Ankuar
We are a team of neutral observers - to provide you with core analysis of politics, culture and society in Ethiopia. www.ankuar.com
28/01/2025
. . . ሰዎች መንግሥትን የመሠረቱት፣ በመንግሥት አልባው ዓለም (State of Nature) የማይቻል በነበረው የመተማመን እና የእኩልነት መንፈስ ተፈጥሯዊ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅና የተፈጥሮን ሕግ ለማረጋገጥ ነው። ይሁንና ግን መንግሥት የተፈጥሮ ሕግን አይተካም፣ እንዲሁም የተፈጥሮ ሕግ ያጐናፀፋቸውን መብቶች መጣስ ወይም ችላ ማለት አይችልም። መንግሥት የታማኝነት ወይም የባላደራነት ተፈጥሮ አለው። ስለመብቶቻችን መጠበቅ አደራ እንጥልበታለን፤ ነገር ግን እነዚያን መብቶች ለእርሱ አሳልፈን አንሰጠውም። ስለዚህም ተፈጥሯዊ መብቶችን የሚጥስ መንግሥት እምነቱን እንዳፈረሰና አደራውን እንደበላ ነው፤ እናም ሕዝቦቹ እርሱን በመቃወም - አስፈላጊ ከሆነ በኃይልም - መብቶቻቸውን እና ነፃነቶቻቸውን የማስከበር መብት አላቸው። ጥሰቱ ከፍተኛ መጠን ያለው በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ሕዝቡ አብዮት የማስነሳት መብት አለው፤ ይህም ማለት መጀመሪያ ለመንግሥት ተሰጥቶ የነበረውን ሥልጣን መልሶ መንጠቅ ማለት ነው . . .
. . አንድ ሕዝብ ሥልጣንን ከመንግሥት ላይ በተመቸው ጊዜ በቀላሉ መግፈፍ መቻሉ፣ መንግሥት ባለመኖሩ ምክንያት የሚከሰት የሥርዓት አልበኝነት ሁኔታ (Anarchy) መገለጫ አይደለምን? ለዚህ ተቃውሞ፣ ጆን ሎክ ሁለት ምላሾች አሉት። በመጀመሪያ ደረጃ፣ መንግሥታት በዜጐቻቸው ላይ ለሚያደርሱት ለእያንዳንዱ እፍኝ ለማይሞላ በደል መገልበጥ አለባቸው የሚል አመለካከት የለውም። ጨቋኝ መንግሥታት (Tyrants)፣ በድርጊታቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተጐጂ ካልሆነ በቀር አይታመፅባቸውም። ሁለተኛ፣ ቀድሞውኑ ህልውናውን የሚያረጋግጡለትን ብቸኛ ተግባራት ወይም ኃላፊነቶች ባለመፈፀሙ ምክንያት፣ ጨቋኝ የሆነ መንግሥት እራሱን በራሱ የሚጥልበት ሁኔታ አለ።"
ከ“ሁነኛውን ማኅበራዊ ውል ፍለጋ - ዘመናትን የተሻገሩ ፈላስፋዎች እና የፖለቲካ እሳቤዎቻቸው” — ከመጽሐፍ የተቀነጨበ።
Now available on Apple Books:-
http://books.apple.com/us/book/id6740996164
Soon will be available on other platforms
21/03/2023
የጀዋር መሐመድ ትንታኔያዊ ጽሁፍ በአማሪኛ - ቀጣዩ የትግል ምዕራፍ
በቅርቡ ጀዋር መሐመድ 76 ገጽ ያለው ሰፊ ትንታኔያዊ ጽሁፍ “Boqonnaa Qabsoo Itti Aanu” በሚል ርዕስ በኦሮምኛ አዘጋጅቶ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። ሙሉውን ጽሁፍ በአማርኛ ለማግኘት ሊንኩን ይከተሉ።
https://ankuar.com/jawar-mohammed-next-chapter-of-the-struggle-amharic/
17/08/2021
የባሕላዊ ሀገር ግንዛቤው የኢንላይትመንት የማህበራዊ ውል እና የሉዓላዊነት እሳቤዎችን ሊተካ እንደሚችል ሄርደር ያስባል። መንግሥት አርቴፊሻል ፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን፣ ሀገር ግን የተፈጥሯዊ እድገት ውጤት ነበር። ይህ፣ ህብረተሰብን፣ በውስጡ ያሉት አካላት በሕብራዊ (harmonious) ዝምድና የተሳሰሩበት አንድነት (organic unity) አድርጎ የመመልከት ራዕይ ነው። ሄርደር ይህንን ሲል የህብረተሰብ አንድ ክፍል ከአጠቃላዩ ወይም ከመላው ያንሳል ማለቱ አይደለም፣ ወይም አንድ ግለሰብ ከአጠቃላዩ ማህበረሰብ ያነሰ መሆኑን አያመለክትም።
ዘርዘር ያለውን የዮኃን ጎትፍሬድ ሄርደር የፖለቲካ ጽንሰ-ሀሳብ በዚህ ሊንክ ማንበብ ይችላሉ፦
https://ankuar.com/johann-gottfried-herder/
«ሀገር ተፈጥሯዊ የእድገት ውጤት ነው»፣ ጆኃን ጐትፍሬ ሄርደር (1744-1803) | Ankuar A media in Ethiopia that provides major stories and analysis on politics, society and entertainment.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa