Wollo Times

Wollo Times

Share

https://t.me/ethifirst ኑ ተከተሉን ስለ ሐገራችን እና አለም አቀፍ የሆኑ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች የተጣራ መረጃ ያገኛሉ ። ስለተከተሉን ለእርስዎ ትልቅ አክብሮት አለን !! እናመሰግናለን

30/04/2026

"እኛ አፋሮች ከአክሱም ሙስሊሞች ጎን ነን! "
ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች!!!. ✊

"ወንድምህን ስትወደው ለአላህ ብለህ ውደደው" 💝

"ረሱል ﷺ🤍❤️‍🩹🫶💝

#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች‼️✊
#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች‼️✊

#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች!

Wollo Times
https://www.facebook.com/share/1DmcLXERwH/

Photos from Wollo Times's post 29/04/2026

ገንዘብ ካለ. . በሆርሙዝ መንገድ አለ ።
ይህችን የቅንጦት መርከብ ፡ መርከብ ወይም ጀልባ ብቻ. ብሎ መጥራት ትንሽ ይከብዳል ።
ምክንያቱም አጠቃላይ አሰራሯ ከመርከብም ሆነ ከጀልባ በላይ ነው ።
ኖርድ በሚል ስያሜ የምትታወቀውና ፡ ንብረትነቷ የሩሲያዊው ቢሊየነር አሌክሲ ሞርዳሾቭ የሆነችው ይህች የቅንጦት ጀልባ አንድ ጊዜ ነዳጅ ከሞላች ፡ የአለምን ግማሽ መዞር የምትችል ሲሆን በላይዋ ሁለት ሄሊኮፕተር ማሳረፍ የሚችል ሄሊፓድ ተሰርቶላታል ።...
ብዙ የቅንጦት ጀልባዎች ሄሊፓድ ስላላቸው ይህ አይገርም ይሆናል ። የዚች ጀልባ የሚለየው ሄሊኮፕተሮቹ ከጀልባዋ አናት ላይ ካረፉ በኋላ በሊፍት መሰል ነገር ወደታች ይወሰዱና ፡ በጀልባዋ የታችኛው ክፍል በተዘጋጀላቸው ቤት ( ሀንጋር ) ውስጥ እንዲቆሙ ይደረጋል ።....
ለአጠቃላይ ግንባታዋ አምስት መቶ ሚሊየን ዶላር የወጣባትና ፡ የቅንጦት ጀልባዎችን በጥራት በመስራት በሚታወቀው የጀርመኑ ላርሰን ኩባንያ የተገነባችው .. ይህች ውድ ጀልባ ፡ እስከ 36 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ ፡ ከእምነበረድ የተሰራ መታጠቢያ ቤት ያላቸው 20 እጅግ ዘመናዊ ማረፊያ ክፍሎች አሏት ።.....
142 ሜትር በምትረዝመውና በ ባለ ስድስት ፎቋ ፡ ኖርድ የቅንጦት ጀልባ ውስጥ ያለው ይህ ብቻ አይደለም ፡ ትልቅ የመዋኛ ገንዳ . .. ዘመናዊ የድምፅ እና የምስል መሳሪያዎች የተሟሉለት ሲኒማ ቤት ፡ ጂም. . ሳውና እና ስፓ በውስጧ ይዛለች ።
እና ከአንዱ ፎቅ ወደሌላኛው ለመሄድ የሚያገለግሉ ዘመናዊ የመስታወት ሊፍቶችም ተገጥመውላታል ።
እንዲሁም በውስጧ አነስተኛ ሰርጓጅ መርከብ እንዲኖራት ተደርጋ የተሰራች ናት ......
ይህች ተንቀሳቃሽ ቤተመንግስት ሰሞኑን ዱባይ ቆይታ ነበር ፡ እና ከትናንት ወዲያ ወደ ኦማን ለመጓዝ ፈልጋ ጉዞ ጀመረች ።....
ኖርድ ከዱባይ በኦማን በኩል ወደ ሲሸልስ ልታደርግ ባሰበችው በዚህ ጉዞ ፡ ሆርሙዝን ማቋረጥ ግድ ነው ። እና ጉዞዋን ወደ ሆርሙዝ አድርጋ መንገድ ጀመረች ።.....
በሺህ የሚቆጠሩ ምስኪን መርከቦች መንገድ ተዘግቶባቸው ቆመዋል ። የቅንጦት ጀልባዋ ኖርድ በየቦታው የቆሙትን መርከቦች ሰላም እያለች በልበሙሉነት እየተጓዘች ወደተዘጋው ሆርሙዝ ደረሰች ።......
የኢራን የባህር ሀይል አባላት ኖርድ ማን እንደሆነችና ወዴት እንደምትሄድ ሁሉንም ያውቃሉ ።
እና ይህችን የወዳጅ ሀገር ሰው የሆነውን የሩሲያዊው ቢሊየነር ግዙፍ ጀልባ ፡ በሆርሙዝ ልታልፍ ስትመጣ አንዳች ችግር እንዳያጋጥማት አድርገው አሳልፈዋታል ።..
በአካባቢው ችግር ከተፈጠረ ከባለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ብዙ መርከቦች ወደዚህ ስፍራ መምጣት በማይደፍሩበት ወቅት ፡ 500 ሚሊየን ( ግማሽ ቢሊየን ዶላር ) ዋጋ ያላት የኖርድ በልበ ሙሉነት ሆርሙዝን ለማቋረጥ መድፈር ፡ ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሆኗል

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


America
Addis Ababa