KOBO TIMES

KOBO TIMES

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from KOBO TIMES, Media/News Company, Addis Ababa.

13/03/2022

አብን የኦነግን ካርታ ፎቶ ኮፒ አድርጎ መንቀሳቀስ ባይጀምርም... ከአቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ከዶክተር ደሳለኝ ጫኔና ከዶክተር ቴዎድሮስ... ውጭ ያሉት አብዛኞቹ አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካዳሚዎች ሆነዋል። አብዛኞቹ አመራሮችም የአማራን የሕልውና ጥያቄ በቤት እና መኪና ቀይረው ትግላቸውን አጠናቅቀዋል።

ስለሆነም ፋኖዎች ቢገደሉ፣ አማራዎች ቢፈናቀሉ፣ አሸባሪዎች ዳግም ወረራ ቢፈጽሙ፣ የአማራ ሕዝብ ባልፈጸመው ጥቃት ቢወገዝ.... መግለጫ እንኳን ለማውጣት ልምምጥ የሚያስፈልጋቸው ዳተኞች ሆነዋል።

እናም የአማራን የመኖር ያለመኖር ጥያቄ በፍርፋሪ የሸጡ የአብን አመራሮችን አስወግዶ በአዲስ አመራር በመተካት ፓርቲውን ማስተካከል ካልተቻለ ከዚህ በኋላ አብን ከተባለ ጥቅመኛ ፓርቲ የሚጠበቅ ድል ቀርቶ ቅንጣት ታክል ትግል አይኖርም።

አሳዬ ደርቤ

24/10/2021

"ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው!"

የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መልዕክት
➖➖➖➖

አሸባሪውንና ወራሪውን ኃይል ባህሪን ጠንቅቀን እናውቀዋለን። በደረሰበት ቦታ ሁሉ እስኪያልፍ ድረስ "ከእናንተ ጋር ችግር የለብኝም" ቢልም ሕዝብን ከማጥፋት ወደኋላ አይልም። ሕዝባችን ላይ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያደረሰውን ግፍና በደል እናውቀዋለን። አሁኑ በተያያዘው የጦር ወረራው በየደረሰበት ቦታ ገና እግሩን ከመትከሉ ነው ሕዝብ እየጨፈጨፈ ያለው። በዚህ ወቅት ወሎ ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ ለጦር ወረራ ዘምቶብናል። ለዚህ መድሃኒቱ እሱ በጀመረው መንገድ መዝመት ነው። ይህ ወረሪ ኃይል እየፈጸመ ያለውን መጠነ ሰፊ ወረራ መላ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አቅማቸው ሊመክቱት ይገባል።

ጀግናው የወሎ ሕዝብ ከቦታው ባለመልቀቅና የጠላትን የእንቅስቃሴ መረጃዎች ለወገን ጦር በመስጠት፣ ምቹ ሁኔታ ሲያገኝ ጠላትን በጋራ በማጥቃት ሊያግዝ ይገባል። ‹ይህ ወራሪ ኃይል መጣ› ብሎ መሸሸ የለበትም። ራያ ላይ የሸሸውን ወልዲያ ላይ ዝም አይለውም። ወልዲያ ላይ የሸሸውን ደሴ የመግባት ዕድል ቢያገኝ ዝም አይለውም። ስለሆነም ሕዝባችን አንድ ልብ መካሪ፤ አንድ ቃል ነጋሪ ሁኖ እንዲመክት ወገናዊ ጥሪየን አቅርባለሁ፡፡

በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የምትኖሩ የዐማራ ልጆች እንዲሁም መላ ኢትዮጵያውያን በወሎ ግንባር ያሰፈሰፈውን ወራሪ ኃይል በመመከት ወሎ ታሪካዊ የፍፃሜው ቦታ እንዲሆን ለማድረግ ርብርብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ንቅናቄ መሀል ሀገር ያለውን ኢትዮጵያዊ ኃይል ያካተተ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ አሁን የሚጠበቀው ከሌላ ቦታ ወደ ወሎ መዝመት አንጅ ከወሎ መውጣት አይደለም፡፡

መላው የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቱ የሆነው ትህነግ ወሎ ላይ የከፈተውን የጦር ወረራ በማክሸፍ ህልውናውን ማፅናት አለበት፡፡

መዝመት የሚችል ይዝመት። ገንዘብ ያለው በገንዘብ ያግዝ። መኪና ያለው መኪናውን ለዘመቻ ያውል። ሁሉንም አቅም አሟጦ በመጠቀም ወራሪው ኃይል ወሎ ላይ ግብአተ መሬቱ ሊፈፀም ይገባል፡፡

አሸባሪውና ወራሪው ኃይል የፈፀመው ወረራ የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም። በመላ ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመ ነው። በዜጎቿና በክብሯ አልፎም በሉአላዊነቷ ላይ የተቃጣ በመሆኑ ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው፡፡ ወራሪው ኃይል ከሁሉም አካባቢ ተጠራርቶ ሲወረን እኛም ከመላ ኢትዮጵያ ተጠራርተን ወደ ወሎ መዝመት አለብን። በተባበረ ክንድ ወራሪውን ኃይል እስካልደመሰሰን ድረስ እንደ አማራም፣ እንደ ኢትዮጵያም ሰላም ማግኘት አንችልም።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Telephone

Website

Address


Addis Ababa