Muler

Muler

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Muler, Computer repair service, A. A, Addis Ababa.

25/05/2022

የራንሰምዌር ጥቃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ማሻቀቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 17/2014: በራንሰምዌር(ransomware) አመካኝነት የሚደርሱ የመረጃ ጥቃቶች በከፍተኛ መጠን ያሻቀበ ሲሆን ቁጥሩ ባልፉት አምስት አመታት ከደረሱት አጠቃላይ ጥቃቶች በ13 በመቶ እንደሚልቅ የቬራይዘን (Verizon) ጥናት አመልክቷል።

ቬራይዘን ይፋ ባደረገዉ የ2022 የዲታ ብሪች ኢንቨስቲጌሽን ሪፖርት (Data Breach Investigations Report) መሰረት ይህ የራንሰምዌር ጥቃት መጠን በሳይበር ደህንነት ታሪክ ውስጥ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን መለየቱን ጠቁሟል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የራንሰምዌር ጥቃት መጨመር ባሻገር ከሰዉ ልጆች አጠቃቀም ስህተት ጋር በተያያዘ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶች 82 በመቶ እንደሚሽፍን የገለጸዉ ቬራይዘን ከስህተቶቹ መካከልም የሶሻል ምህንድስና ጥቃት፣ የአጠቃቀም ስህተቶች እና ያልተገባ የምህዳሩ አጠቃቀም እንደሚገኙበት አሳዉቋል።

የራንሰምዌር ጥቃት በሳይበር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ተጎጂዎችን ፋይሎቻቸውን እና ማህደሮችን እንዳይደርሱ(access) የሚከለክል የአጥፊ ሶፍትዌር አይነት ነው። ራንሰምዌር ጥቃት የተጎጂዎችን ሰነዶች፣ ፎቶዎች፣ የመረጃ ቋቶችን እና ሌሎች ፋይሎችን የሚመሰጥር ሲሆን ተጎጅዎች የተመሰጠረባቸዉን ወሳኝ መረጃዎችን መልሰዉ ለማግኘት የራንሰም(ransom) ክፍያ የሚጠይቅ ነዉ።

ተቋማትን በተለየ ሁኔታ የሚያሳስበው አስደንጋጭ የራንሰምዌር ጥሰቶች መጨመር ነው ያለዉ ሪፖርቱ የሳይበር ወንጀለኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተራቀቁ የማልዌር ዓይነቶችን የመጠቀም ሁኔታ በይበልጥ በህገወጥ መንገድ የግላዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ እና ገቢ ለማግኘት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለማሳካት ራንሰምዌር ጥቃት ውጤታማ መሆኑ ተጠቁሟል።

ወደፊትም ከሰው ልጆች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የመረጃ ጥሰቶች ዋነኛ መንስኤ ሆነዉ እንደሚቀጥሉ የገለጸዉ ሪፖርቱ የተሰረቁ ማስረጃዎችን መጠቀምም ሆነ መረጃ ማጥመድ አልያም የሰዉ ልጆች በእነዚህ ጥቃቶች መከሰት የራሳቸዉ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸዉ ተገልጿል።

የተደራጁ ወንጀለኞች የሳይበር ደህንነት አለምን እንደተቆጣጠሩ የገለጸዉ ሪፖርቱ በአለም ላይ ከሚከሰቱ አምስት የመረጃ ጥሰቶች ውስጥ ቢያንስ አራቱ ከተደራጁ ወንጀሎች ጋር ይያያዛሉ ብሏል።

ከዚህ ባሻገር ከተቋም ዉጪ ያሉ የሳይበር ጥቃት ስጋቶች ውስጥ ካሉ ስጋቶች አንጻር ሲታይ የዉጭ ስጋቶች ተቋማትን የመጉዳት ዕድላቸው በአራት እጥፍ ይበልጣል ሲል በሪፖርቱ ተገልጿል።

የጂኦ-ፖለቲካ ዉጥረቶች የሳይበር ጥቃት አይነቶችን ረቂቅነት እንደጨመረዉ የገለጸዉ የቬራይዘን ሪፖርት በመንግስታት ድጋፍ ስለሚደረግባቸዉ የሳይበር ጥቃቶች ሃገራት ያላቸዉ የግንዛቤ ደረጃም በተጨባጭ ማደጉን ጠቅሷል።

በመሆኑም ወደ ዲጂታሉ አለም የምናደርገዉ ግስጋሴ በጨመረ ቁጥር ዉጤታማ የሆነ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች፣ ጠንካራ የደህንነት ማእቀፍ እና ስለጉዳዩ የሚሰጥ ተከታታይነት ያለዉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተቋማትን ደህንነታቸዉን አስጠብቀዉ እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ተብሏል።

ክላውድ ኮምፒውቲንግ ምንድነው? /What is cloud computing? / 27/04/2022

ክላውድ ኮምፒውቲንግ ምንድነው? /What is cloud computing? / # Cyberegna Ethiopia Network Security Agency Security Ethiopia #የክላውድ ኮምፒውቲንግ ምንነት እንዲሁም ለሳይበር ጥቃት ያለው ተጋላጭነት እና የመከላከያ መንገዶ...

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


A. A
Addis Ababa