PHARMAhelp

PHARMAhelp

Share

we give pharma info for everyone and also add some important tips about health and life

03/10/2022

✍️ #ማዳበር #የሚገባዎት #ጠቃሚ #ልምዶች #ምንድናቸው?

🔹 በቀን ውስጥ የጸሎት ሰአት ይኑሮት

🔹 ሰዎችን ማክበር

🔹 ሁልጊዜ በሰአት መገኘት

🔹 ማንበብን ማዘውተር

🔹 ፍልጎትን በግልጽ መናገር

🔹 እውነትን መናገር

🔹 የግል ንጽህናን መጠበቅ

🔹 ታታሪ ሰራተኛ መሆን

🔹 ከሚያገኙት በላይ አለማጥፋት

🔹 ተስፋ አለመቁረጥ

🔹 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት

✍ 9102 ok አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።

👇👇👇

👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-

👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/

👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102 OK

09/07/2022

✍️ የሩዝ ውሃ ለማራኪ የፊት ገፅታና ለፀጉር እድገት

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🔹 የሩዝ ውሃ የፀጉር ድርቀትን በማስወግድ የተሻለ ልስላሴ እንዲኖረው እና መተጣጠፍ እንዲችል ያደርጋል። የሩዝ ውሃ ለፀጉራችን እና ቆዳችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይታወቃል። በተጨማሪም የተጎዳ ፀጉር እንዲያገግም ከመርዳት ባለፈ ፀጉራችን የተሻለ ገፅታን እንዲላበስ፣ የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖረንም ያግዛል ነው የተባለው።

🔹 ከፀጉር በተመሳሳይ የቆዳ ልስላሴንም የሚያጎናፅፍ ሲሆን በቆዳ ላይ የሚደርስን የማቃጠል አደጋ ለማቀዝቀዝ እና ለማከም፣ በፀሃይ የሚደርስን የማቃጠል ስሜትንም ለማጥፋት ይጠቅማል። በመሆኑም በሩዝ ውሃ ፀጉርን መታጠብ የተለያየ የጤና ጠቀሜታዎችን ያስገኝልናል።

🔹 የሩዝ ውሃ በውስጡ በርካታ አንቲኦክሲዳንትስ፣ ማዕድኖች፣ ቫይታሚን ቢ፣ ኢ ከመያዙም በላይ “ፒተራ” የተሰኘውንና የሞቱ ሴሎች እንደገና እንዲያድጉ የሚያደርገውን ንጥረ ነገር በመያዙ ከእርጅና ጋር የሚያያዙ ምልክቶች እና ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው።

👉 አጠቃቀም
የሚያስፈልጉ ነገሮች፦

🔹 ግማሽ ኩባያ የሩዝ (ነጭ፣ ቡኒ ወይም ሌላ አይነት ሩዝ ሊሆን ይችላል)
🔹 2(ሁለት) ኩባያ ውሃ

👉👉 አዘገጃጀት፦

🔹 አላስፈላጊ ነገሮች ከሩዙ ላይ ለማስወገድ በመጀመሪያ ሩዙን በደንብ ይጠቡት፣
🔹 ከዚያም ሩዙን በጎድጓዳ ሳህን በማድረግ ሩዙ ሙሉ በሙሉ በውሃ እስኪሸፈን ውሃ ይጨምሩበት፣
🔹 ሩዙ ከውሃው ጋር እንዲብላላ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ይተውት/
🔹 ውሃው በደንብ እስኪደፈርስ ድረስ ቀስ እያሉ ውሃውን ከሩዙ ጋር ያቀላቅሉት (ይህም በሩዙ ውስጥ ያሉ በርካታ ማዕድናት እና ቫይታሚኖች በውሃው ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል)
🔹 ከዚያም ውሃውን በሌላ ንፁህ ሳህን በመገልበጥ ለመጠቀም ዝግጁ ማድረግ ይችላሉ

👉 ማስታወሻ

🔹 ይህን ውሃ ቢፈልጉ ለፊትዎ አልያም ለፀጉርዎ መጠቀም ይችላሉ
🔹 በውሃው ፊትዎን ወይም ፀጉርዎን በማሸት ከተጠቀሙ ከአንድ ወይም ሁለት ሰዓት በኋላ ይለቃለቁት

👉👉 ስለዉበትዎ መጠበቂያ ምክር ሲያሻዎ ወደ 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa