IT-EL 46
Senbet Media ፔጃችንን like በማድረግ ሁለገብ የኦርቶዶክስን ተዋህዶን አስተምህሮ ያገኛሉ
11/06/2021
ዘፈን ኃጥያት ነው?
' #ዘፈን' ኃጥያት ስለሆነ ነው ቤተክርስቲያን ዘፈንን አጥብቃ የምታወግዘው::" ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።"(የያዕቆብ መልእክት 1:15)
ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ለምን ዘፈንን አወገዘች???
1. ዘፈን የአጋንንት ሥራ ነው:: አጋንንት ይዘፍናሉና:: ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም:: መጽሐፍ ቅዱስ "በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ" በማለት ስለ አጋንንት
ዘፋኝነት ይናገራል::(ኢሳ.13:21) አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን እንረዳ:: ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል:-
"....እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር::
አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር::" (1ኛ.መቃ.36፥27-28)
በዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለው አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጐራ መሰለፋቸው ነው::ስለዚህ ከዘፋኞች ጎን በመሆን የሚያግዟቸውና የሚደሰተው አጋነንት እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፡፡
2. ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል:- "ስለ ተግባረ ዕድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ሕግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሠሩ ይገባል:: ... እንደ ዘፋኝነት፥ እንደ መጥፎ ጫወታ፥
በእግር እንደ ማሸብሸብ(ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር ነው::" (ፍት.ነገ.መን.አን. 23:820) መንፈሳዊን የሚቃወምን ምንም ነገር መሥራት እንሌለብን እየነገረን፡፡
ይህ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደ ሥራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል::ምክንያቱም አንድ አንድ ሰዎች ስራዬ ነው ካልሰራው አልበላም ስለዚህ መዝፈኔ እንደ ኃጥያት አይቆጠርብኝም የሚሉ አሉና ዘፈንን መዝፈን እንደ ስራ አይቆጠርም፡፡ ይህም ስራ ነው ከተባለ ጠንቋዩም ጥንቁልናውን ስራዬ ነው ማለት ይችላል ማለት ነው::.::
ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡
በዘመናችን የሐጢያት ተግባራ ሁሉ ገቢ ማስገኛ እየሆኑ ነው፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡
3. ዘፋኝነት "የሥጋ ሥራ" በመሆኑ ኃጢአት ነው::
(ገላ.5:21):: "በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፤" ተብሏልና:: (ገላ.5:16)::
ዝማሬ ሰማያዊ፡ዘላለማዊ የሆነውን እግዚአብሔርን ማመስገን ነውና አሱን መምረጥ ይኖርብናል፡፡
ቅዱሳንን ስናመሰግን በቅዱሳን የከበረውን እግዚአብሔርን ማመስገን ነው እንጂ ሠውን እያመሰገንን አይደለም፡፡
4. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል:: ሐዋርያት በዲድስቅልያ "ኢትኩኑ ዘፈንያነ" ፥ "ዘፋኞች አትሁኑ" ብለዋል:: (ዲድስቅልያ፤ አንቀጽ 7) ቅዱስ ጳውሎስ "በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ:: በዘፈንና በስካር አይሁን" ብሏል:: (ሮሜ.13፥13) ቅዱስ ጴጥሮስ
ደግሞ "በስካርና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል::" ይለናል:: (1ኛ.ጴጥ.4:3)::በማለት በዘፈን ያረከስናትን ሕይወታችንን እንድንተው ይመክረናልና ልንተው ያስፈልጋል፡፡
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ "ከሰይጣን የተገኘ ነውና
ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል::" ይለናል::
ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቂ አይንሽ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለሽ መርምሪ፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛውም እንደሆነ ማስተዋል ሞክሪ፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተሽ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለሽ፡፡
ባለውቃቤዎችስ ሲደነፉ ተመልክተሽ አታውቅምን? የባለ ውቃቤዎች ድንፋታ ደግሞ ቁርጥ እዋኽ፣ እዋኽ እየተባለ የሚዘፈነውን ባህላዊ ዘፈን ይመስላል፡፡ ፍከራው ቀረርቶውና በየብሄረሰብ የምትመለከትመለከቺው ዘፈንና ጭፈራ ብትመረምሪ ከዚህ የቀረበ መመሳሰል አናጣበትም፡፡ ቅዱስ ሐዊ እንደተናገረው ‹‹ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ›› ነውና፡፡
(መጽ.ሐዊ አን. 50):: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ "ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችሗለሁ፤" በማለት ይማጸናል:: (ተግ.ዘዮሐ.አፈ.28) ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ጸንተው የሚኖሩ
ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን:: (መጽ.ሐዊ.አን. 12)
ከመጨረሴ በፊት አንድ ታሪክ ልንገርሽ ከእለታት በአንድ ቀን አንድ ጎልማሳ ልጅ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀርቦ እንዲህ በማለት ጠቃቸው፡፡"አባ በተክሊል እንዳላገባ ስጋዊ ድንግልና የለኝምና በዓለማዊ ዘፈን ባገባስ?" ሲላቸው ቅዱስ ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፡፡"ልጄ በዘፈን ሰይጣንን ከምትጠራ በዝማሬ መላዕክትን ጥራ" ብለው መለሱለት፡፡ ስለዚህ በዘፈን ሰይጣንን አንጂ ፈጣሪን የሚባርኩንን እንደማንጠራ ግልፅ ባለ አንደበቱ አስተምሮናል::አሁን የኢትዮጵያን ዘፋኞችና ተወዛዋዦች ስልጣኔ እየመሠላቸው ራቁታቸውን ካልሆኑ በስተቀር መቀረፅ አይፈልጉም፡፡በዕውነት ልቦና ይስጣቸው፡፡ይህ አሁን በየቻናሉ የምንመለከተው ለመንፈሳዊና ለአይን ትውልድን የሚያበላሹ ናቸውና ለአይናችንም ጭምር ልንጠነቀቅ ያስልጋል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |