Pro Elesa edelu

Pro Elesa edelu

Share

የእዉነት ጥግ ኢየሱስ ብቻ ነው ። መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ። ያድናል ኢየሱስ ። ወንጌል ይለወጣል

16/02/2024

👉 በሕይወታችን ብዙ ፈተናዎች እንደሚያጋጥሙን ይታወቃል። በሚያጋጥሙን ልክም ድል እያደረግን የመጣናቸው እንደተጠቁ ሆኖ ከአቅም በላይ የሚሆኑብን ፈተናዎች ብዙ ናቸው።

👉 ይህንንም ተከትሎ ፈተናዎችን እንዴት ድል ማድረግ እንደሚንችል የአህያውን ታርክ ላጋራችሁ ወደድኩኝ። ነገሩ እንዲህ ነው

👉 የአንድ ገበሬ አህያ ጊቢ ውስጥ እየቦረቀ ሳያስበው ጉርጓድ ውስጥ ይገባል። ለመውጣት መላ በመፈለግ ፋንታ ጉርጓድ ውስጥ ሆኖ እርዳታን ለማግኘት መጮኸ ይጀምራል።

👉 በጩኸቱ የተገረመው ገበሬ ይሰራ የነበረውን ስራ ትቶ ወደ አህያው በፍጥነት ይሄዳል። ከደረሰ በሗላ በቤቱ ውስጥ የደከመ አህያ መሆኑን ያረጋግጣል። ገበሬው አስቦ ያሉትን ገና ጉልበታቸው ያልተበሉ አህያዎቹን ያስብና ይሄ አህያ ባለበት ጉርጓድ መቀበር እንዳለበት ይወስናል።

👉 ከወሰነ በሗላ ብቻውን መቅበር እንደማይችል አስቦ ጎረቤቶቹንና የመንደር ሰዎችን ጠርቶ መቅበሩን ያስጀምራል። ከሰፈር የመጣው ሁሉ ቆሻሻውን አፈሩን እየጣለ መቅበር ስጀምር አህየረውም እርዳታ ፍለጋ መጮኸ ጀመረ ነገር ግን ሰመመ አልነበረውም።

👉 ማንም ልደርስለት እንደማይችል የተረዳው አህያ መጮኸ ያቆምና የሚጣልበትን ቆሻሻን እየተንቀሳቀሰ ወደ ታች ማሳለፍ ስጀምር ጉርጓዱ እየተሞላ ደለል ወደ መሆን ተቀየረና አህያው በርግጎ በመሮጥ ነፍሱን ያድናል።

⚠️ ይህ የአህያ ፈተናበሕይወታችን እያጋጠሙን ካሉ በተጨባጭ ፈተናዎች የተለየ ገፅታ የለውም። ባላሰብነው ድንገተኛ አጋጣሚ ስንወድቅ ከወደቅንበት ልያነሱን ከሚያብሩ ይልቅ ልቀብሩን ከሚያብሩብን ቀላል አይደሉም።

🔐 ይህ ስሆን ግን ከገባንበት ጉርጓድ አፈር ስጨምሩብንና ቆሻሻ ስጥሉብን እያየን ዝም የሚንል ከሆነ በሕይወት እያለን መቀበር ይሆንልናል።

🙏 ስለዚህ እላቸዋለሁ ከሚያጋጥሙን ፈተናዎች የሆነ ይሁን ብለን ከመቀመጥ በተቻለን አቅም እየተንቀሳቀስንና የማይወክሉን ሆኖ ከሚጣሉብን ቆሻሻዎችም እየተንቀሳቀስን በማሳለፍ ፈተናዎቻችን ድል ማድረግ ይሁንልን መልዕክቴ ነው።

ከማህበራዊ ሚዲያ እንማሪበታለን ብዬ የቀነጨብኩት

ትምህርት ከእግዚአብሔር ነው መማር መልካም ነው

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa