Prophet ebsa duba
ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና ማራናታ የእግዚአብሔር መንግስት አገልጋይ
ኢየሱስ ፈዋሽ አምለክ ነው!
በህመም እና በበሽታ ለምትሰቃዬ አሁን እፀልያለሁ
091 600 7087 whatsapp
ነብይ ኢብሳ
30/05/2026
is !
29/05/2026
...
ቀን ግንቦት 20-2018 ዓ/ም
ከአምስት አብያተ ክርስቲያናት ኅብረቶች የተሰጠ የጋራ አቋም መግለጫ
እኛ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መስራች አባላት መካከል 5 አብያተ ክርስቲያናት
1.የኢትዮጵያ አንድነት በክርስቶስ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲናት ህብረት
2. የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት
3 የኢትዮጵያ የፍቅር ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ህብረት
4. ርኆቦት አብያተ ክርስቲያናት ህብረት
5. ኢቬንጄልካል ካረዝማቲክ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፤
በማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 ከቁጥር 16-20 ባለው ክፍል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን በሰጠው መለኮታዊ ተልዕኮ መሰረት በዚህ ዘመን ያለን አብያተ ክርስቲያናት ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ በማድረስ መጽሃፍ ቅድሳዊ ተልዕኮአችንን መወጣትና ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲጨመሩ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንዲሆኑ መስራት ቀዳሚ ተግባራችን ነው ።
ከላይ በተጠቀሰው መሠረት አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረቶች በተለያዩ ወቅታዊ ሀገረዊ ጉዳዮች ላይ ከተወያየን በኋላ፣
የወንጌል አመኙን ጴንጤቆስጤያዊ፣ መንፈሳዊ ማህበራዊና ሀገራዊ አንድነትን ለማስጠበቅ የሚከተለውን ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1ኛ. እኛ አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ህብረቶች
ወንጌላዊያን አስተምህሮ የተመሠረቱባቸውን አምስቱ ብቻዎችን የእምነት (Doctorine) እንቀበላለን እነሱም መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ፣ ፀጋ ብቻ፣ ዕምነት ብቻ፣ ክርስቶስ ብቻና ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ።
2ኛ. እኛ አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ህብረቶች
ስመተ-ሐዋርያንና ስመተ- ነቢይ (ነቢይትን)
መጽሃፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ እንቀበለለን ።
በኤፌሶን 4:11-13 ላይ የተጠቀሱት አምስቱም የአገልግሎት ቢሮዎች ማለትም ሐዋርያት፥ ነቢያት፥ ወንጌላውያን፥ መጋቢዎች(እረኞች)ና አስተማሪዎች
ለቤተክርስቲያን እድገትና ለቅዱሳን ፍጹምነት የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው ክርስቶስ ዳግም እስኪ መጠ ድረስ ለቤተክርስቲያን
የተሰጡ ስጦታዎች እንደሆኑ እናምናለን።
1ቆሮ. 12፡28፣ እና ማቴ. 24፡14
3. እኛ አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ህብረቶች የወንጌል አንድነትንና ክርስቲያናዊ እሴቶችን መጠበቅ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን እንገነዘባለን። በመሆኑም ፤ ዘረኝነትንና ጥላቻን እንቃወማለን፣
4. እኛ አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ህብረቶች
መጽሃፍ ቅዱሳዊ የሆነውን ትምህርት የሚቃረኑ የኑፋቄና የስሕተት ትምህርቶች ፣ በጥንት ዘመን እንደ ነበሩ ዛሬም ይኖራሉ ወደ ፊትም እንደሚኖሩ እንገነዘባለን። በመሆኑም በማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ፤5 ላይ በተገለጸው መሰረት ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮና ልምምድ ያፈነገጡ ትምህርቶችንና ልምምዶችን የሚያከናውኑ ሐሰተኛ መጋቢዎችን ፤ነቢያትን፤ ሐሰተኛ ሐዋርያትንና አስተማሪዎችን ሐሰተኛ ሽማግሌዎችን ሐሰተኛ ወንጌላውያንን እንቃወመዋለን።
5. እኛ አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ህብረቶችና አባል ቤተ እምነቶች ከካውንስሉ ጋር በመንፈሳዊ ፣በኢኮኖሚያዊ ፣በማህበራዊና በሁለንተናዊ ጉደዮች ላይ ከዚህ በፊት አብረን እንደምንሰራ ሁሉ ወደ ፊትም በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ተባብረን እንሰራለን። የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞ አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን አዕማደ ዕምነትንም እንቀበላ
29/05/2026
እጃችሁ ላይ ባለው 🤳 በኢየሱስ ስም መልካም ዜና ስትሰሙ አያለሁ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Address
Addis Abeba
Addis Ababa