BBE-News
ቻናላችን፦ ትኩስ ዜናዎችን፣ ስፖርትና በርካታ መረጃዎችን በ?
29/04/2021
በአማራ ክልል 2 ሺህ 705 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው፡፡
በልዩ ልዩ ወንጀሎች እስራት ተፈርዶባቸው በአማራ ክልል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙና የይቅርታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲደረግ የክልሉ ይቅርታ ቦርድ ወስኗል፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው 56 ሴት እና 2 ሺህ 649 በድምሩ 2 ሺህ 705 ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ በይቅርታ መለቀቃቸውን የጠቅላይ አቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አለምሸት ምሕረቴ በተለይ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
አቶ አለምሸት እንዳሉት በተለያዩ ወንጀሎች እስራት ተፈርዶባቸው አንድ ሦስተኛ የእስራት ጊዜያቸውን የጨረሱ እና በማረሚያ ቤት የሥነ ምግባር ለውጥ ማሳየታቸው የተረጋገጠላቸው ታራሚዎች ናቸው በይቅርታ እንዲለቀቁ የተወሰነው፡፡ ሕጻን ይዘው የታሰሩ ሴቶችና ነብሰ ጡር እስረኞች ከሆኑ ደግሞ ከተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ አንድ አምስተኛውን ካጠናቀቁ የይቅርታው ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
የዕድሜ ልክ እስራት ከተፈረደባቸው መካከል 60 ዓመት የሞላቸው ወንዶች 12 ዓመታት በእስራት ከቆዩ፣ ሴቶች ከሆኑ ደግሞ 55 ዓመት ሆኗቸው 10 ዓመታት ከታሠሩ የይቅርታው ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ይሁን እንጂ ይቅርታው ከ15 ዓመት በታች የሆነች ልጃገረድ አስገድዶ የደፈረ፣ ፍጻሜ ባገኘ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ፍጻሜ ባገኘ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም በሙስና ወንጀል 10 ዓመትና ከዚያ በላይ እስራት የተፈረደባቸውን ታራሚዎች አያካትትም ነው ያሉት፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ መውጣት መጀመራቸውንም የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አስታውቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
👇
👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን
👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።
👉 .
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa