Tagel Amsal

Tagel Amsal

Share

ሐሳብ /ፍልስፍና ፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ፊልም፣ትዝብት
ተከታተሉ ፤ ጠቃሚ ሐሳቦችን ሸር አድርጉ የበለጠ ወደ
FEMA ARTS you tube every one can promote especially art works

Photos from Tagel Amsal's post 14/02/2026

በቃ! አንወሻሽ!

ራሱ ተናግሮ ራሱን አድናቂ
ድፍን ልሙጥ ድንጋይ
ከበዛበት ቀየ የሰው ልቅላቂ
ገለል በይ ፀጥ በይ
በሐሳብ በገቢር ሺህ ማይል ራቂ።

ከፊት መንገድ ዘግቶ መሔጃ እያሳጣ
''ሔድሁ በረርሁ!'' ለሚልሽ ቁልቁል እየመጣ
በሌላ ጎን ታጥፎ ከመራመድ በቀር
አንዳች ትርፍ የለውም ወደላይ ሚያስወጣ።

ማሳው ባረር ታርሶ አራሹ እየሞተ
ብሎ ለሚነዛ አዝመራው አሸተ
''ነፍስ ይማር!'' ነው ምሱ ቆይቷል ከሞተ፤ ገምቶ ከበከተ።

አስተውይ የኔ ዓለም ልብ በይ ሀገሬ
ደጋግሞ አያታልሽ 'በላ ባይ በወሬ

እፍኝ ጥሬ ጠፍቶ ሁሌ ፆም ሁዳዴ
በኾነበት እውነት
ሰው እንዴት ያኸልማል ሲዘናፈል ስንዴ?

ውሸት ሲደጋገም ተረት ሲደራረት
የለም ምንም ምትሃት
ኑሮን የሚያሻሽል፣
ሠላም የሚያሰፍን፣
ችግር የሚፈታ . . . ጥሪት ሚሆንበት
ጤና ተስፋ ሚሰጥ ለዜጎቹ ሕይወት!

22/01/2026

ከማይረባ ባል ላጤነት ይደላል!?

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa
1212