Amhara Reporter
Amhara Reporter
11/12/2022
RIP
30/10/2022
ህወሓት ተስፋ ሲቆርጥ ውሸት ማቀናበር ያደገበት ልማዱ ነው።
ህወሓት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በትር መቋቋም ሲያቅተው የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋትን ተያይዞታል። የሐሰት ፊልሞችን እያቀናበረ የሐሰት ክሶችን መፈብረክ ቀጥሏል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተላበሰው ዕሴት ሕዝባዊነት መሆኑን ዓለም ያውቀዋል። ይሄንንም እንኳን በሀገሩ እና በሕዝቡ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮው በተግባር አሳይቷል። ይሄንንም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሰላም ካስከበረላቸው ሕዝቦች የተሰጡት የምስክር ወረቀቶች እስከ ዘለዓለም ሲናገሩለት ይኖራሉ።
ህወሓትና ጋሻ ጃግሬዎቹ መጀመሪያ ተቋሙን ለማፍረስ ሞከሩ፤ አልተሳካም። ጥቅምት 24 ሌሊት በክህደት ወግተው ሊያጠፉት ተፍጨረጨሩ፤ አልተሳካም። ደጋግመው ጦር መዘዙበት፤ ሽንፈት አከናነባቸው። አሁን በመጨረሻ ወደ ቆርጦ ቀጥል አመላቸው ገቡ።
አንዳንድ የሠራዊታችን አባላት በተለያዩ ጊዜያት፣ ለተለያየ ዓላማዎች፣ የተናገሩትን ቆርጦ እየቀጠለ፣ የሠራዊቱን ስም በማጥፋት፣ ጉዞውን የሚገታ መስሎት፣ ህወሓት መከራ እያየ ነው።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከግንዘቤ እጥረትም ሆነ የጠላት መጠቀሚያ በመሆን ከዕሴቱ ውጭ የሆኑ መልክቶችን የሚያስተላልፉ አባላቱን በከፍተኛ የዲሲፒሊን ጥሰት ይቀጣል። ይሄንንም የሚያደርገው ራሱን እያረመና እያበቃ የመሄድ ነባር ሥርዓት ስላለው ነው። የተልዕኮው ዋና ግብ ሕዝብን ከጉዳት መጠበቅ ስለሆነም ነው።
ስለሆነም ሕዝባችን ከህወሓት የቆርጦ ቀጥል ሤራ እንዲጠነቀቅና በዓላማና በአቋም ከሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ቅንጅት እንዲያጠናክር፣ የመከላከያ ሠራዊት ጥሪውን ያቀርባል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
"እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" - ጭካኔ የተሞላበት የህወሓት ውሳኔ
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የሰሜኗ ኮከብ የሆነችውን መቀሌ ከተማ በቅርብ ርቀት ከበባ ውስጥ ማስገባቱን ተከትሎ ከተማዋ በእጁ እንደማትቆይ የተረዳው አሸባሪው የእናት ጡት ነካሹና የወንበዴዎች ስብስብ የሆነው የህወሓት ቡድን በመቀሌ ከተማ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ዘራፊዎችን በመበተን ወደ በረሃ እግሬ እውጪኝ እያለ መሆኑ ታውቋል።
አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ በፊትም በ2013 ዓ/ም መከላከያ መቀሌን ከበባ ውስጥ ሲያስገባ በተመሳሳይ ሁኔታ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በመልቀቅ በከተማው ስርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን፣ ህዝቡ ያለው ቀሪ ንብረት እንዲዘረፍ እና በርካቶች በማጅራት መቺ ህይወታቸውን እንዲያጡ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ የሽብር ቡድኑ ሴራ በዋናነት መከላከያ ሰራዊት ከተማ በማረጋጋት ስራ እንዲጠመድ ለማድረግ ታስቦ ቢሆንም አሳዛኙ ጉዳይ ቡድኑ ለህዝብ ደንታ የሌለው መሆኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑ ነው። የመቀሌ ህዝብ ይህን ሴራ በደንብ የተረዳው ሲሆን መደበቂያ ያለው የዘራፊዎች ሰለባ ላለመሆን ንብረቱን ይዞ ወደ ገጠር አካባቢዎች እየሸሸ እንደሚገኝ ታውቋል።
25/10/2022
የሁለት ጁንታዎች ወግ
ጁንታ 1 ፡- ወዴት እየሄድክ ነው ?
ጁንታ 2 ፡- ለድርድር ወደ ደቡብ አፍሪካ እየሄድኩ ነው፤ አንተስ ?
ጁንታ 1 ፡- ዋይ ለእኔማ እድለ ቢስ ነኝ፡፡ አታይም እንዴ . . . ዙሪያችንን ተከበብን'ኮ፡፡ ወደ ተንቤን በረሐ እየገባን ነው፡፡
ጁንታ 2 ፡- አይዞን የትም ብንሆን እንደመስሳቸዋለን !
ጁንታ 1 ፡- ትቀልዳለህ እንዴ ! ? አንተማ ምን አለብህ ? ! በድርድር ስም ሄደህ በዛው ትቀራለህ፡፡ ይልቅስ እንደመስሳለን ስንል አሁን የራሳችን ያልነው ሕዝብ እንዳይደመስሰን ፍራ፡፡ ትግራዋይ አምርሯል፡፡ አመራሮች ወደ ተንቤን በረሐ የሚወርዱት ለእኛ ሳይሆን እራሳቸውን ለማዳን፤ ለጥቅማቸው ነው እያለ እያጉተመተመ ነው፡፡
ጁንታ 2 ፡- ታዲያ አስቀድምን እንደዚህ የሚሉትን ለምን አንደመስሳቸውም !
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Gotera
Addis Ababa