Axis Law

Axis Law

Share

Legal Service

Telegram: Contact @MrYenesewD 13/08/2024

የግል ድርጅት ሰራተኞች የደረሳባቸውን አስተዳደራዊ በደል ወደ ህዝብ እንባ ጠባቂ ማመልከት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቆሙበትን ወይም የሚታረሙበትን ቀልጣፋ አሰራር በመዘርጋት ለመልካም አስተዳደር መሰረት መጣልን አላማ አድርጎ በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት በማስፋት በግል ድርጅቶች የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን አቤቱታ መቀበል እና ምርመራ ማካሄድ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት በስራ ላይ የቆየውን የተቋሙን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 1142/2011 ለማሻሻል አዋጅ ቁጥር 1307/2016 ፀድቋል።

ይህ ማሻሻያ አዋጅ የያዛቸው ዋና ዋና ለውጦች ተቋሙ በግል ድርጅቶች ጭምር ስልጣን እንዲኖረው ከማድረግ ጋር የተያያዙ ሲሆኑ እነሱም፤
1. ስልጣን ባለው አካል የወጣ እና በስራ ላይ ያለ ሕግን በመፃረር በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚፈፀሙ ድርጊቶች ወይም የሚሰጥ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የአስተዳደር በደል ተደርገው የሚቆጠሩ መሆኑን አካቷል።
2. በግል ድርጅቶች ውስጥ የአስተዳደር ወይም የአስተዳደር ነክ አገልግሎት የሚሰጥ አካል ተመርማሪ አካላት በሚለው ትርጓሜ ውስጥ እንዲካተት አድርጓል።
3. የግል ድርጅት ሲባል በንግድ ህጉ የተገለፁት የንግድ ማሕበር አይነቶች ሆነው የማምረት፣ የማከፋፈል፣ የአገልግሎት እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተግባሮችንና ከእነዚሁ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በንግድ መልክ የሚሰሩትን ሁሉ እንዲያጠቃልል አድርጓል።
4. አዋጁ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት እና በግል ድርጅቶች በሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችና ባለሥልጣኖች እና ኃላፊዎች ላይ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው ደንግጓል።
5. ለተቋሙ በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን የመቀበል እና ምርመራ የማካሄድ ስልጣን እና ኃላፊነት ሰጥቷል።
ተቋሙ በፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የመዳኘት ስልጣን በተሰጣቸው አካላት በመታየት ላይ ያሉ ወይም ታይተው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን የመቀበልም ሆነ የመመርመር ስልጣን የሌለው መሆኑ፣ በስልጣኑ ስር በሚወድቁት ጉዳዮችም ቢሆን የመጨረሻ ውሳኔው ምክረ ሃሳብ ከማቅረብ ያልዘለለ፣ አስተዳደራዊ፣ የፍታብሔር ወይም የወንጀል ተጠያቂነት የመፍጠር አይነተኛ ስልጣን የሌለው መሆኑ ሊኖረው የሚችለውን አበርክቶ በእጅጉ የሚገድብ ቢሆንም ዜጎች ደረሰብን የሚሉትን አስተዳደራዊ በደል የግል ተቋማትን ጨምሮ ብሶታቸውን ለማሰማት ተጨማሪ የመፍትሔ አማራጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ግን ጥርጥር የለውም።


#ህግ

Telegram: Contact @MrYenesewD

11/08/2024

በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የሚቋረጥባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
1. በመደበኛው የውል አተረጓጎም መሰረት የሚኖር የኪራይ ውል መቋረጥ፦ አከራይ እና ተከራይ የተስማሙበት የኪራይ ውል ዘመን ሲጠናቀቅ የኪራይ ውሉ ያለተጨማሪ ስርዓት ይቋረጣል። የኪራይ የውል ዘመን ከሁለት አመት ላነሰ ጊዜ ሊደረግ እንደማይችል በአዋጁ መደንገጉን ልብ ይበሉ።
2. አከራይ እና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት የሚኖር የኪራይ ውል መቋረጥ:- አከራይ እና ተከራይ የሚስማሙ ከሆነ የተለየ ስርዓት መከተል ሳይጠበቅባቸው ውሉን በፈለጉት ጊዜ ሊያቋርጡት ይችላሉ።
3. በተከራይ አነሳሽነት የሚደረግ የኪራይ ውል መቋረጥ:- ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል።
4. በአከራይ አነሳሽነት የሚደረግ የኪራይ ውል መቋረጥ:- አከራዩ ውሉን ለማቋረጥ ሁለት አማራጮች ይኖሩታል። የመጀመሪያው አማራጭ በማስጠንቀቂያ የኪራይ ውሉን ማቋረጥ ሲሆን ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ቤቱ በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ፣ ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት ለሶስተኛ ወገን በሚተላለፍበት ወቅት ነው። ሁለተኛው አማራጭ ያለማስጠንቀቂያ የኪራይ ውሉን ማቋረጥ ሲሆን ይህ አማራጭ ተፈፃሚ የሚሆነውም ተከራዩ ከሚከተሉት ጥፋቶች ውስጥ አንዱን መፈፀሙ ሲረጋገጥ ነው፤
ሀ/ የመክፈያ ጊዜውን ለመጀመሪያ ከሆነ ከአስራ አምስት ቀን ካሳለፈ፣
ለ/ ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣
ሐ/ ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣
መ/የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ፥፣
ሠ/ በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈጽም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈጸሚያ የሚጠቀምበት ከሆነ፣
ረ/ አስቦ ወይም በቸልተኛነት በቤቱ ላይ በመደበኛ አገልግሎት ከሚደርሰው እርጅና ያለፈ የቤቱን ደህንነት እና ዋጋ ግልፅ በሆነ ሁኔታ የሚቀንስ ወይም አደጋ ላይ የሚጥል ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ፣ ወይም
ሰ) በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት፤

#1320 #ጠበቃ
https://t.me/MrYenesewD/166

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Bole Medhanialem Church, Abrhams Building, 5th Floor
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 16:00
Tuesday 08:30 - 04:00
Wednesday 08:30 - 16:00
Thursday 08:30 - 16:00
Friday 08:30 - 16:00
Saturday 09:00 - 15:00