M.O.R East Addis Ababa Branch

M.O.R East Addis Ababa Branch

Share

Offcial page of Ministry Of Revenues Easter Addis Ababa Tax Payer Branch Office

17/05/2026

የሃዘን መግለጫ!

ግንቦት 08/2018 ዓ. ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ደሜ ከበደ ገጀአ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በሀገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ሕይወታቸው በማለፉ የገቢዎች ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!

አቶ ደሜ ከበደ በገቢው ዘርፍ ያላቸውን እውቀት እና የአመራር ክህሎት በመጠቀም ውጤታማ ስራ ከሰሩ አመራሮች መካከል ተጠቃሽ ነበሩ።

የአቶ ደሜ ከበደ የቀብር ስነ-ስርዓት እሁድ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

የወንድማችን ነፍስ በሰላም ትረፍ!

Photos from M.O.R East Addis Ababa Branch's post 03/05/2026

በቅ/ጽ/ቤታችን የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን ሰራተኞች በሆኑት በአቶ ተስፋዬ ግርማ፣ አቶ አዲሱ ኡርጌሳ እና አቶ ጌታሰው አሰፋ በሙያ ስነ-ምግባር፣ በአስቸኳይ ሙስና መከላከል እና የሀብት ምዝገባ ህጎች ጋር በተያያዘ ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም በቅ/ጽቤቱ የስብሰባ አዳራሽ አዲስ ቅ/ጽ/ቤቱን ለተቀላቀሉና ስልጠናውን ከዚህ ቀደም ላልወሰዱ አመራሮችና ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅ/ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾሞ የሥነ-ምግባር ስልጠናዎች የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ህዝብና መንግስት የጣለባቸውን ኃላፊነት በተገቢው ለመወጣት ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸው መልዕክት አስተላልፈዋለ፡፡

29/04/2026
M.O.R East Addis Ababa Branch 29/04/2026

ለ December ዘጊ የምስራቅ ግብር ከፋዮቻችን በሙሉ

M.O.R East Addis Ababa Branch 3 likes. "ለግብር ከፋዮች በሙሉ"

Photos from M.O.R East Addis Ababa Branch's post 29/04/2026

ከዲሴምበር ዘጊዎችና በታክስ ተገዢነት ክፍተት ካሉባቸው ግብር ከፋዮች ስልጠናና ውይይት ተካሄደ
……………
ምስራቅአ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/ ሚያዚያ 20/2018/
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰበብሰብ ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ፡፡» ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ
ስራ አስኪያጇ ይህን ያሉት በዛሬው እለት ከዲሴምበር ዘጊዎችና በታክስ ተገዢነት ክፍተት ካሉባቸው ግብር ከፋዮች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ሲሆን በታክስ ተገዢነት ክፍተት ያለባቸው ግብር ከፋዮች ወደተሻል የታከስ ስርዓት እንዲመጡ የሚያግዝ ስልጠና እና ውይይት ተካሂዷል ፡፡
ወ/ሮ ወርቃለም ግብር ከፋዩ ወደተሻል የታክስ ስርዓት መምጣት የሚችለው በታክስ ስርዓቱ ላይ የተቀመጡ ህጎችን በአግባቡ መወጣት ሲቻል ነው ብለዋል ፡፡ ይህ መድረክ የተዘጋጀው በገሪጎሪያን አቆጣጠር ገቢ ግብራቸውን ዲሴምበር 30 አሳውቀው ለሚከፍሉና አልፎ አልፎ የህግ ተገዢነት ክፍተት ከታየባቸው ግብር ከፋዮች ጋር ሲሆን በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ፣ የህግ ተገዢነት ምንነትና የኦዲት አሰራርን በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል ፡፡ ስልጠናው የተሰጠው በአቶ እሸቱ ኢራጎና በአቶ ሴናመል አብዲሳ ነው ፡፡
ስልጠውን ተከትሎ በስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ እና በታክስ ኦፕሬሽን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አየለ አማካኝነት ውይይት ተደርጓል ፡፡ በውይይቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከጊዜ ወደጊዜ የስልጠና እና የአገልግሎት አሰጣጡን እያሻሻለ መምጣቱ የተጠሩ ግብር ከፋዮች ገልጸው በግብር አከፋፈል ሂደቱ እየገጠሟቸው ያሉ ችግሮችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ይህን መነሻ በማድረግ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እንዲሁም በስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ እና በታክስ ኦፕሬሽን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አየለ ምላሽና ማብራሪያ ተስጥቷል ፡፡ በተጨማሪም እንደ ግብዓት የሚያገለግሉና በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች በእቅድ ይዘው እንደሚፈቱ ወ/ሮ ወርቃለም ተናግረዋል ፡፡
በመጨረሻም ግብር ከፋዮች ከተጠሩበት መድረክ አንጻር ወርሃዊ ታክሳቸውን እንዲከፍሉ እንዲሁም የዲሴምበር 2025 ዘጊዎች በቀሩት ጥቂት ቀናት ግብራቸውን አሳውቀው ክፍያ እንዲፈጽሙ ጥብቅ ማሳሰቢያ ወ/ሮ ወርቃለም የሰጡ ሲሆን የታክስ ለውጥን በጊዜ ማሳወቅ፣ማናቸውንም ግብር ሂደቶችን በቴክኖሎጅ መጠቀም ፣የኢ-ፔይመንት ክፍያ ስርዓትን መከተል ፣ ሀሰተኛ የግብይት ደረሰኞች መለየት ፣ ሁሉም ግብር ከፋዮች የኪውአር ኮድ ደረሰኝን መጠቀም እንደሚያስፈልግና በግብይት ወቅትም ጥንቃቄ ተገቢ እደሆነ ጠቅሰው ኦዲት የሚደረጉ ግብር ከፋዮችም ትክክለኛ መረጃ መስጠት እንደሚገባቸው አጽንዖት ሰጥተዋል ፡፡

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Lem Hotel, Megenagna
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00