Mugher Cement Factory
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mugher Cement Factory, Business service, Global area , Garad BLDG, Addis Ababa.
07/05/2026
ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
=========================================
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተከፈተው ከሚያዝየ 25 እስከ 30 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተዘጋጀዉ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለአራተኛ ጊዜ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት አባላት በቦታው በመገኘት ተዟዙረው የጎበኙ ሲሆን በኤክስፖው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙትን የኮርፖሬሽኑ ተ/ተቋማት የተሳትፎ ሁኔታን ከማበረታታት በተጨማሪ ከሌሎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ የግል ተቋማት ጋር የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት ሁኔታ እና ልምድ ለመቅሰም የሚያስችሉ መደላደሎችን ፈጥሯል፡፡
06/01/2026
Merry Christmas and Happy New Year
01/09/2025
የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
—————————————————————————-
ፋብሪካው የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና 2018 ዓ.ም እቅድ በአባ ገዳዎች ፀሎት እና ምስጋና የተጀመረ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች፣ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች፣ ሠራተኞች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ግምገማ በማድረግ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ የነበሩት ኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢ/ር ሁንዴሳ ደሳለኝ ፕሮግራሙን የመሩት ሲሆን በተሰሩት ስራዎች ላይ እና ወደፊት ስለሚሰሩት ስራዎች የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ገዛኸኝ ደቻሳ ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ በእለቱ የፋብሪካ ጉብኝት፣ በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ጊቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ፣ በሰራተኞች መካከል የተደረገ የስፖርት ትዕይንት መቅረብ ችሏል፡፡
በመጨረሻም የኮሮፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር በሰራተኞች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት እንደ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሽን በ2017 ዓ.ም ለተሰሩት ስራዎች ዕውቅና በመስጠት ለሁሉም ተጠሪ ተቋማት ሥራ አስኪያጆች፣ የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች ላስመዘገቡት መልካም አፈጻጸም ዕዉቅናና ሽልማት በኮሮፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር እና በፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ተሰጥቷል።
ነሃሴ 26/2017 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Global Area , Garad BLDG
Addis Ababa
P.O.BOX5782/30749