Adane Getachew Ministry

Adane Getachew Ministry

Share

እምነት ፀጋ የሰጠውን ይወስዳል ...

25/05/2026

ማነህ አንተ ???

Who are you ? !

ላላችሁኝ በሞላ ...

መልሴ ይኸው...

ይኸው ማንነቴ ...

MY IDENTITY IN CHRIST

እኔ የኢየሱስ አማኝ ነኝ!

እማኝ ነኝ ስል....

ኃጢአተኛ መሆኔን አምኜ ...ለመዳን ...ጌታ ኢየሱስን ተቀብየአለሁ ... አድነኝ ብዬ....ጌታ ነህ ብዬ ኢየሱስን አምኜ መሰክሬአለሁ...ጥሪ አድርጌአለሁ በአደባባይ ጥያቄን ለእግዚአብሔር አቅርቤአለሁ ... ጌታን የምትቀበሉ እጃችሁን አውጡ ሲባል ?

እጄን አውጥቼ ጌታን በግሌ ተቀብዬአለሁ ... ጌታ ኢየሱስን ከኃጢአት ያድነኛል ብዬ አምኜ ተቀብየዋለሁ ።

ስለዚህ አማኝ ነኝ ብዬአለሁ ።ለኃጢአት ሞቶ... ለጽድቅ የተነሳውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አምኜዋአለሁ ።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አያሳፍረኝም... እርሱ ታማኝ ስለሆነ ።

ድኛለሁ።

ፀድቄአለሁ ።

አምልጫለሁ።

ሮሜ 10 (Romans)
9፤ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
10፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
11፤ መጽሐፍ፡— በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም፥ ይላልና።

የኢየሱስ አማኝ በመሆኔ ብቻ...

ከታች በዝርዝር የቀረበውን ማንነት ( IDENTITY ) አግኝቻለሁ

."የፀጋው ስጦታ"

ከዚህ በታች በዝርዝር የማቀርበው "እውነት"

እኛ አማኞች ብቻ ....

ዳግም በተወለደው መንፈስቸን ውስጥ በነፃ ያገኘናቸው በረከቶች እና የጸጋ ስጦታዎች ናቸው ።

ይህን "ነፃ ሰጦታ"( Grace )ማንም ሰው (who so ever) ኢየሱስን አምኖ እና ለኃጢአቱ ይቅርታ ጠይቆ ... አሁኑኑ ... መቀበል ይችላል....

እደግመዋለሁ!

ማንም ሰው ( who so ever ) አሁኑኑ ባለበት ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኖ... በምንም ሁኔታ ውስጥም ቢሆንም ... አባት እግዚአብሔርን ምህረት ጠይቆ...ጌታን እርሱም ክርስቶስ ኢየሱስን ተቀብሎ ...

አሁኑኑ ... በነፃ ... የጸጋ ስጦታዎቹን መቀበል ይችላል።

"አማኝ ያልሆናችሁ"

እባካችሁ!
ዛሬ!
አሁኑኑ!
ባላችሁበት ቦታ ላይ ሆናችሁ

ይህን ከታች ያለውን ፀሎት ከእኛ ጋር በእምነት ፀልዩና ተጠቀሙ!

ወዲያውም(immediately )

ይህን የስጦታ በረከት ትቀበላላችሁ!

እግዚአብሔር ሁሌም ይወዳችኋልና!!! ፈጥኖ ያደርግላችህዋል።

በሉ ቶሎ አብረን እንጸልይ ...

ይኸው ፀሎቱ....

" እግዚአብሔር ሆይ እኔ ኀጢያተኛ ነኝ በደሌን ይቅር በለኝ ለኃጢአት ይቅርታ የፈሰሰውን የልጅህን የኢየሱስ ክርስቶስን ደም እቀበላለሁ
ጌታን አዳኜ አድርጌ በግሌ አሁኑኑ እቀበላለሁ ።

አሜን!

በልጅህ ደም ስላነፃሀኝ አመሰግናለሁ"

አሜን!

እንኳን ደስ አለን ።

ተወዳጁ (የማይወደድ የለም)

አሁን

ዕውቀት እንካ ...

ዳግም ተወልደሃል... እንዲህም ሆኖልሃል ...

ምን ሆኖልኛል ? አትልም ?

እንዲህ ሆኖልሃል....

በመንፈስህ ዳግም ተወልደሃል ።

ዳግም ስለ ተወለደው መንፈስ ደግሞ ዝርዝር እንካ...

ዳግም የተወለደው መንፈሳችን
(our born again spirit )

የእኛ በኢየሱስ ያመንን አማኞች ማንነት ( IDENTITY) ይኸው ...

እኛ አማኞች!

ኃጢያተኝነታችንን አውቀን!

ለበደላችንም ይቅርታ ለማግኘት ስንል ኢየሱስን አምነን ! የዳንን እና የፀደቅን..

ጌታንም እንደግል አዳኛችን በመቀበላችን ብቻ

ያገኘናቸው ልዩ ጥቅሞች እና ማንነት ከዚህ በታች ተዘርዝሯል...

እነሱም (የፀጋ ስጦታዎቹ) የሚከተሉት ናቸው:-

ዝርዝር ወደፊት

ጠብቁ

በዝርዝር እና በጥልቀት ይቀርባል ...

ከገጹ ላይ አትጥፉ

ወዳጃችሁ #አዳነነኝ
መንፈሳዊ ሰው ።

24/05/2026

ሁሉ ነገር perfect አይደለም
ብዙውንም perfect እንዳልሆነ አየሁ

ቃልህ ግን perfect ነው
እስከአሁን ቃልህ perfect አለመሆኑን አላረጋገጥኩም ።

ቃልህ ብቻ perfect .

21/05/2026

ደስታ happiness
ደስተኛ happy

ትንሽ ስለ ደስታ

ለዛሬ አማርኛ እና እንግሊዘኛ እየቀላቀልን እናጥና...
እንግሊዝኛ የማይመቻችሁ...

ለአሁኑ ታገሱኝ

happy የሚለውን እንግሊዝኛ ቃል ... አማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ... ምስጉን እያለ ተርጉሟል

ስለዚህ

ምስጉን = ደስታ = happy

ከዚህ ትርጓሜ ተነስታችሁ

ምስጉን ሲያጋጥም ደስታ እያላችሁ ተረዱ...
እንግሊዝኛ እያስቀደምኩ .. ለትርጉም አማርኛ እከተላለሁ

አማርኛ የሚመቻችሁ... እየዘለላቸሁ.... አማርኛውን ብቻ አንብቡ ።

ENJOY ?

ተወዳጆች ሆይ

ፊትን የሚያበራ ደስታ ...
ፊትን ፏ የሚያደርግ ደስታ...
ሥጋን የሚፈውስ ደስታ የሚሆነው ...

ከውስጥ ...

ከልብ ... የተገኘ ደስታ ነው ...

እንደ መግቢያ

ደስ ያላት ልብ መልካም መድሀኒት ናት .... ደግ ትሰራለች..

ደስ ያላት ልብ...

A merry heart doeth good like a medicine

Proverbs 17 (KJV) - ምሳሌ
22: A merry heart doeth good like a medicine: but a broken spirit drieth the bones.

ደስ ያላት ልብ ልክ እንደ መድኃኒት ናት...

ምሳሌ 17 (Proverbs)
22፤ ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፤ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።

ሲጀመር

የልብ ደስታ .. ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው...

ደስ ያለው ልብ... ፊትን ያበራል

ደስ ያለው ልብ... ፊትን .. ፏ ! ያደርጋል

ምሳሌ 15 (Proverbs)
13፤ ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፤ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች።
14፤ የአዋቂ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፤ የሰነፎች አፍ ግን በስንፍና ይሰማራል።
15፤ ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት፤ የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው።

Proverbs 15 (KJV) - ምሳሌ
13: A merry heart maketh a cheerful countenance: but by sorrow of the heart the spirit is broken.
14: The heart of him that hath understanding seeketh knowledge: but the mouth of fools feedeth on foolishness.
15: All the days of the afflicted are evil: but he that is of a merry heart hath a continual feast.

ወሳኝ ጥያቄ

ልብ እንዴት ትደሰት ?

ልብ እንዴት በደስታ ትሞላ ?

ዋው

አስተውላችህዋል

በቁሳቁስ ደስታም ህይወትም አይገኝም...

ጌታ ኢየሱስ ነው እኮ ያለው...

ቁሳቁስ (ንብረት)(ገንዘብ) ትርፉ ለቁራሌው ነው... [እኔ አልኩ]

ቅራቅንቦ ቢበዛ .... ህይወትን አይሆንም ።

ጌታ እንዲህ አለ...

የገንዘብ(የንብረት) ብዛት .... ህይወትን አይሰጥም...

ሉቃስ 12 (Luke)
15፤ የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ፡ አላቸው።

የንጉሥ ጀምስ ትርጉም

For a man's life consisteth not in the abundance of the things which he possesseth....

Luke 12 (KJV) - ሉቃስ
15: And he said unto them, Take heed, and beware of covetousness: for a man's life consisteth not in the abundance of the things which he possesseth.

ታዲያ

Happy ማነው ? happy እንዴትስ ይኮናል ?

ቁልፍ ጥያቄ ?

ልብ እንዴት ትደሰት ?

Psalms 144 (KJV) - መዝሙር
15: Happy is that people, that is in such a case: yea, happy is that people, whose God is the LORD.

እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ደስተኛ ነው...

መዝሙር 144 (Psalms)
15፤ እንደዚህ የሚሆን ሕዝብ የተመሰገነ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው።

ሌላ ደስተኛ ... ይኸው

Psalms 146 (KJV) - መዝሙር
5: Happy is he that hath the God of Jacob for his help, whose hope is in the LORD his God:

አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ደስተኛ ነው...

መዝሙር 146 (Psalms)
5፤ የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው፤

ደሞ ሌላ ደስተኛ እንካችሁ

Proverbs 3 (KJV) - ምሳሌ
13: Happy is the man that findeth wisdom, and the man that getteth understanding.

ጥበብን የሚያገኝ ሰው ደስተኛ ነው...
ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው ....

ምሳሌ 3 (Proverbs)
13፤ ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤

ታስታውሱ እንደሁ

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ...

ስለዚህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ደስተኛ ነው ።

ተወዳጆች ሆይ

ድሀን የሚረዳ ... ደስታን ያገኛል

ለድሃ የሚራራ ደስተኛ ነው ...

Proverbs 14 (KJV) - ምሳሌ
21: He that despiseth his neighbour sinneth: but he that hath mercy on the poor, happy is he.

ምሳሌ 14 (Proverbs)
21፤ ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል፡ ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉን ነው።

ወዳጄ

ኧረ ሌላም ደስተኛ አለ...

Proverbs 16 (KJV) - ምሳሌ
20: He that handleth a matter wisely shall find good: and whoso trusteth in the LORD, happy is he.

በእግዚአብሔር የታመነ ደስተኛ ነው ...

ምሳሌ 16 (Proverbs)
20፤ ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔር የታመነ ምስጉን ነው።

ተወዳጆች

እንካችሁ የመጨረሻ ደስተኛ ..

Proverbs 28 (KJV) - ምሳሌ
14: Happy is the man that feareth alway: but he that hardeneth his heart shall fall into mischief.

ሁልጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ደስተኛ ነው...

ምሳሌ 28 (Proverbs)
14፤ ሁልጊዜ የሚፈራ ሰው ምስጉን ነው፤ ልቡን የሚያጸና ግን በክፉ ላይ ይወድቃል።

ስንሰበስበው

የዛሬው መልዕክት ሲሰበሰብ እንዲህ ይመጣል

አማኝ ሆይ

ደስታህን ከልብ ... ከውስጥ የሚመነጭ አድርገው... የእግዚአብሔርን ደስታ ተቀብለህ ልብህን በደስታ ሙላ... ልብ ውስጥ ያለ ደስታ ... ሁልጊዜ የሚበላ ... የሁሌ ግብዣ ነው ። በየቀኑ የምትመገበው የደስታ ግብዣ ከልብህ አግኝ ...

ደስታን ውጭ ዓለም ላይ አትፈልግ... ትርፉ ድካም ነው ...የዓለም ደስታ ውጫዊ እና ጊዜያዊ ነው ...

ወዳጄ

የልብ ደስታ ነው ለሥጋህ መድሃኒት

የዓለም ደስታ ... የቁሳቁስ ደስታ ፣ የመጠጥ ደስታ ፣ የሃሺሽ ደስታ ፣ የአደንዛዥ ዕፅ ደስታ ፣ የዝሙት ደስታ ... የዝና ደስታ .... ከወዘተ የተገኘ ደስታ ... አይጠቅምህም... ለሥጋህ መድሃኒት አይሆንህም ... ተወው

ልብን የሚሞላውን ... ልብ ላይ የሚበቅለውን... የእግዚአብሔርን ደስታ ፈልግ...የልብ ደስታ ነው ፊትህን ሁሌ የሚያበራ ...ሥጋህን ሁሌ የሚፈውስ ...

አሁን ወሳኝ ጥያቄ የሚሆነው ....

ልብ እንዴት ትደሰት ? የሚለው ነው

ወዳጄ

ልብህ እንድትደሰት

ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር... ያኔ ደስታ ልብህን ይሞላል

ልብህም... መድሃኒት ትሆናለች ... ፊትህንም ታበራለች...

Proverbs 15 (KJV) - ምሳሌ
13: A merry heart maketh a cheerful countenance: but by sorrow of the heart the spirit is broken.

ምርቃት

ጭማሪ እንካ ...
ወዳጄ

ልባችንን ማስደሰት ያለብን ለምን መሰለክ ?

ይኸውልህ

በልብ ያለ ደስታ ...እንደ ሁልግዜ ግብዣ... ነው ... ሁሌ መዥረጥ እየተደረገ የሚበላ

Proverbs 15 (KJV) - ምሳሌ
15: All the days of the afflicted are evil: but he that is of a merry heart hath a continual feast.

ስንደመድመው

ደስታን የተሞላች ልብ
ልክ... እንደ መድሃኒት ናት ...

ደግ (መልካም) ትሰራለች ።

እንቀምረው ...FORMULA

ደስታ የተሞላች ልብ = መድሃኒት

Proverbs 17 (KJV) - ምሳሌ
22: A merry heart doeth good like a medicine: but a broken spirit drieth the bones.

ደስ ያላት ልብ
መልካም መድሃኒት ናት ...

ስለዚህ

ልብህን ደስታ ሙላት

መድሃኒት እንድትሆን

ምሳሌ 17 (Proverbs)
22፤ ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፤ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።

ወገን

የልብ ደስታ ላይ እንስራ ።

ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት እንዋል ! ድሀን እንርዳ...በእግዚአብሔር እንታመን... እግዚአብሔርን አምላካችን እናድርግ... ጥበብን እናግኝ ... ማስተዋልን ገንዘባችን እናድርግ...

ብቻ

የልብ ደስተኛ ለመሆን ...

ተግተን...

መጽሐፍ ቅዱስ እናንብብ

በእግዚአብሔርም ሥርዓት እንመራ

የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል....

መዝሙር 19 (Psalms)
7፤ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
8፤ የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
9፤ የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
10፤ ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
11፤ ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።

አሜን ።

ወዳጃችሁ #አዳነነኝ
ከ ልዑል መጠጊያ
From the secret place of the most High
---------------------------------------------

16/05/2026

#የምስራቹን #ማብሰር !

የገፃችን ወዳጆችና አባሎች....

ዛሬ በጌታ ፍቅር አንድ ትዕዛዝ እንሰጣችህዋለን ... አንድ ለየት ያለ ነገር እናደርጋለን ...

ያመነበት ብቻ ይሳተፍ !

እኔ አለሁ ይበል !

ወዳጆች !

እስቲ ለምታገኙት አንድ ሰው ወንድ /ሴት [ለሁሉም ሰው ፣ ለማንኛውም ሰው ] በሥራ ቦታ ፣መንገድ ላይ ፣ ቤታችሁ ውስጥ ፣ መዝናኛ ሥፍራ ሊሆን ይችላል ....

ብቻ ለአንድ ሰው የሚከተሉትን ሚስጥሮች ንገሩ ...

1) ዛሬም በእግዚአብሔር ተወዳጅ መሆኑን !

2) ዛሬም እግዚአብሔር ምርጥ ነገሬ የሚለው እሱን / እሷን መሆኑን !

3) ዛሬም በጌታ የተወደደች መሆኗን !

4) ዛሬም እግዚአብሔር አንድ ልጄን እስከ መስጠት በሚደርስ ፍቅር እወደዋለሁ/ እወዳታለሁ እያለ መሆኑን!

5) ዛሬ በምንም ሁኔታ ውስጥ ይሁን ገና ጠላት እየሆነ እንኳን ... ከፍቅሩ የተነሳ... ለእሱ/ለእሷ ሲል ኢየሱስ .... ነፍሱን እንደሰጠ ንገሩ/ንገሯት ....

6) ብቻ "እንዲያው" ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እግዚአብሔር ይወደናል ብላችሁ ንገሩ ...
.. ንገሩ ፤ አውሩ ፤ መስክሩ ፤ በአጠቃላይ

ተወዳጆች !

የምስራቹን ለአንድ ሰው አብስሩ !

ዛሬም

እግዚአብሔር እንደሚወደው አስታውሱት !!!

እግዚአብሔር ፍቅር ነው!

ወዳችሁ አካፍሉ [ Like & Share ]

#ወዳጃችሁ #አዳነነኝ !

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa