Ethio Mereja

Ethio Mereja

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Mereja, Journalist, Adis Ababa, Addis Ababa.

25/04/2025

28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ

28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርትን ጠቅሶ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሞሽን ይፋ አደረገ፡፡

የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል ብሏል።

የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡

ባንኮች ከአነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ብድሮችን እየሰጡ ነው የተባለ ሲሆን ይህ አገልግሎት እየጨመረ መሄድ እና የበይነ መረብ ማጭበርበሮች መበራከት ባንኮች የሚያጡት ገንዘብ ሊጨምር እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡
(ፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ)

12/04/2025

ጨዋታው በአቻ ተጠናቋል ፣ ነገሮች ለሊቨርፑል መስመራቸውን ቀጥለዋል ...

ሰለ ጨዋታው ምን ይላሉ ?

Photos from Ethio Mereja's post 12/04/2025

98 ነጥብ 66 በመቶ አፈፃፀም!..

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈጻጸም አሁን ላይ 98 ነጥብ 66 በመቶ መድረሱና የግድቡ ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ መግባታቸው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩት የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ይፋ ኾነ።

12/04/2025

አሽከርካሪዎች እንድታውቁት‼️

4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች አንድ አቅጣጫ ብቻ ሆነው እንዲያገለግሉ ስለተደረጉ አሽከርካሪዎች በተተከሉ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶች መሰረት እንዲጓዙ ተነገረ

መንገዶቹ ከጥይት ቤት እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት፣ ከቤተመንግስት ፖርኪንግ እስከ ጥይት ቤት እንዲሁም ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ሳይንስ ሙዝየም ቀድሞ የነበረው ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ (Two way) ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ (One way) የተቀየሩ ናቸው።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

12/04/2025

በመካከለኛው ዘመን፣ ባላባቶች ወደ ጦርነት ከመሄዳቸው በፊት በሚስቶቻቸው ላይ የንጽሕና መታጠቂያ ማድረግ የተለመደ ነበር...

የዚህ አሰራር ዓላማ ባሎቻቸው በማይኖሩበት ጊዜ የሴቶችን ታማኝነት ለማረጋገጥ ነበር...ቀበቶውን ለማስወገድ ቁልፍ ስለነበራቸው ይህ ለወራት ወይም ለዓመታት ሊቆይ ይችላል...😍

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Adis Ababa
Addis Ababa