Inform Ethiopia
Ethiopia Forever
23/05/2026
: ከኮንጎና ከኡጋንዳ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት የኢቦላ ስርጭት ያሰጋቸዋል ተባለ !
ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ 10 የአፍሪካ ሐገራት የኢቦላ ቫይረስ ሥርጭት እንደሚያሰጋቸው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን በዝርዝሩ ኢትዮጵያ ተካታለች።
የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት የበላይ ኃላፊ ዣን ካሴያን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው የኢቦላ ወረርሽኝ ስጋት አለባቸው ተብለው ከተዘረዘሩት 10 ተጨማሪ ሐገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ታንዛንያና ዛምቢያ ይገኙባቸዋል ሲል DW ዘግቧል።
23/05/2026
“ለህወሃት የጥፋት ሴራ ማገዶ አንሆንም!” - የትግራይ ሚሊሻዎች
በዚህ ወቅት የህልውና ቀውስ ውስጥ የገባው ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን፣ ህጻናትን ሳይቀር በግዳጅ ወደ ጦር ካምፕ እየተማገደ ይገኛል። ይሁን እንጂ ይሄንን እኩይ ድርጊት የተገነዘበው የክልሉ ህዝብ ሴራውን በጽኑ እየተቃወመው ነው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ የቡድኑ ሚሊሻዎች ጭምር የፅንፈኛው የህወሃትን አጀንዳ በመቃወም ትጥቃቸውን እየፈቱ በስፋት እየኮበለሉ መሆኑን የተገኙ ታማኝ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በተለይም በደቡብ ምስራቅ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የቡድኑ ሚሊሻዎች የቡድኑን ትዕዛዝ አንቀበልም በማለት፣ በብዛት ወደ “ሃራ ማሬት” እየተቀላቀሉ መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቡድኑ የገጠመውን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት ለመሸፈን ሲል እላይ ታች እያለ ቢሆንም የሚያደርገው ጠፍቶት ግራ መጋባት ውስጥ ገብቷል።
ይህም ከየአቅጣጫው የሚነሳበትን የህዝብ ቁጣና ተቃውሞ በሃይልና በማስፈራራት ለማፈን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ህዝቡ ግን በአንድ ድምፅ “ጦርነት በቃን!” በማለት ላይ ነው።
ፅንፈኛው ህወሃት የህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው!
22/05/2026
በአለም ከባድ ሙቀት መጨመር ምክንያት የእባቦች የተናዳፊነት ባህሪየሰ እየጨመረ ምጣቱ ተነገረ!
📌በአየር ንብረት መዛባት ሳቢያ የመርዛማ እባቦች ፍልሰትና የንክሻ አደጋ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት አመለከተ
የአለም ሙቀት መጨመር መርዛማ እባቦች ቀድሞ ከሚኖሩባቸው ስፍራዎች በመውጣት የሰው ልጅ በብዛት ወደሚንቀሳቀስባቸው የእርሻ ቦታዎችና የመኖሪያ መንደሮች እንዲሰደዱ እያደረጋቸው ሲሆን፣ ይህም ከሰዎች ጋር ያላቸውን ንክኪና የአደጋውን መጠን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
በጥናቱ መሰረት በተለይም በአፍሪካ የሚገኙት የሚተፉ ዘንዶዎች (Spitting Cobras) እና በእስያ የሚገኙት ክራይቶች (Kraits) የሙቀት ማዕበሉን ለማምለጥ ሰፊ የቦታ ለውጥ እያደረጉ መሆኑ ተረጋግጧል።
ዘ ጋርዲያን የዓለም ጤና ድርጅትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ አገራት አደጋውን ለመከላከል በገጠራማ አካባቢዎች ለሚገኙ የጤና ተቋማት በቂ የእባብ መርዝ ማክሸፊያ መድኃኒቶችን (Anti-venom) እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።
22/05/2026
የጥራት ደረጃን በኦንላይን የሚያረጋግጥ
አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ!
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት፥ ሸማቾችና ነጋዴዎች የኪው አር ኮዶችን ሰስካን በማድረግ የምርቶችን የጥራት ደረጃ እንዲያረጋግጡ የሚያስችል "IES Verifier" የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል፤ ይህም የሀሰተኛ ምርቶችን ስርጭት ለመቀነስና የኢትዮጵያን ምርቶች በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ገበያዎች ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የመተግበሪያውን መመረቅ አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትርና የኢንስቲትዩቱ ቦርድ ሰብሳቢ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ ይህ ዲጂታል መድረክ የሀገሪቱን የጥራት ማረጋገጫ ስርዓት በማዘመን ለኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ መተግበሪያው ተጠቃሚዎች ምርቶችን በኦንላይን ስርዓት እንዲለዩና እንዲመረምሩ በማስቻል ህዝቡ ከሀሰተኛ ምርቶች ይልቅ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን እንዲገበይ እንደሚረዳው ጠቁመው፣ አሰራሩ የደረጃዎች ማረጋገጫ ሂደቱን በማቀላጠፍ የሀገሪቱን ምርቶችና አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያሳድጋል ብለዋል።
ይህ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ከተመዘገቡ በኋላ ከApp Store እና ከGoogle Play አውርደው መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ ከዚሁ ጎን ለጎን የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ምግብ ቤት፣ የ200 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው የኮንፈረንስ አዳራሽና የኢንስቲትዩቱን ታሪካዊ የስራ እንቅስቃሴዎች የሚያሳይ የኤግዚቢሽን ማዕከልን ጨምሮ ተቋማዊ መገልገያዎቹን ማደሱን አስታውቋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙት የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት የቴክኒክ ዳይሬክተር ሪዩበን ጊሶሬ በበኩላቸው፥ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በስኬት ለመተግበር ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች ወሳኝ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን አርአያነት ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Churchil
Addis Ababa