GebrHeir Project
Meklit Humanitarian Association was established on October 11, 2022 G.C. with the goal of "boosting the economic capacity of EOTC youths."
13/08/2025
LISTEN ON SPOTIFY
https://open.spotify.com/album/1mKAxGeVESTcXIqjj1vrxC?si=kFxQQS3NSd-E5tPaU4cVUw
29/07/2025
”ብዙ ሰዎች የተቸገሩ አረጋውያንና ህጻናት ይረዳሉ እሱ ልክአይደለም ማለቴ አይደለም ነገር ግን ወጣቱ ላይ ማተኮርያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ”
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ስም ሲጠራ ሁሉም ሰው ቀድሞ ከሚጠራቸውከመጀመሪያዎቹ ሰዎች መሐል አንዱ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡
ዘማሪው ከዚህ ቀደም 17 የዝማሬ አልበሞችን(11 የቸብቸቦና 5 የመዲና፣ ዘለሰኛና የበገና አልበሞችን) እንዲሁም በርካታ ነጠላዝማሬዎችን ለአድማጭ ተመልካቾቹ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከረጅም የዓመታት ቆይታ በኋላ ደሃ ራሱን ላንተ ይተዋል የሚል መጠሪ ያለውን 17ኛ የዝማሬ አልበሙን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ በዩቲዩብ ቻናሉ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ዕውን ለማድረግ ሰው ላይ በተለይም ወጣቱ ላይ መሰራት እንዳለበት የሚያምነው አንጋፋው ዘማሪ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ይህን የአዲሱን አልበም ሙሉ ገቢወጣቶች ሁለንተናቸው የተገነባ፤ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው የዳበረ እንዲሆን በማሰብ በመክሊትግብረሰናይ ማኅበር የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍእንደሚውልም አስታውቋል፡፡
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ እሁድ እለት ከሰይፉ ኢቢኤስጋር ባደረገው ቆይታ ላይ ብዙ ሰዎች የተቸገሩ አረጋውያንናህጻናት ይረዳሉ እሱ ልክ አይደለም ማለቴ አይደለም ነገር ግን ወጣቱ ላይ ማተኮር ያስፈልጋልብዬ አምናለሁ ብሏል፡፡ ወጣቱ እንዲሰራ ማድረግ ይገባል የሚለው አንጋፋው ዘማሪ ለዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣቶች የመሰረቱትን መክሊት ግበረሰናይን መደገፍ እንደመረጠና የሚታዩ ለውጦችንም በወጣቶች ህይወት ላይ ማስመዝገቡን ጠቅሷል፡፡
የመክሊት ግብረ ሰናይ ማኅበር የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም የማሳደግ አላማ ይዞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበራት አስተዳደር ደንብ ቁጥር 3/2015 አንቀፅ 3 መሠረት በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር ዋና ክፍል በመዝገብ ቁጥር 004/16 የካቲት 1 2016ዓ.ም የተመዘገበ ማህበር ሲሆን ሊቀ መዘምራንይልማ የማኅበሩ አነሳሽና የክብር አምባሳደር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ምዕመናን Yilma Hailu በሚለው የዩቲዩብ ቻናል በመግባትዝማሬዎቹን እንዲያዳምጡ፣ ለወዳጆቻቸው እንዲያጋሩና ከቪዲዮው ሥር በሚቀመጡ ማስፈንጠሪያዎች የማኅበሩንአገልግሎት እንዲደግፉ ተጠይቋል፡፡
በብር ለመለገስ፡ https://chapa.link/donation/view/DN-4d8x9Icph5dG
በዶላር ለመለገስ፡ https://chapa.link/donation/view/DN-UQn6RZuRBRRe
ለበለጠ መረጃ፡ https://meklitha.org/join
27/07/2025
🔴ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ አዲስ ዝማሬ በዚህ ሊንክ • 🔴አዲስ ዝማሬ ሞት ድል ሆነ like... ያገኛሉ።
የተዋህዶ_መዝሙራትን_በብዛት_ለማግኘት_ቻናሉን_ሰብስክራይብ_ያድርጉ።
መክሊት ግብረ ሰናይ ማህበርን ለመደገፍ
ለሀገር ውስጥ: https://chapa.link/don...
ከሀገር ውጪ: https://chapa.link/don...
የሂሳብ ቁጥሮች
CBE: 1000625419348
Ahadu Bank: 0005202010101
ለበለጠ መረጃ
Www.Meklitha.org
+251 114710994
22/07/2025
Coming soon
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
30/07/2025