Tuji

Tuji

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tuji, Musician/Band, Addis Ababa.

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 18/07/2023
18/07/2023

የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ !!

የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው። ብልጽግና ስንል ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን አዝሎ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና የማኅበራዊ ገፅታ ያለው ነው። የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የሕዝቦች መሠረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የህዝቦችን ድኅነትና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው።

የፖለቲካ ብልጽግና ስንል ለዴሞክራሲ ባህል ማበብ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን በመገንባት፣ የሕዝቦች ነጻነትና እኩልነት ተረጋግጦ፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተከብረውላቸው የሚኖሩባት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተረጋገጠ፣ ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ማለታችን ነው።

የማኅበራዊ ብልጽግና መልካም ሀገራዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ማፍራት፣ በአካልና በአእምሮው የዳበረ ጤናማ ዜጋ መፍጠር፣ ከአስከፊ የማኅበራዊ ችግር የተጠበቀ ኅብረተሰብ መገንባት እና በሕዝቦች መካከል አዎንታዊ ሰላም በመፍጠር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ማለት ነው።

መልካም ሳምንት ይሁንልዎ !!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address


Addis Ababa