Fast Mereja

Fast Mereja

Share

Fast Mereja is one of media for best information subscribe Fast Mereja

22/11/2023

«ኦነግ ሸኔ በመንግስት ታዝዬ መንግስት ልሁን» በማለቱ ድርድሩ ያለውጤት ተበትኗል ሲል መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ

መንግስት አሁን ባወጣው መግለጫ «ባለፉት ሁለት ሳምንታት የሽብር ቡድኑ ከባለፈው ስሕተት ተምሮ የድርድር ነጥቦቹንም ሀገሪቱ ከደረሰችበት ምዕራፍ ጋር ለማጣጣም ይሞክር ይሆናል በሚል ተስፋ ሁለተኛ ዙር ውይይት ታንዛንያ ዳሬሰላም ላይ ሲካሄድ ቆይቷል። በሽብር ቡድኑ ዘንድ በዚህኛው ዙርም "መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ" ከሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት አልቻለም" ሲል መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታስቋል።

በኢፌዲሪ መንግሥት በኩል በሀገሪቱ ሰላም ሰፍኖ ኢትዮጵያ ያሉዋትን ጸጋዎች ወደ ተጨባጭ ሀብትና አቅም ቀይራ ብልጽግናዋን ታረጋግጥ ዘንድ ካለው ጉጉት በመነጨ ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ሞክሯል። ነገር ግን የሽብር ቡድኑ በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል። በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል። በመሆኑም ውይይቱ በዛሬው ዕለት ያለ ውጤት ተበትኗል። የኢፌዴሪ መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሔ ያለው አቋም እንደተጠበቀ ሆኖ ሕግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማስከበር ተልዕኮውን አጠናከሮ ይቀጥላል። በዚሁ አጋጣሚ ውይይቱ እንዲሳካ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት ሁሉ ምስጋና ያቀርባል ሲል መንግስት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

24/08/2023

አቴሌቱ ላይ የተሰራው ሴራ በአንደበቱ እንዲህ ብለዋል!!

26/12/2022

መቀሌ ገቡ!!!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Bethel
Addis Ababa