Medaf Academy
Medaf Academy helps students close foundational math gaps through personalized and engaging learning.
መዳፍ አካደሚ እና ወሲ ኢንተርናሽናል ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ በመተባበር ያዘጋጁት ከ 9 እስከ 18 ዓመት ላሉ ልጆች ለ 6 ሳምንታት የሚቆይ የፋሽን ዲዛይን የ ክረምት ትምህርት(ሀምሌ 29 የሚጀምር ሲሆን
ትምህርቱ የሚያካትተው
📍የፋሽን ዲዛይን ትምህርት ከገሃዱ አለም ጋር በማገናኘት 🌎
📍መሰረታዊ ስፌት እና ጋርመንት
ንድፍ( Sketch)🎨
📍መሰረታዊ ሒሳብ እና ጂኦሜትሪ
📍ካይዘን 📉
📍ትምህርታዊ ጨዋታዎች 🎲
📍የፋሽን ሾው ውድድር እና ሽልማት 🏆
🎯አድራሻ- ሳሪስ ኢንዱስትሪ መንደር ወሲ ኢንተርናሽናል ፋሽን ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ፣ ከ ካዲስኮ አደባባይ ከፍ ብሎ ወይንም ከ ዮሴፍ ቤ/ክ ፊት ለፊት ትራፊክ መብራት አካባቢ
🎯 ይህንን ማስፈንጠርያ (ሊንክ) በመጠቀም ይመዝገቡ-https://forms.gle/rgQcU1PHVQCncgD6A
ወይንም 0969040641/0969040610 ደውሉልን
🎯ያለን ቦታ ዉስን በመሆኑ ቀድመዉ ይመዝገቡ🎯
Medaf Academy in collaboration with Wossi Int'l Fashion College presents an exciting 6-Week Fashion Design Program for Kids & Teenagers! 🎨👗
Our comprehensive program includes:
📍 Kaizen for Continuous Improvement 📈
📍Basic Math for Pattern Making and Geometry 📐
📍Educational Games 🎲
📍Sketching Techniques ✏️
📍Fashion Shows with Competitions and Awards 🎉
💎 Three days per week
🎯Join us for a fun and educational experience that combines creativity with real-world skills! 🌟
Contact us 0969040610/ 0969040641
Telegram: /
Facebook: hMedaf Academy
Apply by using this link : https://forms.gle/rgQcU1PHVQCncgD6A
🎯Enroll Now to secure your spot!
Medaf Academy Medaf Academy is an E-learning platform that addresses starting from aged 5 and above for both disabled and non disabled. our educational classes in a professional , affordable, and flexible manner.
24/04/2024
🎯🎯WHY EXAM IS NECESSARY?🎯🎯
18/04/2024
6️⃣ የቤት አስጠኚ መቅጠር (Find a tutor)
በአንድ ክፍል ውስጥ ሰላሳ ተማሪዎች ቢማሩ እነሱን የሚያስተምረው አስተማሪ ለሁሉም የሚሆን ዝግጅት እንጂ ለእያንዳንዱ ተማሪ በተለየ መልኩ የተዘጋጀ ትምህርት አያቀርቡም፡፡ ስለዚህ የቤት ውስጥ አስጠኚ(Tutor) መቅጠር ለልጆቻችን ብቻ በተለየ መልኩ የተዘጋጀ የማስተማር ስነ ዘዴ ሰለሚቀርብላቸው የሚማሩትን ትምህርት የመረዳት አቅማቸው ይጨምራል ይህም ፈተና ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
7️⃣ እረፍት ማድረግ (Take regular breaks)
ሰውነታችን እና አእምሮአችን ያለ እረፍት በትክክል መስራት ስለሚያዳግተውና የማስታወስ አቅሙ እየተዳከመ ስለሚመጣ በጥናታችን መሀል ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት ውስጥ ቢያንስ ከ10-15 ደቂቃ በመሀል ረፍት ማድረግ ውጤታማ ጥናት እንድናደርግ ይረዳናል፡፡በተጨማሪም ሰውነታችን እና አእምሮአችን ሳይደክመው ረዘም ላለ ሰዓት እንድናጠና ብርታት ይሆነዋል፡፡
8️⃣ ራስን መፈተን ( Test yourself )
የጀመርነውን ምዕራፍ እንደጨረስን ምን ያህል ያነበብነውን እንደተረዳን እና ማስታወስ እንደምንችል ራሳችንን መፈተን እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡የማስታወስ አቅማችንንም ፈተና ያሳድግልናል፡፡ ስለዚህ ፈተና ምን ያህል እነዳወቅን ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን የአእምሮአችንን የማስታወሰስ አቅም ያሳድግልናል፡፡
9️⃣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት (Have enough sleep)
ብዙ ተማሪዎች ረዥም ሰዓት ያለ እረፍት ስላጠኑ ወይንም ለሊቱን ሙሉ ተቀምጠው ስላደሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ በማሰብ ረፍት አልባ ለሊቶችን ያሳልፍሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት የአጠናን ዘዴ ድካምና ዝለት ከማስከተሉም በተጨማሪ የቀን ውሏችን ላይ ንቁ እንዳንሆን በማድረግ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ስለዚህ በቂ ረፍት ማድረግ በትምህርት ሕይወታችን ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥ ስለሚያመጣ ከ6-8 ሰዓት በቂ እንቅልፍ ማግኘታችንን መዘንጋት የለብንም ንቁ እና ብሩህ ቀን ለማሳለፍ፡፡
🔟 ጥናትን በጊዜ መጀመር ( Learn everyday)
የትምህርት ዓመቱ ከተጀመረ ዕለት ጀምሮ ሳይዘናጉ ጥናትን ማስኬድ ለማንኛውም ተማሪ እጅግ ውጤታማ የትምህርት ጊዜ እንዲኖረን እና በቂ አውቀት ለመሰብሰብ መሰረት የሚጥልና ጊዜም እንድናተርፍ ከማድረጉም በተጨማሪ ራሳችንን ሳናስጨንቅ እንድንማር ያደርገናል፡፡
ውድ ተማሪዎች እና ወላጆች መዳፍ አካዳሚ ፈተና ማለፍ እና ከፍተኛ ውጤት አስፈላጊ እንደሆነ በእጅጉ ያምናል ነገር ግን የምንማረውን በቅጡ መረዳት እና ማወቅ ከሕይወታችን ጋር ማዋሃድ ለፈተናም ለወደፊት የትምህርት እና የስራ ሕይወታችን መሰረት የሚጥል ነገር ነውና ዋናው ትኩረታችሁ ምን ያህል አውቄአለሁ ? ለምንድነው የምማረው ? ጠቀሜታውስ? የመሳሰሉ ትኩረት የሚሹ ጥያቄዎችን እየጠየቅን እንድንማርና ወላጆችም በፈተና ውጤት ብቻ ሳይሆን ልጆችዎ ለትምህርት ባላቸው ፍቅር እና ጠቀሜታውን ተረድተዎል ወይንስ አልተረዱም በሚል እንድትመዝኗቸው በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ የመዳፍን ቴሌግራም ለመቀላቀል ከታች ባለው ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ https://t.me/MedafAcademy
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Abeba
Addis Ababa
1000