Girum.com
የጉራጌ እና የኢትዮጵያን ድንቅ የባህል እሴቶች፣የቱሪዝም ሀብቶች፣ታሪካዊ ቦታዎች፣ አስደናቂ ሁነቶች ወደሚጎበኙበት ገጽ እንኳን ደህና መጡ 🙏
የብሳቢ ❤️
20/05/2026
መሪነት መልክ ቢኖረው 🙌💪
20/05/2026
ሳር በቅሎበት የነበረዉ የከሬብ መካከለኛ መስኖ ፕሮጀክት ወደ ተግባር 💪💪
በምሁር አክሊል ወረዳ የከሬብ መካከለኛ መስኖ ፕሮጀክት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የግንባታ ሂደት ምልከታ አድርገዋል።
ሲጠናቀቅ 1660 ሄ/ር መሬት በላይ የሚያለማ ከ4ሺ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ሲሆን ቀድሞ በደቡብ ክልል ግንባታው የተጀመረ ፕሮጀክት ነው።
20/05/2026
ወረዳዋ ሠላማዊ፣ ልማት ወዳድ ህዝብ ያላት በመሆኗ በመቀናጀት የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ያስፈልጋል:- አቶ ብስራት ገብሩ
ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (ምሁር አክሊል ሀዋርያት)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው(ዶ/ር) በተገኙበት ከማህበረሰቡ ከተወጣጡ አካላት ጋር በተደረገ መድረክ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ ባለፉት አመታት ተወላጅ ባለሀብቶችንና የተለያየ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በርካታ የልማት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ገልፀዋል።
የመንግስትን፣ የባለሀብቱንና የማህበረሰቡን አቅም በማቀናጀት በግብርና፣ በከተማ ልማት፣ በትምህርትና በንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ምሁር አክሊል ወረዳም ዕምቅ ያላት በመሆኑ ይህንን ባገናዘበ መልኩ የልማት ተሳትፎን በማሳደግ ወረዳዋን ብሎም ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታ ለማሸጋገር በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተ የህዝቡ ትልቁ ጥያቄ የዋና መንገድ አስፓልት፣ የከሬብ መካከለኛ መስኖ ግንባታ፣ የመብራት ተደራሽነትና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት መሆኑን ገልፀዋል።
7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።
መረጃው የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።
20/05/2026
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል 🙌💪
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Address
Addis Ababa