Global Addis Media
Global Addis - ግሎባል አዲስ
16/02/2026
ከአሥራ ሦስት ዓመታት በፊት በአውስትራሊያ የጫካ ውስጥ የሩጫ ውድድር ላይ ሳታስበው የደረሰው አስፈሪ የሰደድ እሳት የቆንጆዋን ሞዴልና ስፖርተኛ የቱርያ ፒትን ሕይወት ለዘላለም ቀየረው...
በወቅቱ የሰውነቷ 65% በእሳት ተቃጥሎ ከ200 በላይቀዶ ጥገናዎችን ለማድረግና ለዓመታት የሚዘልቅ ስቃይን ለመጋፈጥ ተገዳ ነበር...
ፍቅረኛዋ ሚካኤል ሆስኪን በወቅቱ የፖሊስ መኮንን የነበረ ቢሆንም ቱርያ አደጋ ሲደርስባት ጥሏት ከመሄድ ይልቅ ሥራውን ትቶ ሙሉ ጊዜውን እሷን ለመንከባከብ መረጠ። ቱርያ በራሷ ላይ ተስፋ በቆረጠችበትና ራሷን ማየት በጠላችበት ጊዜ ሚካኤል ውበት ከቆዳ በላይ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ መስታወት ሆናት።
ከዓመታት በኋላም በማልዲቭስ የባህር ዳርቻ ላይ በታላቅ የፍቅር ስሜት የትዳር ጥያቄ አቀረበላት። ሚካኤል ትተሃት የመሄድ ሃሳብ መጥቶብህ አያውቅም? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ዛሬም ድረስ የብዙዎችን ልብ ይነካል፦
"እኔ ያገባሁት ነፍሷንና ማንነቷን እንጂ አካሏን አይደለም'' ነበር ያለው፡፡
ይህ ታሪክ እውነተኛ ፍቅር በአይን የሚታይ ሳይሆን በልብ የሚሰማ ማዕበልን ተቋቁሞ የሚጸና እና ሁሉም ነገር በጠፋበት ጊዜም አብሮ የሚቆይ መሆኑን ለዓለም ያስመሰከረ ድንቅ አጋጣሚ ነው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ የተለየ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ጠ/ም ጆርጂያ ሚሎኒ ❤️🙏
16/02/2026
"እደመስሳችኋለሁ፣ አጠፋችኋላሁ የሚል መንግስት ነው ያለን" ሲሉ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡
ህወሀት የተመሰረተበትን 51ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በዋሽንግተን ዲሲ ትላንት በተከናወነ ስነስርአት ላይ ዶክተር ደብረፅዮን በቪዲዮ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ንግግራቸውን ‹‹ህወሀት በህይወት አለ›› በማለት የጀመሩት ደብረፅዮን ሲቀጥሉም ‹‹ይህ በአል ብዙ የተከፈለበት የህዝብ ታሪክ ነው፡፡ እናም ጥንካሬዎቻችንንና ድክመቶቻችንን ከታሪክ መማር አለብን›› ብለዋል፡፡
ፓርቲው ከዚህ ቀደም የማይታለፉ የሚመስሉ ፈተናዎችን በፅናትና በአንድነት ማለፉን ጠቅሰውም ብዙ እንቅፋቶችን በውጭ አገር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ጠንክረው መታገላቸውን አውስተዋል፡፡
ዲያስፖራ የትግራይ ተወላጆች በትጥቅ ትግል ወቅትም ሆነ ባለፈው ጦርነት ወቅት ትልቅ ሚና ማድረጋቸውን ያስታወቁት ዶክተር ደብረፅዮን የትግራይ ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ ማድረጋቸው ለዚህ ምስክር መሆኑም ገልፀዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹አሁን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተጥሷል፡፡ ህዝባችንም ተበታትኗል፡፡እደመስሳችኋለሁና አጠፋችኋለሁ የሚል መንግስት አሁንም አለን፡፡ ይህ ደግሞ ወደሌላ ጦርነትና ጥፋት እያመራን ነው›› ብለዋል፡፡
የትግራይ ተወላጆች በአንድነት መቆም እንዳለባቸው የጠቀሱት ደብረፅዮን ጨምረውም ‹‹አሁን ከውጭ ጠላቶች በተጨማሪ ከሀዲዎችም የትግራይን አንድነት ለማፍረስና ለመበታተን እየሰሩ ነው፡፡›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa