ABAS TUBE
ለማስታወስ ብቻ ||ሞት እያለ ክፋት||
Saka
18/09/2022
"15 እንቁላል በአንድ ብር ሽጬ፣ በ1 ብር 4 ደብተር ገዝቼ ነው የተማርኩት"
- ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ
| የክብር ዶ/ር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ላምበረት መናኸሪያ ጎን ላስገነባው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ምርቃት ሊወጣ የነበረን ሁለት ሚሊዮን ብር ለተማሪዎች ደብተር መግዣ በማዋል እያከፋፈለ ይገኛል።
“ደብተር ለአንድ ተማሪ በአዕምሮው ከያዛቸው ቀጥሎ ያሉትን ጠቃሚ ነገሮች ሁሉ ሰንዶ የሚያስቀምጥበት መዝገቡ ነው” ሲል ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገልጿል።
“እኔ እየረዳሁ ሳይሆን ኢንቨስት እያደረኩ ነው፤ ነገ የምንፈልገውን የሰው ኃይል ለማግኘት ዛሬ ላይ በመተባበር እና በመተጋገዝ መሥራት ይጠበቅብናል” ሲልም አክሏል።
"15 እንቁላል በአንድ ብር ሽጬ፣ በ1 ብር 4 ደብተር ገዝቼ ነው የተማርኩት"፣ ሲል ያለፈው ታሪኩን የተናገረው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ፣ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ማለት ሀገር እና ራስን መጥቀም መሆኑንም ገልጿል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
Addis Ababa