Guna Media Service
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Guna Media Service, Media/News Company, Addis Ababa.
15/12/2021
የኢትዮጵያ ጦር በሸዋና ደቡብ ወሎ ግንባር በህወሃት ጦር ላይ ስለተቀናጀው ድል ለወደፊቱ ዘለግ አድርጌ እጽፋለሁ። ለአሁኑ ግን በጦርነት የተገኘውን ድል በፖለቲካ ውዝግብ የተነሳ እንዳናጣው ስለሰጋሁ፣ በአንድ ቁልፍ ጉዳይ ላይ ሃሳቤን ላካፍላችሁ ወደድኩ።
በቅርቡ ለተገኘው የጦር ሜዳ ላይ ድል አንደኛው አወንታዊ ምክንያት የአመራር ወጥነት ( unity of command) መፈጠሩ ነው። አጠቃላይ የጦርነቱ አካሄድ በአንድ ሰው የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪነት እንዲካሄድ መደረጉ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠሩ ይችሉ የነበሩ ውዝግቦችንና መጓተቶችንና አስቀርቷል። ጦርነት በተፈጥሮው ፈጣን ውሳኔን የሚጠይቅ መስክ በመሆኑ፣ የጠ/ሚኒስትሩ በጦር ሜዳው ላይ መገኘት፣ ከፈጠረው የስሜት መነቃቃት በተጨማሪ፣ ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲሰጡና እንዲተገብሩ እረድቷል። ከጠ/ሚኒስትሩ በታች የሚገኙ የጦር አመራሮች፣ ብናጠፋ በፖለቲካ አመራሩ እንወገዛለን ብለው ሳይሰጉ፣ በቀጥታ የሚሰጣቸውን ትዕዛዝ ያለ ስጋት እንዲያስፈጽሙ እገዛ አድርጎላቸዋል።
የአመራር ማዕከላዊነቱ መከላከያውን ብቻ ሳይሆን፣ የክልል ልዩ ሃይሎችን፣ ሚሊሺያውንና ፋኖውን ያካተተ በመሆኑ፣ እነዚህን ሁሉ ሃይሎች በአንድ መስመር አሰልፎ በማዋጋት ታላቅ የሚባል ሃይል መፍጠር ተችሏል። እነዚህ ሃይሎች በተበታተነ አመራር ቢንቀሳቀሱ ኑሮ፣ እስካሁን የተገኘው ድል ባልተመዘገበም ነበር። (በደብረታቦር ግንባር ተፈጥሮ በነበረው የአመራር ክፍተት፣ ህወሃት ጊዜያዊ ድል እንድታገኝ እረድቷት እንደነበር አንረሳውም። )
የአመራር ወጥነት እንዳይኖር ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ፣ በአጠቃላይ በግንባር በተሰለፈው ሰራዊት መካከል የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚፈጥሩት ችግር ነው። የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚጨነቁት ራሳቸውን ወደፊት ስለማምጣት ወይም ሁሉም ነገር በራሳቸው ዛቢያ እንዲሽከረከርላቸው በመሆኑ፣ በሰራዊቱ ውስጥ መከፋፈል እንዲፈጠርና የአመራር አንድነቱም እንዲፈርስ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ ጦርነት ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ፣ በግንባር የተሰለፉት ሃይሎች የፈጠሩትን አንድ ወጥ የእዝ ሰንሰለት የሚጎዳ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ መንግስት በፍጠነት ማስቆም አለበት። ሊታገሰውም አይገባም።
ይህ ጊዜ እርስ በርስ የምንናቆርበት ሳይሆን፣ በአንድነት ቆመን የመጣብንን አደጋ በመቀልበስ የኢትዮጵያን የወደፊት ታሪክ የምንጽፍበት ነው።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል‼️
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡
በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
Woldia loading
ላሊበላ በወገን እጅ!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Culinary Team
Attire
Website
Address
Addis Ababa