Lemi Tesfa
Success
23/04/2026
ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሻገረ ኢኮኖሚ!!
የሀገራችን ኢኮኖሚ በብዙ መዋቅራዊ ፈተናዎች ተተብትቦ፣ በዕዳ ምርኮ ወደ ኋላ የመንሸራተት ጉዞ ላይ ነበር። ለውጡ ይሄንን የኋልዮሽ ጉዞ ገትቶታል፡፡ ቀጣይነት ያለውና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የብልፅግናችን ዋስትና ነው ብለን እናምናለን። ጥራትና ጤናማነት የጎደለው የኢኮኖሚ ዕድገትና እንቅስቃሴ፣ ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ የሚያስከትለው ሸክም እጅግ የከፋ መሆኑን እንረዳለን።
ከለውጡ በፊት የተመዘገበው ዕድገት በዘላቂ የፋይናንስ መሠረት ላይ አልተገነባም፡፡ በአግባቡ አልተመራም፡፡ በመሆኑም የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን ፈጥሮ ሀገርን ለከፍተኛ ዕዳ ጫና የዳረገ ነው። በአቅርቦት እና በፍላጎት፣ በመንግሥት ገቢና ወጪ፣ በቁጠባና በኢንቨስትመንት፣ በገቢና በውጭ ንግድ መካከል መዛባትን ፈጥሯል፡፡ ሀገራችንን በውጭ ምንዛሬ አጣብቂኝ፣ በዋጋ ንረት፣ በሥራ አጥነት እና በፍትሐዊ ተጠቃሚነት ችግር ውስጥ የከተተ ነው።
ሀገራችን በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት እና በመዋቅራዊ ስብራቶች ተይዛ ኖራለች፡፡ ይህቺን ሀገር ሀገራዊ ዐቅምን በማሰባሰብ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ችግርን በመጋፈጥ፣ ብርሃን ፈንጣቂ ውጤቶች እንዲመዘገቡ አድርገናል። የዘመናት መዋቅራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ሀገራችንን ወደ ብልፅግና ለማድረስ ቆራጥ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚን መዛባት ችግሮችን ለማረም የሚያስችሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ሆነዋል።
በዚህም የተነሣ የምርት አቅርቦትን፣ የመንግሥት ገቢን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን እና የውጭ ንግድን ለማሳደግ ተችሏል፡፡ እንዲሁም የዕዳ ጫናን፣ የዋጋ ንረትን እና የሥራ አጥነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ የማሻሻያ እርምጃዎች ተወስደዋል። የልማት አቅጣጫችንን ከአንድ ዘርፍ መሪነት እና ትኩረት ወደ ብዙኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መሠረቶች ቀይረናል፡፡ ውጤቶችንም በዚሁ አግባብ ለማስመዝገብ ችለናል።
30/03/2026
የተጀመረውን የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ በምርጫ ካርድዎ ያጽኑ!
የምርጫ ምልክታችን "የስንዴ ነዶ"
"የስንዴ ነዶ"፦
• የመደመር፣
• የምርታማነት፣
• ከተረጂነት የመላቀቅ፣
• የተምሳሌትነት፣
• የልዕልና፣
• የሉዓላዊነት፣
• የበረከትና የብልፅግና ምልክት ነው።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
23/03/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa