Anole Press
24/07/2025
Abel Mulugeta የሚባለውን ዘፋኝ ከዚህ ቀደም የወደድኸው/ያደመጥኸው የፖለቲካ አመለካከቱ ካንተ ጋር የሚመሳሰል ስለነበር ነው እንዴ ?!
ከዚህ ሰው ጋር የሚያገናኝህ እኮ ሙዚቃ ነው ...ከተመቸህ ትሰማዋለህ ካልተመቸህ ታልፈዋለህ ...That's it .
ልክ እንዳንተ እሱም የፖለቲካ አመለካከት አለው ። ልክ እንዳንተ እሱም የሚያምንበት አስተሳሰብ አለው ። አንተም ያሻህን ማመን መብትህ ነው እሱም መብቱ ነው ። ያንተም የእርሱም መከበር አለበት ።
እንደ ፋብሪካ እቃ ካልተመሳሰልን ጠላቴ ነው ካልኸኝ original ደደብ እንደሆንህ ላስታውስህ እወዳለሁ
ሰልጥን እንጂ ...ከእኔ የፖለቲካ አመለካከት ጋር ካልተመሳሰለ ሰርቶ አይብላ ማለት ድንቁርና ነው ።
29/01/2025
የብርሀን አእማድ- ፒራንዴሎ /ተፈሪ መኮንን/
መጭው ጊዜ ብሩህ ነው።
ባለቅኔው ‹‹ሀገር ወዳድ ይባላል›› ያለው አዋሽ አሁንም መፍሰሱን ቀጥሏል። ‹‹ሀገሬን›› ማለት የጀመረውና የሱዳን እና የሲና በረሃ ሰልችቶት በኢትዮጵያ ምድር ከደጋው ጎጆ የቀለሰው አባይም በሰነፍ ልጀቹ እየተበሳጨ ቆይቶ፤ ሀገሩን ለማገልገል ደፋ ቀና ማለት ይዟል። ዓመለ ሸጋው ጊቤ... አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት እየቆጠረ፤ 'ለወገን አለኝታ ነኝ' እያለ ነው። ዋቢ ሸበሌ የሶማሌን ምድር በስስት ሲቃኝ ይታየኛል። ገናሌ መስኖ ገብቷል። ብላቴ አትክልት ያለማል። ደዴሳ እና ሙገር በበጋ ጎርፍ አስቸግረዋል። ሰላም የራቀው ተከዜ ግን ኃይል ማመንጨቱን አቋርጦ ይጎርፋል።
ወጣቱ መሪ በጎርፉ ተቸግሯል።
አንበጣ፣ ድርቅ፣ ኮሮና፣ ግሽበት፣ ጦርነት ህልሙን ሊነጥቁት ታግለውታል። በሰላም ጉዳይ ህሊናው በእጅጉ ተነዋውጧል። እንደ ንጉሥ ክርዮን ያለ ፈተና ገጥሞት፤ መከራው ሲጠናበት፤ ‹‹በአትዮጵያ አንድነት ከመጣችሁብኝ፤ አንገቴ ይቆረጣል እንጂ አይደረገም። ብዕር የጨበጠ እጃችን ክላሽ ማንሳት አይገደውም። ይህ የኖርንበት እና በብዙ የምናውቀው አካሄድ ነው›› እያለ ይብከነከናል- ይብሰከሰካል።
እንደ ባራክ ኦባማ፤ ‹‹የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ብሆንም፤ ከአሸባሪዎች ጋር አልሞዳሞድም›› ማለት ቢጀምርም፤ ደጋግሞ ወንድሞቹን ይማጻናል፤ ይለምናል። ጉዞው የግሪክ ትራጀዲ ቅርጽ ይዞ፤ የክርዮንን ፈተና ተጋፍጧል።
ልዕልት አንቲገን የቤተሰብ ፍቅር ተምሳሌ ተደርጋ የምትቀርብ ወጣት ልጃገረድ ናት። ስለ አባቷ ስለ ንጉሥ ኤዲፐስ መከራን ተቀብላለች። የመከራው ተካፋይ ሆና፤ ኦዲፐስ ዓይኑ ጠፍቶ እውር በሆነ ጊዜ መንገድ መሪው ሆናለች። አሁን ደግሞ በወንድሟ በፖሊነስ ተቸግራለች።
ፖሊነስ ህግ ጥሶ፣ የሞት ፍርድ ተፈረዶበት ተሰቅሏል። በቴብዝ ልማድ በሞት ፍርድ የተቀጣ ሰው እንዳይቀበር ህግ ይከለክላል። እርሷ ግን ስለ ወንድሟ ፍቅር ይህን ሕግ ጥሳ በድብቅ ለመቅበር ወሰነች። ከክርዮን ሰማ። 'ተይ' አላት። 'እምቢ' አለች።
ክርዮን፣ ልጁ አንቲገንን በጣም እንደሚወዳት ያውቃል። ግን አንቲገን ህግን ከጣሰች፤ ክርዮን እያለቀሰም ቢሆን ይቀጣታል። በዚህ እርምጃው ከልጁ ይቀያየማል። ስለዚህ ተጨንቋል። ‹‹ንጉሥ እንደ ፈቃዱ የሚያድር ከመሰለሽ ተሳስተሻል አንቲገን›› እያለ ይለምናታል። ‹‹ንጉሥነት ሥራዬ ነው›› ይላታል። ንጉሥ ህግ የማስከበር ግዴታ ያለበት አሽከር እንደሆነ ለማስረዳት ይጣጣራል።
አንቲገን ግን ‹‹ታሳዝነኛለህ ክርዮን …… እኔ ግን የልቤን የምሞላ ንግስት ነኝ!›› እያለች፤ ህግ ተላልፋ ወንድሟን ለመቀበር መወሰኗን ትናገራለች። በለበጣ መንፈስ፤ ‹‹ታሳዝነኛለህ ክርዮን …›› ያለችውን ይዞ፤ ‹‹ታዲያ ምነው ካዘንሽልኝ፤ ህይወትሽን ልስጥሽ ስልሽ እሺ ብትይኝ? መስኮቴ ስር ተጋድሞ የሚበሰብሰው የወንድምሽ እሬሳ ለቴብዝ ሰላም በቂ መስዋዕት አይደለም? አንቲገን፤ ልጄ ያፈቅርሻል …ደምሽን ከመስዋዕቱ እንድቀላቅለው አታድርጊኝ! የፈሰሰው ደም ይበቃናል። እኔም የሚበቃኝን ዕዳ ከፍያለሁ።"
አንቲገን ሸብረክ አትልም። ‹‹አይምሰልህ! … አሜን አልክ! ንጉስ ሆንክ! እናም ዕድሜ ልክህን መስዋዕትህን ስታቀርብ፣ ዕዳህን ስትገፈግፍ ትኖራለህ። አያበቃም!›› እያለች በእምቢታዋ ጸናች። ክርዮን በጣም አዝኖና ተቆጥቶ፤
‹‹… እንዴት አትረጂኝም አንቲገን። ይኸው እኔ ልረዳሽ እጥር የለም?! ሀገሪቱ በሁከት ተንጣ የሚደርስላት ባጣች በዚያ ሰዓት፤ የህዝቧን አደራ' እሺ ' ብሎ የሚቀበል አንድ ሰው የግድ ያስፈልግ ነበር። አንድ የሆነ ሰው ይህን ሸክም "አሜን" ብሎ ተቀብሎ፤ ሁከት በሚንጣት መርከብ ፊት ቆሞ፤ ሊመራት ግድ ነበር!
‹‹መርከቧ ከሥሯ ሺህ ቦታ ተሸንቁራ፤ ከወለል እስከ ሠገነት በወንጀል …በድህነትና በድንቁርና ታፍና ነው ያገኘኋት! መዘውሯ ከነፋሱ ጋር ይዋልላል። … ሠራተኞቿ ሊያቀኗት አልፈለጉም። … ይልቅ እንደ ጠላት ጓዳ ይመዘብሯት ነበር… መኮንኖቿ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ማምለጫ ጀልባ ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ፤ ሰዎቿንና ሀብቷን ይዛ ለመስጠም ስታጣጥር ነበር ያገኘኋት! እናም ይህ ሰዓት በ‹እሺ› እና ‹እምቢ› ምንነት የቃላት ጨዋታ ለመጫወት የሚቻልበት ሰዓት ነው?! 'ንጉስ መሆን ጥቅሙ፤ …. ንጉስ መሆን ጉዳቱ' ብሎ የግል ሀሳብን ግራ ቀኝ የሚያዳምጡበት ሰዓት ነው ወይ? ....
‹‹ሳታቅማሚ ዘለሽ መሪውን ትጨብጫለሽ፤ መርከቧን ታቀኛለሽ፤ ማዕበሉን ትታገያለሽ! ጮኸሽ ትዕዛዝ ትሰጫለሽ። አንዱ የመርከቧን ህልውና ለመፈታተን ከመጣ፤ በቀጥታ ትተኩሻለሽ! ቀጥታ ትተኩሻለሽ! … እገሌ አትይውም። ስም የለሽ፤ መልክ የለሽ ነው። በጆሮሽ እንደሚያፏጨው ንፋስ፤ መርከቧን እንደሚንጣት ሞገድ፣ ስም የለሽ ምጣት ነው! ታዲያ ስትተኩሽ… በጥይትሽ ተመትቶ የወደቀው ሰው፤ ትናንት ጠምቶሽ ውሃ ያጠጣሽ ሰው ይሆናል። አለያም ደግፎሽ ከሠገነቱ ያወጣሽ ጎበዝ ይሆናል። … ግን ስም የለውም። ማንም ስም የለውም… ።! አንቺ መሪውን የጨበጥሽው እንኳን ስም የለሽም። መርከቢቷ ብቻ ናት ስም ያላት… ሀገር ብቻ ናት ስም ያላት!... እ…። አሁንስ ገባሽ?፤ ተረዳሽኝ!?›› ይላታል።
አንቲገን ግን፤ ‹‹ልረዳህ አይደለም እዚህ የመጣሁት። ይኸ ያልከው ሁሉ ለአንተ ይጠቅምህ ይሆናል። እኔ ግን እዚህ የመጣሁት እምቢታየን ለመግለጽ ብቻ ነው›› ትለዋች።
‹‹እምቢታ ቀላል ነው፣ አንቲገን። እምቢታ ቀላል ነው። ዕዳው ሞት ቢሆን እንኳን፣ እምቢታ ቀላል ነው። ቁጭ ብሎ የሚመጣውን መጠበቅ ብቻ ነው። ያ የሰነፍ ሰው ድርሻ ነው። እሺ ስትይ ግን፣ ላብሽን ማንጠፍጠፍ፤ እጅሽን ጠቅልለሽ፤ እስከ አንገትሽ ድረስ በህይወት ማጥ ውስጥ መዘፈቅ ይኖርብሻል›› ይላታል።
እንደ ሴቴ ሸረሪት ጽንስ ራሱን በራሱ የሚውጠው፤ ከውቂያኖስ መግባት የሚመኘው አዋሽ፤ አሁን ወደ ብርሃን መውጫ በእርጋታ እየፈሰሰ ነው። አባይ ጉባ ተሰናድቶ፤ ብርሃን እያፈሰሰ ነው። ጊቤ ኮሽታ ሳያሰማ፤ በኮይሻ ብልጽግናን በጸጥታ እየተጣራ ነው። የኢትዮጵያ ወንዞች፤ ‹‹የኢኮኖሚ ዋልታ፤ ቡና ቡና›› በሚሉት የጅማዎቹ ህጻናት ዜማ ዚቅ ‹‹ስንዴ ስንዴ›› እያሉ ነው።
መጭው ጊዜ ብሩህ ነው።
Abiy Ahmed Ali
Sandokan Debebe Jemaneh
Kassahun Gofe Balami
Addisu Arega Kitessa
Wondwosen Andualem Abaye
Negera Duguma Gutema
Haftay Gebre-Egziabher
Ashinie Astin
Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ
Jantirar Abay - ጃንጥራር አባይ
ሀሳብን ከመፍራት- ሀሳብ ወደማፍራት ስትሄድ ከቃል ወደ ባህል ታድጋለህ።
19/08/2024
#የኮርደር _ልማት_በሻሸመኔ
👉ባለአምስት በሯን ከተማ ባለብዙ ውበት እና ባለብዙ እድገት የሚያደርግ ስርነቀል ልማት።
👉የህዝብ ተባባሪነት + የአመራር ቁርጠኝነት = የሻሽቱ የከፍታ ሰገነት ❤
03/08/2024
ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ከብሔራዊ የንግድ ተቋማት የፀረ ንግድና ገበያ መቆጣጠር የጋራ ኮሚቴ አባላት ጋር የህገ ወጥ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪና ምርትን የማከማቸት ህገ ወጥ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ ውይይቶች እየተከናወኑ ሲሆን በየክልሉ እየተተገበሩ ያሉ ተግባራት አፈፃፀምም በየእለቱ በዝርዝር እየተገመገሙ ነው።
በሪፖርቱ እጅግ አበረታች የሆነ ጅምር የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙና በሚቀጥሉት ቀናትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።
ለአብነት በትላንትናው ቀን ብቻ 324 የንግድ ድርጅቶች ማሰጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 542 የንግድ ተቋማት ታሽገው የንግድ ፍቃዳቸው እንዲታገድ ተደርጓል። በቀጣይም የንግዱ ማህበረሰብ ህጋዊነትን ብቻ ተከትሎ ሊሰራ ይገባል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa