Tigst
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tigst, Business service, Merkto, Addis Ababa.
15/04/2026
በህጻኗ ላይ የተፈጸመ ድብቅ ጥቃት ይፋ ሆነ
በአዲስ አበባ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በታማኝነት ስታገለግል የነበረች የቤት ሰራተኛ፣ የ1 አመት ከ8 ወር ህጻን ላይ የፈጸመችው አሳዛኝ ጥቃት በድብቅ ካሜራ ተመዝግቦ ይፋ ሆኗል።
ወላጆቹ ሰራተኛዋን እንደ ቤተሰብ አባል አምነው ለረጅም ጊዜ ከእነርሱ ጋር ቢኖርችም፣ በህጻኗ ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ የመውደቅ አደጋዎች እና በመጨረሻም የእጅ መሰበር ከፍተኛ ጥርጣሬ አስከትሎባቸዋል።
እውነቱን ለማረጋገጥ በቤቱ ውስጥ የተገጠመ የድብቅ ካሜራ ያሳየው ግን እጅግ አስደንጋጭ ነበር።
የተመዘገቡ ጥቃቶች፦
-ህጻኗን ከፍተኛ አካላዊ ጥቃት መፈጸም
-ከቤት እቃዎች ጋር በመጣል እና በጭካኔ መጎዳት
-የህጻኗን እርዳታ እጥረት ተጠቅመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች መፈጸም
ተከሳሽዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከተያዘች በኋላ ለ9 ቀናት ቆይታ ካደረገች በኋላ፣ በ4,500 ብር ዋስትና መፈታቷ ተነግሯል። ይህም በወላጆቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እና ስጋት አስከትሏል።
ተከሳሽዋ ሸጋዬ ምንይች (የመታወቂያ ስም ዝያን) መሆኗ ሲገለጽ፣ በአዲሱ ገበያ አካባቢ ሌላ ስራ ጀምሯል ተብሏል።
የወላጆች ጥንቃቄ፦ ይህ ክስተት ለማኅበረሰቡ ትልቅ ትምህርት ሲሆን፣ ወላጆች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲወስዱ ተመክሮባቸዋል፦
-የህጻናትን ደህንነት በካሜራ (CCTV) በመከታተል መጠንቀቅ
-ድንገተኛ የፍርሃት ስሜት፣ አካላዊ ጉዳት ወይም እንግዳ ባህሪ ካሳዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል
እንደዚህ ያሉ ጥቃቶች በህግ እንዲቀጡ ማህበረሰቡ ድምጹን እንዲያሰማ ለተጎጂዋ ህጻን ፈጣን ፈውስ እየተመኘን፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Merkto
Addis Ababa