Info_net in Addis

Info_net in Addis

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Info_net in Addis, News & Media Website, Ethiopian, Addis Ababa.

23/02/2023

VPN ስንጠቀም ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች

በኢትዮጵያ በተለይም የተወሰኑ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ የቪፒኤን ፍላጎት በ1430 በመቶ ጨምሯል።

በአንድ ሀገር ያለ ኔትወርክ በብዙ ምክንያቶች መደበኛ የኔትወርክ ገደብ ሲጣል ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትወርክ ወይም ቪፒኤን በሚል የሚጠሩ መተግበሪያዎችን መጠቀም የተለመደ ነው።

በኢትዮጵያም መደበኛው የኔትውርክ አገልግሎት ገደብ ሲጣልበት የተለያዩ የቪፒኤን መተግበሪያዎችን በማውረድ መጠቀም ተለምዷል።

በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያ በተለይም የተወሰኑ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች በቪፒኤን በመጠቀም ላይ ናቸው።

የቪፒኤን መተበሪያዎች ባጭሩ አንድ ሀገር ሆነን በሌላ ሀገር ኔትወርክ መጠቀም ማለት ሲሆን በተለይም የምንጠቀምበትን ሰርቨር፣ የምንጠቀማቸውን ዌብሳይቶች፣ የተጠቀምናቸወን ፋይሎች እና ሌሎች መረጃዎችን ሰዎች አልያም ስለ እኛ ማወቅ የሚፈልጉ አካላት መረጃውን ማግኘት እንዳይችሉ ያደርጋሉ።

ይሁንና ሁሉም አይነት የቪፒኤን መተግበሪያዎች አስተማማኝ ባለመሆናቸው የተወሰኑት በቀላሉ ለመረጃ መንታፊዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

በአውስትራሊያ በተደረገ ጥናት 67 በመቶ የዓለማችን ቪፒኤን መተግበሪያዎች ቢያንስ አንድ መረጃ መመንተፊያ ቫይረስ ያላቸው ሲሆን ከተጠቃሚዎች የወሰዷቸውን መረጃዎች ለሶስተኛ ወገኖች አሳልፈው ይሸጣሉ።

የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከተጠቃሚዎች መረጃዎችን በመግዛት የማስታወቂያ ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን የቪፒኤን ተጠቃሚዎች ዋነኛ ኢላማ እንደሚሆኑም ተገልጿል።

በተለይም ነጻ የቪፒኤን መተግበሪያዎች ለመረጃ መንታፊዎች የተጋለጡ ሲሆኑ 65 በመቶ ነጻ የቪፒኤን መተግበሪያዎች መረጃዎችን ከተጠቃሚዎች ወስደው ለቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ይሸጣሉ።

ይሁንና በክፍያ የሚገኙ የቪፒኤን መተግበሪያዎች ከመረጃ መንታፊዎች የተጠበቁ ሲሆን ደንበኞች ለመረጃዎቻቸው የሚጠነቀቁ ከሆነ የክፍያ ቪፒኤን መተግበሪያዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል።

በአጠቃላይ ቪፒኤን መተግበሪያዎችን መጠቀም ለመረጃ ምንተፋ፣ ለቫይረስ ጥቃት፣ ለከፍተኛ የኔትወርክ ክፍያ፣ ካለፍላጎት እና ለአሰልቺ ማስታወቂያዎች እና ለኔትወርክ መዘግየት ሊያጋልጥ ይችላል ተብሏል።
ምንጭ:-አል አይን
ለበለጠ መረጃ ➧https://t.me/fastnewsfromreal

23/02/2023

የ6 ዓመቷን ህጻን አስገድዶ የደፈረው የ30 አመት ወጣት በጽኑ እስራት ተቀጣ።

ነዋሪነቱ በምንጃር ሸንኮራ በአረርቲ 02 ቀበሌ ያደረገው ወጣት ኃ/ማርያም ሳህለ የ30 ዓመት ወጣት ባለትዳር ሲሆን ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም የተለመደ የዕለት ስራውን ሲያከናውን ቆይቶ ቁርስ ለመቅመስ ወደ ቤቱ ያመራው በግምት ከጥዋቱ 3፡00 በሚሆንበት ጊዜ ነበር የ6 ዓመቷ ህጻን ከእኩዮቿ ጋር የልጅነት ጨዋታ ለመጫዋት ከጎረቤት ግቢ ተገኘች፡፡

ከላይ ስሙ የተጠቀሰው ግለሰብ ታድያ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 627(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር 02ቀበሌ ልዩ ስሙ አይራራ አምባ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ አጋጣሚውን በመጠቀም ህጻኗን ወደ ቤቱ ይዞ ከገባ በኋላ ቆየት ያለውን ከሩቅ ዘመድ ልቆ የሚገኘውን ጉርብትና የወዳጅነት ባህል በመካድ በዕለታዊ ስሜት ተነሳስቶ ይህችን ገና ከእቅፍ ያልወጣችውን ህፃን አስገድዶ ደፈራት፤ የደረሰባትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው ህጻን ገላዋ የሰለለና የደከመ ድምጽ ማሰማት ሲጀምር ምንም እንዳልተፈጠረ ከቤቱ አስወጥቶ ትቷት ወደ ስራው ይሄዳል፡፡

ህጻኗ እያለቀሰች ወደ ቤቷ በመሄድ በደነገጠና በተኮላተፈ አንደበቷ ሁኔታውን ለቤተሰቦቿ ታስረዳለች ቤተሰቦቿም ጉዳዩን ለፖሊስ ያሳውቃሉ፡፡ በፖሊስ የወንጅል ክስ የተመሰረተበት ተከሳሹ የክሱ ቅጅ ደርሶት እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ በችሎት ቀርቦ ድርጊቱን መፈጸሙንና ጥፋተኛ መሆኑን ያመነ በመሆኑ ተከሳሹን ጥፋተኛ ብሎታል፡፡ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም በዋለው ችሎትም ተከሳሹን ያርማል መሰል አጥፊዎችንም ያስተምራል ያለውን በ14/አስራ አራት አመት/ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ምንጃር ወረዳ ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኮምንኬሽን
https://t.me/fastnewsfromreal

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Ethiopian
Addis Ababa