Road Safety & Insurance Fund Service
This is the official page of Road Safety & Insurance Fund Service
22/10/2025
ለትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ... ....
ጥቅምት 12 / 2018 ዓ.ም / መ.ደ.መ.ፈ.አ /
የመንገድ ደህንነት መድን ፈንድ አገልግሎት ለትራፊክ ፖሊሶች ፣ ለአደጋ መርማሪዎች እና ለመንገድ ደህንነት ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረወ ሀገር አቀፍ ስልጠና ተጠናቀቀ ።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የተቋሙ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ ለሰልጣኞት የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ተቋማቸው የግንዛቤና የህግ ማስከበር ሰራዎችን በሰፊው እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል። ከዚህም ጋር በተያያዝ ሰው ሰራሽ በሆኑ ችግሮች የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ግንዛቤ በማስጨበጥ ህግን በማስከበር የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ አንስተዋል።
አክለውም የተሰጠውን ስልጠና በሙሉ አቅም በመጠቀም የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሀገር ደረጀ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በመጨረሻ ስልጣኞች ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው የተሻለ ስራ እንደሚሰሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተናግዋል።
21/10/2025
የትራፊክ አደጋ መቀነሻ መፍትሄዎች ላይ ስልጠና ተሰጠ።... -- ....
ጥቅምት 11/ 2018 ዓ.ም
የተሸከርካራ ፍጥነትን ለመግታት የሚወሰዱ መፍትሄዎች በመተግበር አደጋን ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ፣ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምርመራና ሪፖርት አዘገጃጀት፣ በተደጋጋሚ አደጋ የሚደርሰባቸው ቦታዎች ልየታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገር አቀፍ ስልጠና ለባለመያዎች ተሰጠ ።
21/10/2025
ፎቶ ዜና
የመንገድ ትራፊክ አደጋ ምርመራና ሪፖርት አዘገጃጀት፣ በተደጋጋሚ አደጋ የሚደርሰባቸው ቦታዎች ልየታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሀገር አቀፍ የስልጠና መድረክ ላይ ውይይት ሲደረግ ።
21/10/2025
የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ጉዳዮች የሀገር አጀንዳ ሊሆነ እንደሚገባ ተገለፁ.. ... ...
ጥቅምት 11 / 2018 ዓ.ም
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ለፌድራል ፖሊስ፣ ለሁለቱ ከተማ መስተዳድር ፣ ለክልል ትራፊክ ፖሊስ አባላት ፣
ለትራፊክ አደጋ መርማሪዎችና ለመንገድ ትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
በስልጠና መድረኩ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጀማል አባሶ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። አሳቸውም እንደገለጹት የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ለመቀነስ በተግባር አውቆ የሚያሳውቅ ባለሙያን በማፍራት ራስን በመጠበቅ ህዝብ እንዳይዘናጋ ለማድግ በጥናት ተለይቶ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ስልጠናው የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ኃላፈነታቸሁን እንድትወጡ ለማስቻል የአሰልጣኞች ስልጠና ተዘጋግቷል ብለዋል።
19/10/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
P.O.BOX1288