AddisWalta 105.3 Radio
Fana Media105.3 fm radio station
Fana Media Corporate
ክረምታችን!
23/06/2024
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ የምርጫ ዞን ዛሬ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም ሲካሄድ የዋለው የድጋሚና ቀሪ ምርጫ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ተራዝሞ የነበረ ቢሆንም በሰላም ተጠናቋል።
አራት የፓለቲካ ፓርቲዋች ማለትም
ብልፅግና ፓርቲ፣ቦዴፓ / ቦሮ ሽናሻ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/፣አብን/ አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ/እንዲሁም ቤህነን/ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ/ በተሳተፉበት በአሶሳ የምርጫ ዞን መራጩ ህዝብ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ ተሰልፎ 12 ሰዓት ላይ ድምፅ መስጠት መጀመሩን ተመልክተናል።ነገር ግን በሰልፍ ላይ የነበሩ መራጮች በመገኘታቸው ምክንያት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ቀጥሎ እንደነበርና በሠላም ሊጠናቀቅ መቻሉን ለማወቅ ችለናል።
የምርጫ ውጤትም ከነገ ማለዳ 12 ሰአት ጀምሮ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚለጠፍ ተገልጿል።
23/06/2024
በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም የተካሄደው የድጋሚ ምርጫ በሰላም ተጠናቋል።
በ123 የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የድጋሚ ምርጫ ሰኔ 16/2016 ከጠዋቱ 11:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ተካሂዷል።
አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሶስት የግል ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ምርጫ ምሽት 12:00 ላይ ተጠናቋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጅግጅጋ ምርጫ ክልል አስተባባሪ ኃይለሥላሴ ወርቁ ምርጫው በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ያለ አንዳች ችግር መጠናቀቁን ለአዲስ ዋልታ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ከማለዳው ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ የተካሄደው የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የድጋሚ ምርጫ ውጤት ነገ ጠዋት ከ12:00 ጀምሮ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ይለጠፋልም ተብሏል።
የ6ኛው ዙር የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የድጋሚ ምርጫ ሐሙስ ዕለት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አማካኝነት ውጤቱ ይፋ ይደረጋል ነው የተባለው።
ወልደአማኑኤል ይርዳው ከጅግጅጋ፤ ሶማሌ
23/06/2024
በሌላ መረጃ
በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የድጋሚና ቀሪ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል። ይኸው ምርጫ በቤንሻጉል ክልል አሶሳ ከተማም እየተካሄደ ሲሆን በዚሁ የምርጫ ክልል አጠቃላይ 102 የምርጫ ጣቢያዋች ይገናኛሉ ። አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩም ለማወቅ ችለናል።
በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ አምስት አምስት የምርጫ አስፈፃሚዎች የሚገኙ ሲሆን በአጠቃላይም ከ500 በላይ አስፈፃሚዎች አሉ ተብሏል።
የከተማው ነዋሪም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ወጥቶ በመሰለፍ እየመረጠ ይገኛል። የምርጫ አስፈፃሚዎችም መረጃዋችን ለመራጮች በመስጠትና በማስተባበር ላይ መሆናቸውን ለመመልከት ችለናል።
መቅደስ የኔሁን ከቤንሻንጉል አሶሳ ከተማ
23/06/2024
በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የድጋሜ ምርጫው መካሄድ ጀምሯል።
በጅግጅጋ ከተማ የድጋሚ ምርጫው በዛሬው ዕለት ሰኔ 16/2016 ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች እየተካሄደ ይገኛል።
በ123 የምርጫ ጣቢያዎች የሚደረገው የሶማሌ ክልል ምርጫ 615 የምርጫ አስፈፃሚዎች ምርጫውን ያስፈፅማሉ።
መራጮች ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሚካሄድበት ወቅት እየተመዘገቡ በመምረጥ ሂደት ላይ መሆናቸውን አዲስ ዋልታ ሬዲዮ በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል።
ምርጫው ዛሬ ሙሉ ቀን እስከ ምሽት 12 ሰአት ሲደረግ ይውላል።
ወልደአማኑኤል ይርዳው፡ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ
22/06/2024
የምርጫ መረጃ
በሶማሌ ክልል የ6ኛው ዙር የድጋሚ ምርጫ በነገው እለት በ123 የምርጫ ጣቢያዎች ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል።
በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ6ኛው ዙር የድጋሚ ምርጫ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በ123 የምርጫ ጣቢያዎች ይካሄዳል።
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጅግጅጋ ከተማ ምርጫ አስተባባሪ ኃይለሥላሴ ወርቁ፤ ምርጫውን ያለ ምንም የፀጥታ ችግር ለማከናወን የተለያዩ የፀጥታ ዝግጅቶች ተደርጓል ብለዋል። በዚህም ሰኔ 15/2016 ዓ.ም ከማለዳው ጀምሮ በተካሄደው የቅድመ ምርጫ ዝግጅት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅቶች ተጠናቅቀዋል ነው ያሉት።
በምርጫ ሂደቱ 369 የምርጫ ጣቢያ አስፈፃሚዎች ከአዲስአበባ የመጡ ሲሆን፤ ሌሎች 246 የምርጫ አስፈፃሚዎች ደግሞ ከሶማሌ ምርጫውን ያስፈፅማሉ ሲሉም ለአዲስ ዋልታ ሬዲዮ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 615 የምርጫ ጣቢያ አስፈፃሚዎች በምርጫ ሂደቱ የሚሳተፋ ይሆናል።
በ6ኛው ዙር የድጋሚ ምርጫ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች በ123ቱም የምርጫ ጣቢያዎች ይወዳደራሉ። ሦስት የግል ተወዳዳሪዎችም በምርጫው ይሳተፋሉ።
ምርጫው ሰኔ 16/2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፤ መራጮች ምርጫው በሚካሄድበት ዕለት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች እየተመዘገቡ እንደሚመርጡም ተጠቁሟል።
ወልደአማኑኤል ይርዳው ከጅግጅጋ፤ ሶማሌ።
02/06/2024
ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።
የ 1 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ተወዳዳሪ ማን ይሆን? የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊ አሰልጣኝስ?
የእናንተን ምርጥ በ 8970 ድምፅ ይስጡ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን እንዲሁም በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይጠብቁን!
01/06/2024
ሊጠናቀቅ !
እንደ ስሙ አዲስ ነገርን ይዞ የመጣው ደሞ አዲስ ሊጠናቀቅ ነው፡፡
የፍፃሜ ውድድሩን ሊያካሂድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው በእናንተ በውድ ተመልካቾቻን የSMS ድምጽ የ ብር ሽልማቱን ለባለዕድሉ ለመስጠት ነገን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
በታኅሣሥ 28/2016 ዓ.ም በአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን መተላለፉን የጀመረው የ የድምፃዊያን ተሰጥዖ ውድድር ነገ እሁድ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም በደመቀ ሥነ ሥርዓት ይጠናቀቃል፡፡
በአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሁሉም የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ይጠብቁን!
ድምጽዎንም በSMs 8970 ላይ በመላክ ተሸላሚውን ይምረጡ!
ማን ያሸንፍ ይሁን ? አብረን እናየዋለን!
30/05/2024
የሁለት ውኃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ ክፍል 11 .3 |exclusive |abiy_ahmed |ዐቢይ_አሕመድ |አቃቂ |akaki |gebeta_leheger | ገበታ_ለሀገርየአዲስ ዋልታ 105.3 ኤፍ ኤምን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚድያን ለመከታተል 👇 ቴሌግራም ...
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Piaza
Addis Ababa