Inter-ministerial Task force

Inter-ministerial Task force

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Inter-ministerial Task force, Public & Government Service, Addis Ababa.

Photos from Inter-ministerial Task force's post 01/06/2022

ግብረ-ኃይሉ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ያከናወናቸውን ተግባራት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ማብራሪያ ሰጠ

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ግጭት አውድ ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ከማጣራትና ተጎጂዎችን ከመጠበቅ እና ከመደገፍ አንጻር ስራዎችን ለማስተባበር የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል ጽ/ቤት እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በዛሬው ዕለት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የተከናወኑትን ተግባራት በተመለከተ የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና የግብረ-ኃይሉ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ካሳ ለመድረኩ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፤ በሪፖርታቸውም በአክሱም በማይካድራ እና በሌሎች የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ የተለያዩ የጦር ወንጀሎች እና በሴቶች ላይ የተፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን፤ እንዲሁም በመንግስት እና በግለሰቦች ንብረት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ በቦታው የተሰማራው የምርመራ ቡድን እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባር በገለጻቸው ላይ አካተው አቅርበዋል፡፡

ከምርመራ ሂደት ጋር በተያያዘም ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከመከላከያ ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ከክልል ዐቃቤ ህግ ቢሮ የተውጣጡ ባለሙያዎችን የያዘ ቡድን ተዋቅሮ በአፋርና አማራ ክልል ለምርመራ ስራ ተሰማርቶ አብዛኛውን የምርመራ ስራ ማጠናቀቁን ለአምባሳደሮቹ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ምርመራው በ9 የተለያዩ ቦታዎች ማለትም በሰሜን ሽዋ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ በኮምቦልቻ፣ በደሴ፣ በላሊበላ እንዲሁም በአፋር ክልል የተለያዩ ቦታዎች እየተካሄደ እንደሚገኝና ቡድኑም የሰውና ገላጭ ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ዶ/ር ታደሰ አብራርተዋል፡፡
ተጎጂዎችን መልሶ ከማቋቋም፣ ህጎች እና አሰራሮችን ከማሻሻል፣ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትንም በዝርዝር ለታዳሚው ገልጸዋል፡፡

ከአቅም ግንባታ ስራዎች ጋር በተያያዘ ጉዳዩን ለመመርመር ለተሰማራው የምርመራ ቡድን ምርመራው ዓለማቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል የሚያግዙ ጾታን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ውስብስብ ጥቃቶች የሚመረመሩበት ህጋዊ እና ሳይንሳዊ አካሄድን አስመልክቶ ዓለማቀፋዊ ደረጃዎች እና የተመረጡ ልምዶችን መሰረት ያደረገ ከፍተኛ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ እንዲሁም የአለም አቀፍ የወንጀል ምርመራን ስርዓትን እና በልዩ የወንጀል ምርመራ አካሄድ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን (OHCHR)፣ የተባበሩት መንግስታት የአደገኛ መድሀኒትና እና ወንጀል መከላከል ጽ/ቤት (UNODC) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (EHRC) ጋር በመተባበር በ3 ዙሮች ለሰልጣኞች መሰጠቱን እና በቀጣይም በተለያ ርዕሠ-ጉዳዮች የምርመራ ቡድኑን አቅም ለማጎልበት የሚያዙ ስልጠናች እንደሚሰጡ ዶክተር ታደሰ ለአምባሳደሮቹ ባደረጉት ገለጻ ወቅት ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተከፋይ የሆኑት አውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮችም በቀረበው ገለጻ ላይ ተመርኩዘው ያሏቸውን ሀሳቦች እና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን እና የሴክሬታሪያቱ ኃላፊ ዶ/ር ታደሰ ካሳ ምላሾች እና ማብራሪያዎችን ሰጥተው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Photos from Inter-ministerial Task force's post 28/04/2022

Intensive training kicks off on international criminal investigation

Co-organized by the Investigation and Prosecution Committee (IPC) of the Inter-Ministerial Taskforce, the UN Office of the High Commissioner for Human Rights and The Hague-based Institute for International Criminal Investigation, a six-day (26 April-1 May 2022) world-class Training of Trainers is being offered to core members of the IPC.

The training aims to further build the investigative knowledge and technical skills of the IPC who is mandated to conduct investigation into all allegations of serious violations of international law committed in the context of the conflict in Northern Ethiopia - including those amounting to international crimes.

The training mainly focuses on acquainting high-end notional and practical approaches in relation to investigation and mission planning, documenting crime scenes, collecting information and interview skills (using PEACE model), open source research, social media analysis and review of materials, military organisations, operations and weapons (command and control systems, chains of command), forensic death investigations (injury identification, exhumation of human remains from mass graves), analysis skills (evaluation of information, standards of proof), and sexual violence in armed conflict.

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa