋት (area) ማለት ርዝመት (length) ሲባዛ የጎን ስፋት (width) ይሆናል ። ይህም
A=L×W= 1.083 sq.m
በ IS ተጠቃሽ (recommended) የርዝመት መጠን ከሁለት እጥፍ የጎን ርዝመት መጠን ጋር እኩል ነው ።
ይህም L= 2W
L×W=1.083 sq.m
2W×W = 1.083 sq.m
B^2 = 0.054 sq.m
B= 0.74
L= 2×0.74 = 1.48 m
▶ስለዚህ 650 liter የሚይዝ ታንከር ፦
ርዝመት (L) =1.48m
የጎን ርዝመት (W) = 0.74m
ቁመት/ጥልቀት= 0.6 m ይሆናል ማለት ነው ። ልንረሳው ማይገባ ነገር ለታንከሩ free flow provide ማረግ አለብን [125mm free flow ]
04/12/2021
🏷የ Foundation (መሠረት) አይነቶች
🚧1)Shallow Foundation
➡️እነዚህን ፋውንዴሽኖች የምንጠቀመው አፈሩ ብዙም ሳይቆፈር በቅርብ ጥልቀት ጠንካራ የአፈር ሁኔታ ካለ ነው፡፡
➡️ለመገንባት ትልልቅ ማሺኖች አያስፈልጉም ብዙ ችሎታም አይጠይቁም::
▶️1.1) Spread/ Pad/Isolated Footing
➡️አንድ ኮለን ብቻ ነው support የሚያደርጉትእንዲሁም የሚመጣውን ፎርስ eccentricity መሰረት በማድረግ circular/ rectangular or square የሆነ ቅርፅ ሊኖራቸው ይችላል፡፡
▶️1.2)Combined Footing
➡️ሁለትና ከዛ በላይ ኮለኖችን በአንድ ፓድ support ለማድረግ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡
➡️እነዚህን የምንጠቀመው ሁለት ተቀራራቢ Isolated Footing ካሉ ሁለቱን አንድ ላይ combine በማድረግ ኮንክሪትም ፌሮም ሴቭ ማድረግ እንችላለን፡፡
➡️በተጨማሪም isolated ለመጠቀም property limit ካለ እነዚህን መጠቀም እንችላለን::
➡️2 አይነት Combined Footing አሉፐእነርሱም
▶️1.2.1) Rectangular Combined Footing
➡️ይህንን የምንጠቀመው ሁለቱም ኮለኖች የሚሸከሙት ሎድ ተቀራራቢ ወይም እኩል ከሆከሆነይም ትራፖዞይዳል ለመጠቀም የስፋት ገደብ ካለ ነው።
▶️1.2.2. Trapezoidal Combined Footing
➡️ሁለቱ ኮለኖች የሚሸከሙት ሎድ ልዩነት የተጋነነ ከሆነ ነው።
▶️1.3) Strap/ Cantilever Footing
➡️ሁለት ፓዶችን በቢም በማያያዝ ሎድ ከአንዱ ፓድ ወደሌላው እንዲተላለፍ ማድረግ እንችላለን፡፡
➡️ቢሙ በራሱ ሎድ አይሸከምም ሎድ ያስተላልፋል እንጂ እነዚህን የምንጠቀመው ኮለኖቹ ከ7 ሜትር በላይ ከተራራቁ combined footing ብንጠቀም ኢኮኖሚካል ስለማንሆን ፓዶቹን በቢም በማያያዝ እንደ combined footing ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡
▶️1.4) Mat/ Raft foundation
➡️እነዚህን የምንጠቀመው መሬቱ የመሸከም አቅሙ ትንሽ ከሆነና spread footing ስንጠቀም የህንጸውን ስፋት ከ50 ፐርሰንት በላይ ከሸፈኑት ነው።
➡️አንዳንዴ ግን spread footing ከ 50 ፐርሰንት በላይ ቢሸፍኑትም ለ spread footing negative reinforcement ስለማንጠቀም ከ Mat ይልቅ ኢኮኖሚካል ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም Mat negative & positive reinforcement ይጠቀማሉ፡፡
➡️ማን ኢኮኖሚካል እንደሆነ ቼክ ማድረግ የኢንጅነሩ ድርሻ ነው፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Address
Cherchil
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:00 |
| Tuesday | 08:30 - 17:00 |
| Wednesday | 08:30 - 17:00 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:00 |
| Saturday | 08:30 - 17:00 |