Abay Media Network

Abay Media  Network

Share

ታማኝ እና ወቅታዊ ሁሉን አቀፍ መረጃ የሚያገኙበት ሚዲያ!

16/06/2025

ከፍተኛ የኢራን የስለላ ድርጅት ኃላፊዎች ተገደሉ
::::::::::::::::::

ሶስት ከፍተኛ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የስለላ ድርጅት አዛዦች መገደላቸው ተሰማ።

ተካሮ በቀጠለው የእስራኤል እና ኢራን ግጭት እስራኤል እሁድ አመሻሽ በኢራን ላይ በፈመችው የአየር ጥቃት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) የስለላ ድርጅት ኃላፊ ጨምሮ ሁለት ጀነራሎች መገደላቸው ተገለፀ ።

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) የስለላ ድርጅት ኃላፊ ጄኔራል መሀመድ ካዜሚ ፣ ምክትል የደህንነት ኃላፊ ጄኔራል ሀሰን ሞሃቀ እና ከፍተኛ የስለላ መኮንን ጄኔራል ሞህሰን ባገሪ መሆናቸው ነው የኢራን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት።

ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ እስራኤል በኢራን ወታደራዊ እና የኒውክሌር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ ጣቢያዎች ላይ የተቀናጀ የአየር ድብደባ የጀመረች ሲሆን ይህም ቴህራን የአጸፋ ጥቃት እንድትሰነዝር አድርጓታል።

እስራኤልና ኢራን እርስ በእርስ የሚሰነዛዘሩት ጥቃት አሁንም የቀጠለ ሲሆን በኢራን የሚሳኤል ጥቃት ቢያንስ 13 ሰዎች ሲሞቱ ከ370 በላይ ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስራኤል ከአርብ ጀምሮ በቴህራን እየወሰደች ባለችው ጥቃት በትንሹ 224 ሰዎች ሲገደሉ ከአንድ ሺ ሁለት መቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል የኢራን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል ።

ዘገባው የአልጄዚራ እና አናዶሉ ነው
HighLight

14/06/2025

ባለፉት 48 ሰዓታት፦
- ከ240 በላይ ሰዎችን ይዞ ወደ ለንደን ለመብረር የተነሳ የህንድ አውሮፕላን ተከስክሶ በትንሹ 204 ሰዎች አልቀው ዓለም ሀዘኑን ገልጿል።
-ከአደጋው በተአምር የተረፈች አንዲት ነፍስ እና በአደጋው ያለቁ የአንድ ቤተሰብ አባላት የብዙዎች መነጋገሪያ ሆነዋል።
- እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት በመፈጸም የኢራንን ወታደራዊ አዛዦች ገድላለች። የኑክሌር ማብላያዋ ላይ ጉዳት አድርሳለች።
-ኢራን በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ወደ እስራኤል ባላስቲክ ሚሳይሎችን በማስወንጨፍ እና የድሮን ዝናብ በማዝነብ ከፍ ያለ ጉዳት አድርሳለች።
-ትራምፕ፤ ኢራን በኑክሌሯ ጉዳይ ወደ ስምምነት ካልመጣች የከፋ ጥቃት ይጠብቃታል ብለው አስጠንቅቀዋል።
-ፑቲን የእስራኤልን ድርጊት በማውገዝ-ሁለቱን መሪዎች አነጋግረዋል። ውጥረቱን እንዲያረግቡ ጠይቀዋል።
-የእንግሊዙ ኬር ስታርመር እና በርካታ የአውሮፓ መሪዎችም ተማጽኗቸውን ቀጥለዋል።
-የዓለም የነዳጅ ዋጋ በ13 በመቶ ጨምሯል።
ጣና ነሽ ግን ገና ከአዳማ(ናዝሬት) አልወጣችም።

14/06/2025

የእስራኤል መከላከያ ኃይል በኢራን ኢላማዎች ባላቸው ላይ የአየር ጥቃቱን መቀጠሉን አስታወቀ።
መከላከያው በቴሌግራም ባወጣው አጭር መግለጫ “የእስራኤል ኃይል በኢራን ውስጥ ያሉ ስጋቶችን ለማስወገድ ኢላማ ባደረጋቸው ይዞታዎች ላይ ጥቃቱን ቀጥሏል” ብሏል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


4 Kilo
Addis Ababa