Kidist Arsema

Kidist Arsema

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kidist Arsema, Religious Center, united state, Addis Ababa.

29/05/2026

"በክብር ያዩሽ ዓይኖች የተመሰገኑ ናቸው" - አርኬ ዘግንቦት ፳፩ (21)

"በዚህች ዕለት (ግንቦት 21) አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ።" - ስንክሳር ዘግንቦት 21

"በዚህ ወር (በግንቦት) በሃያ አንድ ቀን በግብጽ አገር ደብረ ምጥማቅ በምትባል በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ከያገሩም ሁሉ ይመጣሉ። እነዚህ ሁሉ ሰቀላ ሠርተው ድንኳን ተክለው አጎበር ጥለው ይከትማሉ፤ ከሃያ አንድ ቀን ጀምረው እስከ ሃያ አምስት ቀን ድረስ በፍጹም ደስታ ክብር የድንግልን በዓሏን ማክበር ይጀምራሉ። ድንግልም ከግንቦት ሃያ አንድ ቀን ጀምራ እስከ ሃያ አምስት ቀን ድረስ ሳታቋርጥ ባምስቱ ዕለታት ከመላእክት ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር ትገለጽላቸው ነበር። ክርስቲያንም እስላምም በገሃድ ተገልጻ ያዩዋት ነበር፤ በፍጹም ክብር በፍጹም ደስታ በዓሏን ያከብሩ ነበር።" - መቅድመ ተአምረ ማርያም 23 - 25

"እንደፀሐይ እያበራች ከሰማይ የምትወርደዋ ይህች ማን ናት?" ዚቅ ዘግንቦት ደብረ ምጥማቅ

👉"ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች" ራእይ 12፥1

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


United State
Addis Ababa