ZOBEL TIMES

ZOBEL TIMES

Share

ፈጣን ወቅታዊ የተጣሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መረጃዎችን ለተከታዮቻችን እናደርሳለን።
ቤተሰብ ስለሆኑን እናመሰግናለን።�ኢትዮጵያ ትቅደም!!!�

Photos from ZOBEL TIMES's post 28/08/2023

ይድነቃቸው ከበደ ታስሮ ቀረ። ኤርሚያስ መኩሪያ ታስሮ ቀረ። በላይ በቀለ ታስሮ ቀረ። ሌላም ብዙ ሰው ታስሮ ቀረ። ከትናንት የከፋ ጊዜ ላይ መሆናችን የሚታወቀው፣ በፊት ሰው ሲታሰር መደንገጥ፣ "ፍቷቸው" ማለት ነበረ።

አሁን ሁሉንም ዓይነት ግፍ ተለማምደነው ለብዙ ነገር ግድ የሌለው ይበዛል። ሰው ሲሞት፣ ቁጥሩ እና አገዳደሉም የማይደንቀን ጊዜ ላይ ደርሰናል። ደጅ እንደተሰጣ እቃ ሰው ጠፋ ሲባል ሁሉ መደነቅ እየቀነሰ፣ ሰብዓዊነት ቀስ በቀስ እየቀዘቀዘ መጣ።

በርግጥ መከራ እና ግፍ አዲስ አይደለም። ነገር ግን የአሁኑን የከፋ የሚያደርገው፣ ሁሉንም ከስር ከስር እየጋቱ ያለማምዱናል። ያደነዝዙናል። :-/

Yohanes Molla - ዮሐንስ ሞላ

Photos from ZOBEL TIMES's post 02/08/2023

ጎጃም ከባህርዳር ጀምሮ ወደ ደጀን የሚዎስደውን አውራ መንገድ ሁሉም ቦታዎች ላይ ጠርቅማለች።

ጎጃም ማለትም ደንበጫ፣ቡሬ፣የጁቤ፣ፈረስ ቤት፣ደጋ ዳሞት፣ፍኖተ ሰላም፣አማኑኤል፣ጅጋ፣የጨረቃ፣መራዊ፣ማርቆርስ በአገዛዙ የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት ሙሉ ጦርነት ውስጥ ናቸው።

ይሁን እንጂ "የገባው አይወጣም" ሲሉ በፋፁም ኩራት ገልፀውልናል።

የገባው የስርዓቱ ወታደር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል።

ጎንደር በዋናነት ደ/ታቦር ጦርነት ውስጥ ናት።

አማራው ላይመለስ ተነስቷል።

Wogderes Tenaw ወግደረስ ጤናው

31/07/2023

ዛሬ 8 ሰአት ፍርድቤት ቀርበው የነበሩት ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ የችሎት ውሎ ፦

ለመከላከያ ምስክርነት ቀርቦ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድቤቱ ለመከላከል ደብዳቤ ፅፈን ከመከላከያና ከሀገር ደህንነት አኳያ በምን ጉዳይ ይመስክር የሚለውን ወስነን በቀጣይ ቀጠሮ ትቀርባለህ ተብሎ ምስክርነትቱ አልተደመጠም።

የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 4 ጊዜ ቢጠሩም ባለመቅረባቸው ተጠያቂነት የሚያስከትል ስለሆነ በቀጣዩ ቀጠሮ የአዲስአበባ ሀገረስብከት ስራአስኪያጅ እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጥቷል።

ከዚህ በፊት የመከላከያ ምስክር ሆነው ቃል የሰጡት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል ቃል በሰጡበት ወቅት የተቀዳው ቅጂ በደንብ ስለማይሰማ በቀጣዩ ቀጠሮ ቀረበው ድጋሚ ምስክርነትቸው እንዲደመጥ

ቀጣዩ ቀጠሮ ለሚቀጥለው አመት ጥቅምት 19 ፤ 20 ፤21 እንዲሆን በማለት የዛሬው ውሎ ተጠናቋል።

የታሪክ ምሁሩና ጋዜጠኛው ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ የታሰሩት አምና ግንቦት/2014 ዓ.ም ነበር። ከአንድ አመት በላይ ምስክር እንኳን አዳምጠው አልጨረሱም። በጋሽ ታዲዎስ እስር ላይ ሽመልስ አብዲሳ "እዛው ይበሰብሳታል እንጂ መቼም አይወጣም" ማለቱ ይታወሳል።

Via Kura Gebre

30/07/2023

ነፃ በወጡ አካባቢዎች እንዲህ እየሆነ ነው። የዐማራ ልዩ ኃይል ከነ ሙሉ ትጥቁ፣ እውቀቱ፣ ወኔውና ጀብዱው ከጀግናው በተፈጥሮ ነፍጠኛ ከሆነው አራሽ፣ ቀዳሽ፣ ተኳሽ ፋኖ ጋር መቀላቀሉ ትግሉን ወደፊት እያስፈነጠረው ነው።

የገበሬው ማዳበሪያና ምርጥ ዘር መከልከል ለፋኖ ጥሩ ከለላ ነው የሆነው።ስንቅ ከመስጠት አልፎ መንገድ መምራት፣ጠላት ሲመጣ በጋራ ማጥቃት፣ መመከትም ተጀምሯል።

"የጥንት የደርግ ወታደሮች፣በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ተሳታፊ የነበሩ ወታደሮች፣አሁን ካለው መከላከያ፣ፌደራል ፖሊስ እና ሪፐብሊካን ጋ ር የኮበለሉ ዐማሮች ፋኖን መቀላቀል የፋኖን አደረጃጀት አሳድጎታል።

ሥልጠና ከገጠር ወጥቶ ከተማ አስፓልት ላይ የሚሰጠው ከተሞ ችን ከብአዴን እና ከዐቢይ፣ብራኑ ጁላ ጦር ነፃ ስላወጡ ነው። አሁ ን ፋኖ ነፃ ባወጣቸው ከተሞች ላይ ወጣት ሆኖ አረቄ መገሸር፣ጠ ላ ሲያንቃርር መዋል፣ጫት እና ሺሻ ሲጠቀም፣ሴት ሲያሳድድ መዋ ል ክልክል እየሆነ ነው።ወጣት ያውም ጤነኛ ከሆነ ሳይወድ በግ ዱ ትግሉን ይቀላቀላታል።ማንም ሞቶ ይሄን ጀዝባ የሃገር ሸክም ነፃ አያወጣም።

አሁን ትልቁ እሾክ የዐማራ ጎታች ወጣት ፀረ ዐማራ ዲቃላ ብአዴን ነት ያለው ነፃ ባልወጡ የዐማራ ከተሞች ላይ ብቻ ነው።በተለይ ባ ሕርዳር ቁማር ቤቱ እንደሞላ ነው።ጃምቦ ቤቱ እና ቤቴንግ ጢቅ እ ንዳለ ነው።የባህርዳር ከነማ እና የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊ ማኅበራት ውስጥ ያሉ ጎታቾች የትየለሌ ናቸው። በማርቆስ ቢንጎ ቤት፣በጎንደር ድራፍት ቤት፣ በደሴ ጫት ቤት፣ በደብረ ብርሃን አረቄ ቤት የተከማቸውን ድንዙዝ የዐማራ ወጣት እንዲህ ልክ የሚያገባ ው ኃይል ሊመጣ ግድ ይላል።በተለይ የባህርዳር ቁማር ቤት ሊታ ሰብበት ይገባል።

• ድል ለዐማራ ፋኖ✊✊✊
ዘመድኩን በቀለ

Photos from ZOBEL TIMES's post 29/07/2023

ፋኖ እንደ አቦ ሸማኔ እየተወረወረ ከብልጽግና የጸዳ ቀጠና እየፈጠረ ነው።

ስር የምትገኘው የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ #መኮይ ከተማ በጀግናው የህዝብ ልጅ #ፋኖ ቁጥጥር ስር ገብታለች።💪💪💪💪

29/07/2023

አስከተማ የአማራ ፋኖ አቀባበል ተደርጎለታል።

በዛሬው ዕለት አስከተማ እና መቄትን ሙሉ በሙሉ በአማራ ፋኖ ላስታ አውራጃ አሳምነው ብርጌድ ተቆጣጥሯል።

ምስራቅ አማራ ቀጠና በአንድ ዕዝ ይመራል።

ብአዴን እስከዘላለሙ ይቀበራል።

ድል ለአማራ ሕዝብ‼️

Via = Mulugeta Anberber

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa