ETIO salam

ETIO salam

Share

salam.media ለሁሉም የሰው ልጅ ሠላም ይመኛል

13/03/2026

''አሰብ አፈጣጠሩም ለኤርትራ ሳይሆን ለአባት ሀገሩ ኢትዮጲያ ነው'' ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ

ሜጄር ጀኔራሉ በሰጡት ማብራሪያ የባህር በር ጉዳይ የብሄር የዘር የጎሀሳ አይለም የህልውና ጉዳይ ነው፣ ኢትዮጲያ የባህር በር ካላከኘች መቀጠል አትችልም፣ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን በስተቀር ማለትም ከግብፅና ከጥቂት ምቀኛ ጎረቤቶቻችን በስተቀር የአለም መንግስታት ኢትዮጲያ በዲፕሎማሲ መንገድ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት አምነዋል።

እናም ዋነኛው እኛ ላንድ ሎክድ አይደለንም እኛ ኦሽን ሊንክድ ሎክድ ነን ሲሉ በቦልድነስ ተናግረዋል። የአሰብን ወደብ ኢትዮጵያ ካልተጠቀመችው ይበሰብሳል እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም።

ሜ/ጄነራል ተሾመ ገመቹ ይህን የተናገሩት የባህር በር እና ወደብን አስመልክቶ በአድዋ ሙዚየም ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው፤ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ እንኳን በሰጥቶ መቀበል ሕግ በነፃ የባሕር በር ይገባት ነበር ብለዋል።

ለዚህ ንግግራቸው ሞሮኮ ለጎረቤት ሀገራት በነፃ የባሕር በር መስጠቷን በምሳሌነት አንስተዋል፤ ሞሮኮ ምዕራብ ሰሃራ አካባቢ ላሉ ሀገሮች፣ ጎረቤታቸው ላሉ ሀገሮች በነፃ የባሕር በር ሰጥታለች። ይሄን ለመድረክ ፍጆታ ሳይሆን እዚህ ሞሮኮ ኤምባሲ መጠየቅ ትችላላችሁ፤ ምንም ሳያስከፍሉ በነፃ፣ ይሄ ታሪክ ሳይሆን አሁን በሥራ ላይ ያለ ነገር ብለዋል።

የኛ ጉዳይ የምቀኝነት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር እንደ ሞሮኮ ዓይነት ልብ ስለሌላቸው ካልሆነ በስቀር እንኳን በሰጥቶ መቀበል ሕግ ነፃም ይገባን ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ቢኖራት ተጠቃሚዎቹ አሁን ባሕር በር አይገባችሁም የሚሉት የጎረቤቶቻችን ቡድኖች እና ግለሰቦች ናቸው፤ ጄነራሉ በማብራሪያቸው የአሰብን ወደብ በመጥቀስ ለኤርትራ ሳይሆን ኢትዮጵያን ብቻ እንዲያገለግል ታስቦ የተሰራ ነውም ብለዋል።

ይህን ወደብ በኤርትራ ያሉ ግመሎች እንኳን አያገኙትም በማለት አስረድተዋል፤ አሰብ የሚባለው ወደብ እራሱ ሲሰራ ዲዛይንድ ሲሆን ኢትዮጵያን እንዲያገለግል ብቻ ታስቦ ነው። አፋርን ጨምሮ ወደዚህ ያለውን ሀገር ወይም ደግሞ አቅጣጫ ብቻ እንዲያገለግል ተብሎ ስለተሰራ በዚያ በኤርትራ በኩል ግመልም አይደርስበትም።

የግመል ውኃ መጠጫ ይባላል እንጂ አሰብ ወደብ በጀርባው በኩል ግመልም አያገኘውም፤ ምንም ሊሆን አይችልም ሲሉ የመከላከያ የውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa