Adem Mohammed
ሀገር በትብብር ይገነባል!! የድርሻችን እንወጣ!!
07/01/2026
የበለፀገችና ተደማጭ ሀገር ለነገው ትውልድ‼️
____________________________
ሀገር በትብብር ይገነባል‼️ የመተባበር አስኳል ደግሞ የወንድማማችነትንና የእህትማማችነትን እሳቤን በተግባር መግለጥ መቻል ነው‼️ አንዱ ለሌላው ማሰብ፣ ለእኔ ብቻ ከሚሉት ነጠላ የሆነ ትርክት ከማዜም በመወጣት በወል ጉዳዮቻችን ላይ አተኩረን አንድነትን ማጎልበት‼️ እርስ በእርሳችን መተዛዘን፣በሰዎች መካከል መከባበርና መተሳሰብን አብዝተን መሻትን የህይወታችን መርህ ማድረግ ይገባናል‼️
ለመጪው ትውልድ የበለፀገችና ተደማጭ ሀገር ለመገንባት የምክክር፣ የውይይትና የተግባቦት ባህላችን ዘመኑን የዋጀ መሆን ይገባዋል‼️ ከምንም በላይ ሰላማችን እንዲፀና ፍቅርን እንስበክ፣ መዋደድን በተግባር መኖር እንጀምር‼️ሀሳባችን ተግባራዊ ምላሽ የሚሰጥ ይሁን‼️እያንዳንዱ ድርጊታችን ነገ የሚሰራ፣ትውልድን የሚያንፅ፣ለትውልድ የሚተርፍ ምንዳን የሚያወርስ ይሁን‼️
05/01/2026
01/11/2025
መደመር መደፍጠጥን አይቀበልም!!
መደመር መደፍጠጥን አይቀበልም፡፡ ሕዝብን በአንድ የሐሳብ ቅርጫት ውስጥ መክተትን ፈጽሞ አይቀበልም፡፡ በብዙ ነገር ወደ ኃላ ስለቀረን ብዙ ዓይነት ሐሳብ ያስፈልገናል ብሎ ያምናል፡፡ በተመሳሳይ ጫፍ የረገጠና የሀገሪቱን ህልውና የሚፈታተን ማንኛውም የመከፋፈል አዝማሚያ በጠንካራ የሕግ የበላይነትና በተቋማት ብርታት ወደ መሥመር እንዲገባ መደረግ አለበት ይላል፡፡ ከላይ የጠቀስነውን የህልውና ፍላጎት የምናሳካው ሥርዓትን በሚገባ የሚያውቅ ሕዝብና ሀገር ስንፈጥር ፤ ይህም ሥርዓት የሚያውቅ ሕዝብ የበኩሉን አስተዋጽፆ እንዲያበረከት እንደየአመጣጡ ስናቅፈው ነው፡፡
የመደመር መንግሥት ገጽ 1፣ 2018 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa