A.a. Smkc YOUTH
ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥2
03/08/2021
ተወዳጅ እና ትሁት ከሆነው ከወንድማችን ዶክተር Abraham Tekle Mariam ጋር ባለፈው ቅዳሜ አስደናቂ ጊዜን አሳልፈናል። ባሣለፍነው ጊዜ የህይወት ተሞክሮውን ሲያካፍለን ነበር እናም ብዙ ተምረናል፡፡ ፕሮግራማችን በወንድማችን አሸናፊ አማካኝነት በፀሎት ጀምረናል እናም ከዚያ በመቀጠል ከወንድማችን አቤኔዘር ጋር በዝማሬ ጌታን አምልከናል፡፡ እግዚአብሄር ሁለቱንም አብዝቶ ይባርክ! እጅግ በጣም ጥሩ ጊዜ ነበር፡፡ከዚያ ወደ ህይወት ተሞከሮ ማካፈል ገባን፡፡ ዶክተር አብርሽ ሰባኪ ከመሆኑ በፊት በትናንሽ ቡድኖች ያገለገል አና ይሰብክ ነበር ፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፀሎት ፣በአምልኮ እና በሌሎች የተለያዩ አገልግሎት ውስጥ ሲያገለግል እና ሲሳተፍ ቆይቶአል፡፡ እናም ይህ ነገር ጥሪውን ለመለየት ረድቶታል፡፡ ከማንኛውም ነገር በተሻለ ሁኔታ ቃሉን ለመስበክ እና ለማጥናት ይፈልግ ነበር ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለጓደኞቹ ያካፍል ነበር፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ያሣልፍም ነበር፡፡ አብርሽ ራሱ በሠራት ትንሿ ክፍሉ ውስጥ ከጌታ ጋር ብዙ ጊዜ ያሳልፍ ነበር፡፡ የእግዚአብሄር ድምፅ ለመስማትም የተለማመደው በዚህች ክፍሉ ውስጥነበር
አብርሽም በክርስትና ህይወቱ እንዲያድግ፣ በቤተክርስቲያንም ሆነ ከውጭ ትልቅ ተፅዕኖ የሳደሩበት÷ አርአያዎችና እና አማከሪዎቹን ነበሩት፡፡ለታላላቅ የህይወት ውሳኔዎቹ እና ለፈታኝ ችግሮቹ ምክርን ከብዙ ሰዎች ያገኝ ነበር ብዙ ሰዎችም ነበሩት አሁንም አሉት፡፡ ስለቤተሰቡ ፣ ጋብቻውን ፣ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎቹን ፣ ተግዳሮቶቹን እና እንዴት ወደ ትምህርት ቤት እንደገባ አካፍሎናል፡፡አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን ትቶልናል። (ወጣት ቡድን) በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ፤በተለይ እኛ ለወጣቶች ጌታን ማገልገል ትልቅ ዕድል መሆኑንና እንድናገለግል መክሮናል ብሎአል፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ!! ዶክተር አብርሽን በማግኘታችን በእውነት ተባርከናል፡፡ የቅዳሜው ትምህርት በዋጋ የማይታመን ነበር፡፡ ሁላችሁንም እናመሰግናለን፡፡ ዛሬ እኛን ስለተቀላቀላችሁ፤ መንፈሳዊ ግንኙነታቹን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር እንድታጠነከሩ አሰናሣስባለን። ከሁለት ሳምንት በኃላ ቋሚ በኘሮግራማችን ይጀመራል። ሁላቹንም ለማየት በጉጉትእንጠብቃለን፡፡
ለማንኛውም ምክርና ፀሎት የወጣቶች አስተባባሪያችንን፡
እህት ኤልሻዳይ ቢወጣን ያነጋግሩ
0986987554
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa