Daniel Wodajo

Daniel Wodajo

Share

Grateful to Serve You

28/06/2026

“እኔ እንዲህ አይነት ነገር ምን እንደማደርግ ምን እንደምል ይጠፉኛል ተው እንደዚህ አታድርግ አላልኩህም🤷‍♀️ ቆይ እነሱንስ በትክክል አመስግኛቸዋለው ?” ከቪዲዮው በኋላ እንዲህ ነበር ያለችኝ

የኔ ትሁት ሚስት እኔ ደግሞ አንቺን ድንገት ማስደሰት ደስ ስለሚለኝ እኮ ነው 😘 አይዞሽ ደግሞ እነሱንም ቢሆን እኔም በደንብ አመስግኜልሻለው 🙏 ነፍ አመት ከጎኔ ሆነሽ ኑሪልኝ አፈቅርሻለው የኔ ንግስት 👸❤️❤️❤️

መልካም ልደት 🎂🍰🎂

26/06/2026

"ችግር ማለት መልስ የሚፈልግ ወይም ትክክለኛ መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ነው።”

ተመሳሳይ ችግሮች ከዓመት እስከ ዓመት አልፈታ ኳሏችሁ ፤ ከራሳችሁም ከፈጣሪም ከመጣላት አልያም ለመከራ እንደተፈጠራችሁ ከማሰብ ይልቅ ይሄንን አድርጉ !

ችግሩ ራሱ ላይ ማተኮር አቁሙና ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ :-

"እኔ መመለስ ያለብኝ ትክክለኛ መልስ ምንድነው? ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠኝ?"

ትምህርት ቤት ለአንድ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ እስካላገኘን ድረስ ውጤታችን ሁሌም "ኤክስ" (X) ነው።

ወደ ቀጣዩ ክፍልም የምንሸጋገረው ትክክለኛውን መልስ አግኝተን "ራይት" (✓) ስንሆን ነው።

በህይወትህም ውስጥ ያለው ህግ ልክ እንደዚሁ ነው። ለችግሮቻችን ትክክለኛውን መልስ ከሰጠን ብቻ ነው የህይወት ደረጃችን ከፍ የሚለው ፤ ካልሆነ ግን እዛው መዳከራችን አይቀርም።

ስለዚህ ከማያልቅ አዙሪት ተላቃችሁ ህይወታችሁን መቀየር ከፈለጋችሁ ችግሩ ላይ ማተኮሩን ተውት እና ትክክለኛውን መልስ በራሳችሁ መንገድ ፈልጉ አልያም በትክክለኛው መንገድ ለእናንተ ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ሰጥተው ደረጃቸውን ከፍ ካደረጉ ሰዎች ልምድ ቅሰሙ።

መልካም ምሽት 🙏
ዳንኤል ወዳጆ

25/06/2026

እስኪ ሃሳብህን ኮመንት ላይ አስቀምጥልኝ !

24/06/2026

ፈጣሪ በሰዓቱ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ያዘጋጃል !

Photos from Daniel Wodajo's post 22/06/2026

ህልምህን የምታሳካበት ሚስጥር !

መልካም ምሽት 🙏

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa