Adis Tube
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Adis Tube, Media/News Company, Addis Ababa.
10/03/2023
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የተቋማዊ ሪፎርም የዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ዘመናዊ ሕንፃ እና ሌሎች የ90 ቀን ፕሮጀክቶች ዛሬ ይመረቃሉ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💚💛❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፍ እና ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ የተቋማዊ ሪፎርም የዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ዘመናዊ ሕንፃ እና ሌሎች የ90 ቀን ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ዛሬ ይመረቃሉ።
ከሚመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የለሚ ኩራ የቴክኖሎጂ ማዕከል ህንጻ ፥ G+4 የመኖሪያ ቤቶች፣ ሞዴል ጤና ጣቢያዎች፣የውሃና የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና መሰል ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡
በ 14-05-2013 ዓ.ም ለምረቃ ዝግጁ የነበረው የክፍለከተማ አስተዳደሩ ሕንፃ እና በሕንፃው ውስጥ ዝርጋታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ በሆኑ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ በተከሰተው እሳት ጉዳት ደርሶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ በእሳት አደጋው ጉዳት ደርሶበት የነበረው ሕንፃ እና የቴክኖሎጂ ልማት ለሕዝብ በተገባው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የመልሶ ግንባታ ፥ጥገናና የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ዝርጋታው በአፋጣኝ እንዲስተካከል ተደርጎ ለሕዝብ አገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት የተገነቡ ሁሉም ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግስትና ከባለሃብቱ በተገኘ የበጀት ድጋፍ የተገነቡ ናቸው።
08/03/2023
ኢትዮዽያዊነት በተግባር የታየበትና: በዝቅታችን ወቅት ከፍታን ያየንበት ተግባር ነበር።
ለኮሜዲያን እሸቱ: ለደጉ ቢንያም እና ተሳታፊውን በሙሉ አለማመስገን ንፉግነት ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
28/02/2023
"ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ !!"
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት መልዕክት ፦
"ለቦረና ህዝብ ያሰባሰብነውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክበናል::
በተለያዩ ግዜያት ከህዝብ ጎን በመቆም የሚታወቁ የከተማችን ባለሃብቶች ፣ ያስተባበራችሁ አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታነት እና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ::
በቀጣይም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት እየሰራቸው ያለውን ስራዎች ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚደግፍ ለማሳወቅ እወዳለሁ።"
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa