Habesha Daily
ፈጣን እለታዊ የሀገር ውስጥ የውጭ ዜናዎች እንዲሁም አዳዲስና ትኩስ የሀገር ውስጥና የውጭ ስፖርት ዜናዎች ይደርሶታል።
20/08/2024
የታንዛኒያ የፖሊስ አዛዥ በቡድን ጾታዊ ጥቃት የደረሰባትን ሴት "የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ናት" በማለታቸው ከኃላፊነት ተነሱ
በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዶዶማ በቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ደርሶባታል የተባለችውን ሴት ጉዳይ ከወሲብ ስራ ጋር በማያያዝ አወዛጋቢ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አንዲት ወጣት ሴት ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባት የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋትተሰራጭቷል። በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ታንዛኒ ድርጊቱ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።አራት ሰዎች ሰኞ እለት በተጠረጠሩበት ጾታዊ ጥቃት ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ቢመሰረትባቸውም ወንጀሉን አለመፈፀማቸውን ተናግረዋል። እሁድ እለት በዋና ከተማዋ ዶዶማ የሚገኙት የፖሊስ አዛዥ የሆነችው ግለሰብ ለታንዛኒያ ጋዜጣ ጥቃት የደረሰባት ሴት የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ነች ሲሉ ተናግረዋል።
ይህንን አስተያየት ተከትሎ የታንዛኒያ ብሄራዊ የፖሊስ ሃይል ይቅርታ በመጠየቅ የፖሊስ አዛዧን ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወሩን ገልጿል። የብሔራዊ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዴቪድ ሚሲሜ እንደተናገሩት የፖሊስ ሃይሉ በመገናኛ ብዙኃን በተሰራጨው መግለጫ የተናደዱትን ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ ይፈልጋል ብለዋል።ሚሲሜ አክለውም የዶዶማ ክልል የፖሊስ አዛዥ የሆነችው ቴዎፒስታ ማሊያ ለሃገር ውስጥ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ተጎጂዋ የወሲብ ሰራተኛ ብትሆንም "እንዲህ አይነት ጥቃት ሊፈፀምባት አይገባም" ሲሉ መናገራቸው ቁጣን ፈጥሯል።
በማህበራዊ ድረ-ገጽ ኤክስ ላይ የፖሊስ አዛዧ ማልያ አስተያየት "ፖሊስ በሴቶች መብት ላይ ያለውን ጭካኔ የሚያሳይ ማስረጃ ነው" ሲሉ በርካቶች ተደምጠዋል። የህግ ባለሙያዋ እና ታዋቂዋ የመብት ተሟጋች ፋቲማ ካሩሜ በኤክስ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት በወሲብ ንግድ የሚሰማሩ ሰዎች ሊደፈሩ አይችሉም ማለት ነው ስትል ተናግራለች። ተጎጂዋ ጥቃት ሲደርስባት በሚያሳየው ቪዲዮ ላይ ተጠርጣሪዎቹ “አፋንዴ”ን ይቅርታ እንድትጠይቅ ሲያስገድዷት ይታያል። በታንዛኒያ "አፋንዴ" የሚለው ቃል ወታደርን ወይም የፖሊስ መኮንንን ለመጥራት ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።
በርካታ የመብት ተሟጋቾች እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በፀጥታ ሀይሉ ትብብር ጾታዊ ጥቃት ሲፈፀም ቆይቷል በማለት ቁጣቸውን ገልፀዋል።ከስልጣን የተነሳችው የፖሊስ አዛዥ በንግግሯ በአልኮል እና በአደንዛዥ እፅ ተፅእኖ ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥቃት ከፖሊስ ጋር አይያያዝም ተናግራለች። አክላም ጥቃት የደረሰባት ሴት በወሲብ ስራ ላይ የተሰማራች ትመስላለች ማለቷ የታንዛኒያን ህዝብ አስቆጥቷል።ቪዲዮው መቼ እንደተቀረፀ ግልፅ ባይሆንም ተጎጂው በሀገሪቱ የንግድ ዋና ከተማ ዳሬሰላም ውስጥ ነዋሪ እንደሆነች ተነግሯል።
ምንጭ ፦Dagu Journal
19/08/2024
የአማራ ክልል ፖሊስ በህፃን ሄቨን ጉዳይ
ያወጣው መግለጫ
ህፃን ሄቨንን በተመለከተ ፖሊስ የሚጠበቅበትን ተወጥቷል፤
የአማራ ክልል ፖሊስ ቀዳሚ ተልዕኮው ወንጀል መከላከል ነው። በተለይም ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ህፃናትና አረጋዊያን ከመጠበቅ አልፎ ወንጀል ሲፈፀም መርምሮ ለፍርድ ማቅረብ ቀዳሚ ተግባሩ ነው። ለዚህም የሴቶችን ጉዳይ ብቻ የሚከታተል የስራ ክፍል አቋቁሞ ፍትህ ለተነፈጋቸው በሚችለው ደርሷል።
ከሰሞኑ በልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አዲስ ሆኖ ብዙዎቹን ያሳዘነው የህፃን ሄቨን ጉዳይ ለክልሉ ፖሊስ በተለይም ለባህርዳር ከተማ 8ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከአመት በፊት ሐምሌ 25/ 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሪፖርት ከደረሰን ጀምሮ እስከ ፍርድ ቀን አብሮን የዘለቀ ጉዳይ ነው።
በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ቆጠጢና አካባቢ የ7 አመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ህጻን ሄቨን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት መርምሮ ለፍርድ ለማቅረብ ከፍትህ ነጣቂዎች ጋር ታግለን መረጃና መስረጃ አሟልተን ለፍርድ አቅርበናል።
በዚህ ሂደት ለሙያቸው ታምነው ለፍትህ መረጋገጥ የሚችሉትን ለፈፀሙ ፖሊሶቻችን ምስጋና እናቀርባለን።ጉዳዩ ብዙ ሂደቶችን አልፎ ውሳኔ ከተሰጠ በኅላም ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በአማራ ፖሊስ ቴልቨዥን ፕሮግራም በተደጋጋሚ እንዲተላለፍ ተደርጓል።
ከሰሞኑ የህፃኗን ጉዳይ ህብረተሰቡ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መከታተሉ የሚደነቅ ሆኖ አንዳዶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተቋማችን ኀላፊነቱን እንዳልተወጣ ይልቁንም የችግሩ አካል አድርገው ለማቅረብ ሲሞክሩ ታዝበናል።
ትችት ለጋራ መሻሻል ጠቃሚ ቢሆንም መርህ አልባ ሲሆን የተግባር እንቅፋት ይሆናል። እንደተቋም ለፍርድ የማቅረብ ተልኳችንን ተወጥተናል ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ከህፃን ሄቨን በተጨማሪ በክልሉ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ92 በላይ አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅመዋል።
የቤት ውስጥ ጥቃቶች በቅርብ ሰውና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ አዳጋች በሆነበት አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ ለፖሊስ የምርመራ አስቸጋሪ ነው።
ስለሆነም ማህበረሰቡ የህፃን ሄቨን ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት እንደሰጠው ሁሉ ነገ ለሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች መረጃና ማስረጃ በመሆን ፍትህን በጋራ እንድናረጋግጥ እንጠይቃለን ።
አማራ ክልል ፖሊስ
ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም
ባህርዳር
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa