Addis Machine and Spare Part Manufacturing Industry
Machine and Spare part
26/11/2022
የቀላልና የከባድ ተሽከርካሪዎችን ፍሬን ሸራ በማምረት ወደ ገበያ ማስገባት ላይ ያለመ ውይይት ተካሄደ።
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የፍሬን ሸራ ምርት ወደ ገበያው ለማስገባት ከዘርፉ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል።
በእለቱም የኢ.ኢ.ግ ም/ዋ/ስ/አስፈፃሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ፣የኢንዱስትሪው ዋ/ስ/አስኪያጅ አቶ ላቀው አስማረ፣ የኢንዱስትሪው ሽያጭ ሀላፊ አቶ ዳዊት ተስፋዬ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
የፍሬን ሸራ ምርትን በስፋት በማምረት በቀጣይ በአከፋፋይነት ከኢንዱስትሪው ጋር እንዲሰሩ የሚያስችል ሁኔታን ለመፍጠር ነው ውይይቱ የተካሄደው።
በምርቱ ጥራት፣አቅርቦትና ዋጋ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም እንዴት የገበያ ትስስር መፍጠር ይቻላል የሚል ሀሳቦች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
በውውይቱ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ የፍሬን ሸራ መመረት ሀገራችን ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች ላይ የውጭ ምንዛሬ ከመቀነስ አንጻር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ ተናግረዋል።
የፍሬን ሸራው በአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በስሩ ከሚገኙ ሰባት ፍብሪካዎች አንዱ በሆነው በአዋሽ አርባ ብሬክ ፓድ ማምረቻ ፋብሪካ የሚመረት ነው።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ፣ ሸገር የብዙሀን ትራንስፖርት፣ አንበሳ የህዝብ አውቶቡስ ፣ታገን ትሬዲንግ፣ ካሪቡ አውቶሞቲቭ፣ ከትራፊክ ማነጅመንት፣አምሮ ዎርክሾ፣አውቶሞቲቭ ታይም እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳትፈዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Around Mexico Square
Addis Ababa
4321