Basketo Intellectuals Association-BIA

Basketo Intellectuals Association-BIA

Share

Basketo Intellectual's Association is a non governmental civic society which concern all about the Basket community members.

25/05/2026

Here we Go!
👏

የተከበሩ ፍቃዱ ጋውሻሎ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ከጠዋት 2:30 ላይ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩንቨርስቲ የሦስተኛ ድግሪ መመረቂያ ፅሁፋቸውን ያቀርባሉ።

ይህንን ፕሮግራም ለመታደም የምትፈልጉ በሙሉ አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ CMC አካባቢ በሚገኘው ዩንቨርስቲው ግቢ በመገኘት ከከተማችን ህዝብ ተወካይ ከሆኑት ከዕጩ ዶ/ር ፍቃዱ ጋውሻሎ ጎን እንድትገኙ እናስታውሳችኋለን።

እንኳን ደስ አልዎት የተከበሩ ዶክተር ፍቃዱ ጋውሻሎ!
👏🤝

Photos from Basketo Intellectuals Association-BIA's post 24/05/2026

ኪነ ጥበባዊ ይዘት ያለው ቅስቀሳ በቦላ ጋባላ ቀበሌ
⚖️
ኢዜማ ባስኬቶ በላስካ ዙሪያ ወረዳ ቦላ ጋባላ ቀበሌ የአካባቢው ነዋሪዎች በቀበሌው ያለውን የመሠረተ ልማት እጥረት እና የመንግስት የጤና ጣቢያ ጥራት አለመኖር በታካሚዎች ላይ ያደረሰውን ጫና በኪነ ጥበባዊ ድራማ ተውነው ስሜታቸውን ገልፀዋል።

የኢዜማ ባስኬቶ ልዩ ዕጩዎች በስፍራው ተገኝተው የህዝባችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ትኩረት እስኪያገኝ ድረስ ኢዜማ ትግል እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

⚖️

የቀበሌው ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ኢዜማን እንደሚመርጥ አረጋግጧል።
⚖️

Photos from Basketo Intellectuals Association-BIA's post 22/05/2026

ኢዜማ ባስኬቶ

በጌዜ ኣይማ ቀበሌ
⚖️

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ-ኢዜማ ባስኬቶ በላስካ ዙሪያ ወረዳ ጌዜ ኣይማ ቀበሌ ከነዋሪዎች ጋር በመሠረተ ልማት ጉዳይ ተወያይተዋል። የገዢው መንግስት አርሶ አደሩን በየሦስት ሳምንቱ በየመኖሪያ ቤቱ እየዞረ መዋጮ የሚሰበስበው አካል ለአካባቢው መደበኛ የማብራት አገልግሎት ባለማስገባቱ የህብረተሰቡን ጥያቄ እያወቀ መመለስ አለመፈለጉን አንስተዋል።

ከላስካ 02 ቀበሌ ጋር የሚዋሰነው የዛባ እና ጌዜ ኣይማ ቀበሌ ነዋሪዎች መንግስት የነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ፍላጎት መመለስ ተስኖት አካባቢው ከመብራት አገልግሎት መገለሉን አውስተዋል።

ኢዜማ የመንግስት መሠረተ ልማቶች ለዜጎች በፍትሃዊነት እንዲሰራጭ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲመጣ እየታገለ እንደሚገኝ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ኢዜማ ባስኬቶ ልዩ የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች ባለሚዛን ምልክቱን ኢዜማን እንዲመርጡ ጥሪ ቀርቧል።
⚖️
ኢዜማን ይምረጡ!
⚖️
ሚዛን ነው ምልክታችሁ!

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Basketo Laska
Addis Ababa