Addis Home Care
Professional Home-based Health Care provider in Addis Abebe Ethiopia.
16/03/2022
➕➕ የተረሳ እንክብል ➕➕
🖲የሚዋጥ የወሊድ መቆጣጠሪያ ለምትወስዱ ሰዎች በመሀል መውሰድ ብትረሱ እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያው አይነት ተጨማሪ ጥንቃቄ ያስፈልጋችሁዋል
🖲ባለ 1 ሆርሞን ወይም ለምታጠባ እናት የሚሆነውን እንክብል የምትጠቀሙ ከሆነ፣ አወሳሰድ ላይ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
🖲በተመሳሳይ ሰአት ካልተወሰደ ማለትም፣ ከሚወሰድበት ሰአት ለ3 ሰአት እንኳን ከተዛነፈ እርግዝና የመፈጠር እድል ይኖራል
🖲በዚህን ግዜ፣ መዳኒቱን መውሰድ ሳታቋርጡ ለ 2 ተከታታይ ቀናት ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ ወይም ተጨማሪ የእርግዝና መከላከያ፣ እንደ ኮንዶም እና ፖስት ፒል መጠቀም አለባችሁ።
🖲ባለ ሁለት ሆርሞን መከላከያ የሚወሰድ ከሆነ ደሞ፣ አንድ ቀን ብቻ ሳትወስዱ ከረሳችሁ በማግስቱ ሁለት እንክብል ወስዶ የተቀረውን መቀጠል።
👉አብዛኛውን ግዜ ተጨማሪ መከላከያ መውሰድ አያስፈልግም
👉ነገርግን የተዘለለው እንክብል የወር አበባ መቶ ከሄደ የመጀመሪያው ሳምንት አካባቢ ከሆነ ፣ በግንኙነት ግዜ ተጨማሪ መከላከያ ፣ ኮንዶም ወይም ፖስት ፒል መጠቀም ያስፈልጋል።
🖲ሁለት ቀን እና ከዛ በላይ ከረሳችሁ ደሞ፣ የረሳችሁትን እንክብል ትተውት እና ካስታወሳችሁበት ቀን ጀምሮ በቀን በቀን እየወሰዳችሁ። ለሚቀጥሉት 7 ቀናት ከግንኙነት መቆጠብ። ካልተቻለ ደሞ በግንኙነት ግዜ ተጨማሪ መከላከያ ያስፈልጋል።
ዶ/ር ሰይፈ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
0001