Alebachew Worku

Alebachew Worku

Share

This page is about the Ethiopian Orthodox Tewahido Church Doctrine and other spiritual wisd

07/01/2026

"ሦስት ነገሮች ያስደንቁኛል!
አባቱ የማይቀድመው ልጅ፤
እናቱን የፈጠረ ሕፃን፤
ፈጣሪዋን የወለደች እናት"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ አደረሳችሁ!

Photos from Alebachew Worku's post 25/04/2025

ካህን አባት ማነው? አሁን ምን አጋጠመን?

ሊቀ ልሳናት Fantahun Wakie
========

✍️ የሊቀ ካህን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ ሥልጣን የሆነች ክህነት በጸጋ ለሰው ልጆች ለዘላለም እየታደለች ሰዎች እንዲድኑባት የተደረገበት መንገድ ቀኖናዊ፣ ሰንሰለታዊ፣ እምነታዊ፣ ሥርዓታዊ መንገዱ አንድ ብቻና ብቻ ነው። እርሱም ቀኖና ሐርያትን፣ ፫ቱን ዓለም አቀፍ የአበው ጉባኤአትን፣ በተቀደሰ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ቤተክርስቲያን የኖረችበትን ሥርዓት ያለመቆነጻጸልና በተቃራኒ መንገድ ባለ መውሰድ ነው።

✍️ ይህ መንገድ በሐዋርያት እጅ መጫን ብቻ የሚተላለፍ፣ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ በጸጋ የሚታደለውና በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው ክህነት ኮኖ ለሰው ልጆች መዳን የሚያገለግለው ሿሚና ተሿሚው የማይነጣጠሉ ምሥጢራት የሚፈጸሙባት እና ትእዛዛት በትግባር የሚተረጎሙባቸውን የሚከተሉትን ሐዋርያዊ ትውፊትና ቀነኖናት መከበራቸውን በሚያረጋግጡ አኗኗሮች ተሟልተው ሲገኙ ነው:-

፩) ያመነ፣ የተጠመቀ፣ በሜሮን የታተመ፣ የቆረበ፣ በክርስቲያናዊ ስነ ምግባር የጸና ሿሚና ተሿሚ ሲገናኙ፤

፪) የዚህን ዓለም ከንቱ ኢክርስቲያናዊ አስተምህሮዎችን፣ አሕዛባዊ አኗኗሮችን፣ ባዕድ አምልኮን እና የሰው ልጆችን ክብር የሚያበላልጡ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ዝንባሌዎችን በአፍ፣ በመጽሐፍና በተግባራዊ ሕይወቱ እየተዋጋ ለቤተክርስቲያን መንጋ የሚያበዛ፣ የሚጠብቅ፣ ለሰማእትነት የተዘጋጀ ሿሚና ተሿሚ ሲገናኙ፤

፫) የአበውን ትምህርት፣ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ፣ ሥርዓተ አምልኮና አርአያ ክህነቱን በሁሉ ቦታና ሁኔታ ውስጥ የሚጠብቅ ሿሚና ተሿሚ ሲገናኙ፤

፬) ቅድስናን ከሚቃረኑ ከዝሙት፣ ከሀሰተኝነት፣ ከስግብግብነት፣ ከዘረኝነት፣ ከኑፋቄ፣ ከትዕቢት፣ ከከፋፋይነት እጅግ የተጠነቀቁ ሿሚናንተሿሚ ሲሆኑ፤

፭) ሲመተ ክህነትን በምልጃ፣ በእጅ መንሻ፣ በጎሣና በብሔረሰብ ድርሻ አስደግፈው ያልተሾሙ፣ ያልሾሙ፣ ሥልጣኑን ለምድራዊ ዓላማ የማይጠቀሙ አባቶች ሲሾሙና ሲሾ'ሙ ነው።

* በዚህ ዘመን በእኛ ያጋጠመን ምንድነው?
* በገንዘብና በፖለቲካው ትልቅ ገብነት ስንቱ ተሾመ?
* እንደየዘመኑ የዘር ፖለቲካ ፍላጎት በጎሣ ድርሻ ተሰብስበው የክርስቶስን የጸጋው ማደያ ክህነትን ለኑሮአቸው ማደያደያ የተጠቀሙ ስንቶቹ ናቸው?
* ልጆቻቸው በኑፋቄ፣ በዘረኛ ፖለቲካዊ ትርክት ሲጠፉ እንደ መከላከል በተቃራኒው መለያየትን የሚመሩ አባቶች አልተፈጠሩም?

* ለመፍትሄው በዚህ ዘመን ከዚህ ውድቀት የተረፉት ከከካህናትና ክከምእመናን ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች ድርሻ ምን ይሁን?
የሁሉም የውይይት ነጥብ ሆኖ በመፍትሄው ላይ ቀኖና ሐዋርያትን ሳያፋልስ መደረግ የሚገባውን በማጋራት እንሳተፍ።

https://t.me/MekaneTibeb1

ኦርቶዶክሳዊ የትንሣኤ መዝሙራት ስብስብ 21/04/2025

https://youtu.be/CaFjGIsLLIQ?si=6qzi_RjwYCqfpgkt

ኦርቶዶክሳዊ የትንሣኤ መዝሙራት ስብስብ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ! በበዓለ ትንሣኤ እና በበዓለ ሃምሳ የሚዘመሩ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት Ethiopian Orthodox Mezmur #ኦ....

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
1000