KASu//TV
No one do anything
11/04/2023
ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews
በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተውን የሰደድ እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገለፀ
| ከባለፈው መጋቢት 29 ቀን ጀምሮ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተውን የሰደድ እሳት እስካሁን መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል።
በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሰደድ እሳት መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከ ቀኑ 9 ሰዓት ባልታወቀ ምክንያት መነሳቱ ተጠቁሟል።
የፓርኩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዛናው ከፍያለው እንደተናገሩት÷ እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢው ማህበረሰብ ቢሞክርም መቆጣጠር አለመቻሉንና ከ600 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እሳቱን ለማጥፋት መግባታቸውን ጠቁመዋል።
የቦታ አቀማመጡ ገደላማ መሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር ፈተና ሆኖብናል ያሉት ሃላፊው÷ እሳቱ ግጭ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በኩል እንደተነሳ አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ማለትም እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2015 ድረስ እሳቱ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በዚህም በፓርኩ የተነሳውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
10/04/2023
📍Ensaro amhara region Ethiopia 🇪🇹
Ethiopia Land of Origins Travel to Ethiopia Visit Amhara RISE UP Hiking
10/04/2023
ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የሚከተሉትን ጥሪዎች በድጋሜ አስተላልፏል!
1. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን በይፋ እንዲሰርዙ ፣ ውሳኔው ስለመሰረዙ በአደባባይ እንዲገልጹ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ካምፓቻቸው እና ወደ ግዳጅ ቦታቸው እንዲመለሱ በይፋ ጥሪ እንዲያደርጉ፤
2. በፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ እና ትዕዛዝ ከስራ ውጭ የሆኑት የአማራ ልዩ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብርጌድ እና የክፍለ ጦር አዛዦች ወደ ኃላፊነታቸው እና ምድብ ቦታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ፤
3. የክልሉ መንግስት ለልዩ ኃይሉ አስፈላጊ የሆኑ የስንቅ እና ሎጂስቲክ እንዲያቀርብ እና ደሞዝ እንዲከፍል፤
4. በካምፕ እና በግዳጅ ቦታችሁ ላይ የምትገኙ ውድ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ሠራዊቱ እንዲበተን የሚደረጉ ጥረቶችን እና የፕሮፖጋንዳ ጥቃቶችን በመቋቋም በተለመደው ሥነ-ምግባር ፣ ዲስፕሊን እና ጨዋነት የሠራዊቱን የእዝ ሰንሰለት አክብራችሁ እና ጠብቃችሁ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤
5. ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች በሙሉ በግፍ እየተጠቃ ካለው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ እና ለግጭት ከሚጋብዙ ማናቸውም ሁኔታዎች እንድትቆጠቡ፤
6. የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞን እና የወረዳ አመራሮች በሙሉ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከልዩ ኃይል ፖሊስ ሰራዊት እና ከሕዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤
7. የአማራ ሕዝብ በየአካባቢው ላሉት የልዩ ኃይል አባላት አስፈላጊውን ስንቅ እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ድርጅታችን አብን ጥሪውን አቅርቧል።
አብን መላው የአማራ ሕዝብ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከሀገር ወዳዱ የአማራ ልዩ ኃይል ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000