Anwar seid
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Anwar seid, College & University, Addis abebe, Addis Ababa.
የስም ሀብታም ነኝ። ማለቴ ብዙ መጠሪያ ስም ነው ያለኝ። ከ’ነሱ ውስጥ አንዱ ዛህራ ነው። ይህንን ስም ያወጡልኝ የቁርዓን ቤት ሸኼ ናቸው። ይወዱኝ ነበር። ለዛም ይሆናል ስም ያወጡልኝ። እሳቸው ከሌሉ በቦታቸው ይሾሙኛል። እናም እርሳቸውና የቁርዓን ቤት ልጆች በዚህ ስም ነው የሚጠሩኝ። ትዝ ይለኛል። እንደዛሬው ጁምዓ ሲሆን ቂርዓት አይኖርም ነበር። የእረፍት ቀን ነው። ቁርዓን ከምንቀራባት ትንሿ መስጊድ በቅርበት የምንኖር ልጆች በጠዋት ሄደን የሸኻችንን ጀለብያና ጥምጣም እናጥብላቸዋለን። ልብሳቸው እስኪደርቅ ፀሐይ እየሞቁ፣ ሲዋክና ሙስበሐቸውን ይዘው ጎርደድ እያሉ ይጠባበቁና ሰዓት ሲደርስ ለባብሰው ወደ ዋናው መስጅድ ይሄዳሉ።
ሸኻችን እንደዬአቅማችን ያስቀሩንና "በሉ ሀይያ ከርሩ!" ይሉናል። ያስቀሩንን በትእዛዛቸው መሰረት ደጋግመን እናጠናና "ተሰሙን" ብለን ዞረን እርሳቸው ጋር እንቀርባለን። ያኔ እንደ አሁኑ የቁርዓኑን ምዕራፎች በስም አናውቃቸውም ነበር። በምዕራፎቹ መጀመሪያ ላይ በሚገኘው አንቀፅ ቃል እንጂ። "የት ደረስሽ?" "ፈሰብቢህ!" ማን ጋር ነሽ? "ተባረክን አለፍኩ።" በአንዳንድ ምዕራፎች መጨረሻ ላይ ካለው ቃል ጋር ደግሞ አዛምደን እንገጥም ነበር። ለምሳሌ በሱረቱል ፈትሕ መጨረሻ ላይ ኢንነሁ ካነ ተውዋባ ካልን በኋላ የሸኻችን ላም ትንቧቧ እንል ነበር። ሱረቱዱሐ ላይ ደግሞ ወአምማ ቢኒዕመቲ ረብቢከ ፈሐድዲስ ብለን የሸኻችን ልብስ ሁሉም አዳዲስ እንላለን። ሌላው በሌሎች አካባቢዎች ሲቀራ አናባቢ ምልክቶች ፈትሐ፣ ከስራ፣ ዾማ እንደሚባሉት ደሴ ነስባ፣ ኪፍዻ፣ ኡርፋ ነበር የምንለው። የአሊፉን ነስባ አ…ኪፍዻውን ኢ…ኡርፋውን ኡ አ ኢ ኡ። የቁርዓኑን ቃላት አቀጣጥሎ የመቅራት ስልት "ሸድዳ" የሚባል ሲሆን (ከማጥበቂያው ሸድዳ የተለዬ ነው) ጀማሪዎች የሚጠቀሙት ፊደላቱን ነጣጥሎ ቀርቶ በመጨረሻ ማገጣጠም "ውጥጥ" ይባላል። ሌላው ነገር አድጌ ትርጉሙን ከተረዳሁ በኋላ እንደገመትኩት ምናልባት በልጅነት አንደበት የትርጉም መፋለስ እንዳያመጣ ከመስጋት ይመስለኛል ሸኾቻችን ሱረቱል ካፊሩንን ያዘልሉን ነበር። ሙስሊም ያልሆኑ ወዳጆቻችን ታድያ እንደ ከባድ ግኝት "ቁርዓን ውስጥ ሳይቀራ የሚታለፍ ሚስጥር አለ!" እያሉ ይንሾካሾኩ ነበር።😆
ከሁሉም ደስ የሚለው በዬደረጃው ደግሰን የምናበላው ነገር ነው። ከላይ ወደታች ስለነበረ የምንቀራው ኢቅራዕ ላይ የደረሰ ቆሎ ያበላል። ዐምመን የጨረሰ ድፎ ያስደፋና ከጆሊጁስ ጋር ያመጣል። እንዲህ እንዲህ እያለ ጊዜው ደርሶ ሲኸተምማ ደስታ ነው። ሰደቃ ነው። በግ ይታረዳ
ል።
እንዲህ እ
ንደዛሬው እንደ አጭር ኮርስ የሶስት ወር ለብ ለብ ሳይሆን በፊት የቁርዓን ኺታም ይሄን የመሰለ ወዝና ለዛ ነበረው።
My ቂርኣት style via atiqa ahmed ali
ጁምዓ ሙባረክ!💚💚💚
ይህም ያልፋል 😐😐😐😐
03/06/2023
አሁንም ይዋሹናል። ልክ ክህደት እንደፈፀሙብን ሁሉ የጋራ ግብረሀይል እያሉ በግፍ የገደሏቸውን ዜጎች አፅም እያነደዱ ከአጥንታቸው ብራና ቀለም ፍቀው የተሳሳተ ሀሰተኛ መግለጫ ይሰጣሉ። በመሰረቱ አንድም መሰረታዊ የመረጃ ግብአት አቀባበልን መሰረት ያደረገ አዎንታዊ መግለጫ መስጠት አያቁም። አሰለጠናቸው የሚሏቸው የፖሊስ አባሎቻቸው እጅግ አረመኔና ኢሰዋዊ አረመኔ እንጅ አንድም የሰለጠነና የተገራ ህዝባዊ ሀይል የላቸውም።
መጅሊሱን እንደ ፍየል ማሰሪያ ገመድ ነው የናቁት። እንደተቋም አያከብሩትም። አይፈሩትም። ይህ የዋህ ህዝብ ስንቱን ችሎ የተሸከመውን ስረአት ይፈርስ አይመስላቸውም። በግድ ጦርነት እገጥማለሁ አትበሉ ተው ብለን ስንመክራቸው እናተ ሁሉንም የምታቁት ለምን ስሜታዊ ትሆናላችሁ ይሉናል። የህዝብ ልጅ ነን። ህዝብ የሰቀለን ህዝብ የተቀበለን በህዝብ የተወደድን እንጅ ከስረአታቸው ጋር ውል የለንም። ይህ መንግስት በሰራው ስህተት 238 ዜና ተሰርቶበታል። ይህ በአለማቀፍ ሚዲያ ጉዱ የተዘከዘከው መንግስት አደገኛ ኢስላም ፎቢያ እንዳለው የአለም ሙስሊም ኡለሞች የሰሩበትን ዜና አይተናል።
ለነሱ ይህ አደገኛ ሁኔታቸው መሆኑን አያቁም።
ስልጣን ከተረከቡ ጀምሮ አንድ ነጥብ 2 ሚሊየን የአገሪቱን ዜጋ አስገድለዋል። ልክ የኩዌትን ህዝብ ቁጥር ጨርሰዋል። 10 አመት የተደረገው የሶሪያ ጦርነትን በእጥፍ በልጠው ተገኝተዋል። ሙስናቸው አለምን ያስንቃል። የስልጣን መዋቅራቸው እጅግ ያፀየፈ ነው። ይህንን ጎደሎ ተሸክሞ የኖረ ህዝብ ላይ ጥይት ሲተኩሱ አያፍሩም። አይፈሩም። ለምን ከተባለ ንቀት አላቸው። ስለዚህ ልክ ማስገባት ያለበት ህዝቡ ነው።
ደም ለምደዋል። ገለው መዋሸት ውሸት ማቀነባበር ሱሳቸው ነው። 5 አመት አታለሉን አምስት አመት ገደሉን ረሀብ ጦርነት ዝርፊያ ማፈናቀላቸው ሁሉ ጆኖሳይድ ነው። በደም የሰከረ ስረአት ለማንም አይጠቅምም። ከአዲስ አበባ 400 km እርቀት ላይ በአማፂ እየተቆላ ዋና ከተማ ላይ የተቀመጠን ሰላማዊ ህዝብ ጥላቶቸ ናቸው የሚል ስረአት ነው አሁን ያለው ስረአት። እያበዱ የሚስቁ በሰው ደም ውስኪ የሚራጩ በደሀ ኢኮኖሚ የሚንደላቀቁ አንድም ለአገር ሰላም የማያስቡ ለሚመሩት ህዝብ የማይራሩ አደረጃጀቶችን ይዘው ነው እናበልፅጋችሁ የሚሉን።
ሱሌማን አብደላ
ደወል ሲደወል
🍁 🍁 🍁
በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሰጥሜ እያለ የቤቴ በር በኃይል ተንኳኳ። «በዚህ ደረቅ ሌሊት በሩን የሚያንኳኳው ማን ነው?» በማለት በድንጋጤ ተነሳሁ። ከቅርብ ዘመዶቼ አደጋ ያጋጠመው እንዳይኖር ሰጋሁ። አንደበቴ ተርበተበተ። እጆቼ ተንቀጠቀጡ። እያለከለኩ ወደ በሩ አመራሁ። ፈራ ተባ እያልኩ በሩን ስከፍተው እንግዳ የሆነ ፍጡር ከፊቴ ተገትሯል።
«ጤና የለህም እንዴ ?? ለመሆኑ ሰፈሩን እና ቤተሰቦቼን ሰላም እንደነሳህ ታውቆሃል? ማን ነህ አንተ ??» አልኩት።
«ተረጋጋ ! ካንተ ውጭ በሩ ሲንኳኳ የሰማ አንድም ሰው የለም። አሁን ሰዓት የለንም። ፈጠን በል እንሂድ» አለኝ።
«ወዴት ነው የምንሄደው?» አልኩት።
«እኔ መልዓከ ሞት ነኝ። የምድር ቆይታህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊገባደድ የቀሩህ ደቂቃዎች ኢምንት ናቸው። አሁን ጨርቄን ማቄን ሳትል በለበሰከው የመኝታ ልብስ ተከተለኝ» አለኝ።
ፊቴ በእንባ ጎርፍ ታጠበ። ሰውነቴ ከብርድ አምልጠው በእናታቸው እቅፍ ውስጥ ለመግባት እንደሚሽቀዳደሙ ጫጩቶች ተርገፈገፈ። መልዓከ ሞትን ቢያንስ ተጨማሪ የአስር ደቂቃ ዕድል እንዲሰጠኝ ተማጸንኩት። ለበርካታ ቀናት ያስቀየምኳት ሚስቴን ይቅርታ ለመጠየቅ እና በእንቅልፍ ዓለም ውስጥ ያሉ ልጆቼን እንድስማቸው ፈቃዱን ጠየኩት። ይህ ጉዳይ በጭራሽ የማይታሰብ እንደሆነ ቁርጡን ነገረኝ።
«ከሁለት ወራት በላይ ወላጆቼን በአይነ ስጋ አላየሁም። በስልክም እንደምን ናችሁ ብዬ አላናገርኩም። እባክህን አንዴ ድምጻቸውን እንድሰማ ፍቀድልኝ ?» በማለት በጉልበቴ ተንበርክኬ ለመንኩት። ሰማይ ከፍ መሬት ዝቅ ቢል የማይሆን ነገር እንደሆነ አረዳኝ።
«ባለቤትህን ከማስቀየምህ ሌላ ይህን ያህል ጊዜያት የወላጆችህን ደህንነት ለማወቅ አለመጣርህ ትልቅ ነውር ነው። ጥያቄህ በፍጹም ተቀባይነት የለውም። የመጨረሻ ህቅታህ ከሰዓቷ ዝንፍ የማትል መሆኑን ማወቅ አለብህ። ስማ አንተ ክፉ የሆንክ ! በል አሁን ዓይኖችህን ክፈት» ሲለኝ ድንገት ከእንቅልፌ ባነንኩ።
«በህልም ዓለም ስዋኝ ኖሯል። ከእንቅልፌ የነቃሁት ከሌሊቱ 9:00 ላይ ነው። አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እየዬዬን አቀለጥኩት። ፊቴ በእንባ ጎርፍ ወረዛ። በክስተቱ አላህ በምድር ላይ የመኖር ዕድል ሰጥቶኝ እኔን ለማስተማር ያሳየኝ ህልም መሆኑን ተረዳሁ። ሚስቴ ከእንቅልፏ እንድትነቃ በማድረግ ጉዳዩን አጫወትኳት። ይቅርታ አደረገችልኝ። ልጆቼ ከተኙበት አልጋ ላይ በፍቅር ተጠመጠምኩባቸው። ሲነጋ ስንቄን ሸክፌ ወደ ወላጆቼ ቤት አቀናሁ። ይቅርታ እንዲያደርጉልኝ ተማጸንኩ። ጥያቄዬም ተቀባይነት አገኘ።» በማለት አንዱ ባለ ታሪክ ያጫውተናል...
ምጥን አስተምህሮ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ባቡሩ ፈጣን ነው። እስከዛሬ በመንገዱ ላይ ባሉ ፌርማታዎች ቆመው የሚጠብቁ ብዙ ተጓዥ መንገደኞችን እየለቀመ አንስቷል። የኛም ወረፋ ደርሶ ነፍስና ስጋችንን ለመነጠል ተልዕኮ የተሰጠው መልዓከ ሞት የቤቶቻችንን በር ከማንኳኳቱ በፊት ቀሪ የቤት ስራዎቻችንን ንቁ ሆነን ከስር ከስሩ ለመቀነስ እንሞክር።
Mohammed Ahmed
ስለ ቁርኣን በጥቂቱ እንናገር!!
-----
(በአፈንዲ ሙተቂ)
------
ቅዱስ ቁርኣን 114 ምእራፎች (ሱራ) እና 6236 አንቀጾች (አያህ) ያሉት የአላህ ቃል ነው። በየወሩ ለማንበብ በሚያመች መልኩም በሰላሳ ጁዝእ (ክፍሎች) ተከፋፍሏል።
ረጅሙ የቁርኣን ሱራ "አል በቀራህ" ሲሆን እርሱም 286 አንቀጾች አሉት።
አጭር የሆኑት የቁርኣን ሱራዎች "አል ዐስር"፣ "አል ከውሠር" እና "አል ነስር" ሲሆኑ እያንዳንዳቸው ሶስት አንቀጾች አሏቸው።
ረጅሙ የቁርኣን አንቀጽ ስለ ብድርና ውል የሚያወሳው የሱረቱል በቀራህ 282ኛ አንቀጽ ነው። ይህ አንቀጽ ለብቻው የአንድ ገጽ ርዝመት አለው።
አጫጭሮቹ የቁርኣን አያዎች "ጣሃ"፣ "ሃ ሚም" እና "ያ ሲን" ናቸው። እነዚህ አንቀጾች በሁለት ፊደላት ብቻ ነው የተዋቀሩት።
መጀመሪያ የወረደው የቁርኣን ሱራ "አል ዐለቅ" ሲሆን መጨረሻ ላይ የወረደው ሱራ "አል ነስር" ነው።
በአንቀጽ ደረጃ ደግሞ በቅድሚያ የወረዱት የሱረቱል ዐለቅ አምስት የመጀመሪያ አንቀጾች ሲሆኑ መጨረሻ ላይ የወረደው የሱረቱል ማኢዳ ሶስተኛ አንቀጽ (አያህ) ነው።
የቁርኣን ሱራዎች በመጽሐፉ ውስጥ የተቀመጡት በወረዱበት ቅደም ተከተል ሳይሆን ለውሀል ማሕፉዝ (ጥብቁ ሰሌዳ) በሚባለው ታላቁ ሰሌዳ ላይ በተጻፉበት መልክ ነው።
የቁርኣን አወራረድ ሁለት መልክ አለው። በመጀመሪያ ከለውሐል ማሕፉዝ (የተጠበቀው ሰሌዳ) ተወስዶ "ለይቱል ቀድር" በምትባለው ታላቋ የረመዳን ሌሊት፣ በቅርቢቷ ሰማይ በሚገኘውና ቤይቱል ማእሙር በሚባለው ቤት ወደ ጂብሪል ወርዷል።
ቁርኣኑ ወደ ጂብሪል የወረደው በተሟላ ሁኔታ እና በለውሐል ማሕፉዝ ላይ ያለውን የሱራዎችና የአያዎች ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ነው።
የነቢዩ ሙሐመድ መልእክተኛነት ከተበሰረ በኋላ ደግሞ ጂብሪል ቁርኣኑን በምእራፎችና በአንቀጾች እየከፋፈለ በ23 ዓመታት ውስጥ በነቢዩ (ሰዐወ) ላይ አውርዷል።
ነቢዩ ሙሐመድም (ሰዐወ) ወሕዩን ከጂብሪል መቀበል የጀመሩት በወርሃ ረመዳን "ለይቱል ቀድር" በምትባለው ትልቋ ሌሊት ነው። "ረመዳን" የወራቶች ንጉሥ የሚባለው በዚሁ ምክንያት ነው።
----
አላህ ለይቱል ቀድርን ከሚወፍቃቸው ባሮቹ ያድርገን።
አሚን
አሚን
አሚን
አሚን
አሚን
----
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Website
Address
Addis Abebe
Addis Ababa