ethio 24

ethio 24

Share

በ ኢትዮ 24 ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከታማኝ ምንጮቻችን እምናገ

05/05/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,047 ላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ75 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)

ታማሚ 2 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ8 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት።

ታማሚ 5 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊት የመኖሪያ ቦታ ኦሮሚያ፣ ባቱ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት 16 ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) ደርሷል።

05/05/2020

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 24,088
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,758
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 5
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 60
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 75
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 140

05/05/2020

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ወሰነ!

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ህዝብና ለትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሙሉ እውቅና ከሚሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመሆን ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የህዝቡን መብት ከትርምስ ለመታደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን በክልል ደረጃ ለማድረግ ዝግጅት እንዲደረግ መወሰኑን አሳውቋል፡፡

የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይህ እንቅስቃሴ የፀረ ኮረና (ኮቪድ-19) ዘመቻዎችን እንዲሁም ተቀባይነት ያላቸውን ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን ባሟላ መልኩ የሚፈፀም ይሆናልም ብሏል።

ከላይ ያለውን ውሳኔ ጨምሮ ሌሎች በህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ የተላለፉ ውሳኔዎችን ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/TPLF-05-04

03/05/2020

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መናገራቸው DW ዘግቧል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢያ በአገሪቱ ዕርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአጠቃላይ ወደ 30 ሚሊዮን ያሻቅባል።

መንግስት የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል ያቋቋመው የምኒስትሮች ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ባደረገው እና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ለዚህ ብቻ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና ቻይና 2.1 ቢሊዮን ዶላር ዕገዛ መጠየቋን አቶ አሕመድ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በትናንትናው ዕለት የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ጫና ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ411 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አጽድቋል። የዓለም ባንክ በበኩሉ 750 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል የፋይናንስ ሚኒስትሩ አስረድተዋል -
ምንጭ-DW

02/05/2020

በግብፅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ በ358 ሰዎች በኮሮና COVID-19 መያዛቸውን ዘግቧል፡፡ ይህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 5 ሺህ 895 አድርሶታል፡፡

የጤና ሚንስቴር ቃል አቀባይ ካሊድ መጋህድ እንደገለጹት በ24 ሰዓታቱ 14 ታማሚዎች ሕይወት አልፏል ፤ ይህም በግብፅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 406 አድርሶታል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ 79 ሰዎች ማገገማቸውና ከሆስፒታል መውጣታቸው ነው የተነገረው፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Ethiopia, Addis Abeba
Addis Ababa
1000