Fact News

Fact News

Share

Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld

10/01/2022

ለሰዎች ገደብን አብጅላቸው
ያላመንክበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነትህን እንደሚሸረሽረው አትርሳ ፡፡

https://www.facebook.com/Newsfactnews/

Fact News Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld

Photos from Fact News's post 02/01/2022

አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈጸመበት ወቅት ለህዝቡ እውነተኛ አባት ሆነው ለቆዩት ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ተሽከርካሪ ተበረከተ

ታህሳስ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በተወረረበት ወቅት ለህዝቡ እውነተኛ አባት ሆነው ለቆዩት ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ተሽከርካሪ ተበረከተላቸው።

የተሽከርካሪ ስጦታውን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ እና የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አስረክበዋቸዋል።

የብጹዕነታቸውን ተሽከርካሪ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እንደዘረፋቸው ይታወቃል።

ዛሬ በስጦታ የተረከቡት ተሽከርካርም ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል።

አቡነ ኤርሚያስም መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

17/12/2021

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ ነው
***********************

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ ነው፡፡

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡ በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

ባለፈው ጊዜ ውጫሌ ከተማን ነጸ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣የጊራና፣የመርሳ፣የኪሌ፣ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሀብሩ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል፡፡

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል፡፡ የአካባቢው ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል፡፡ ጠላትም የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡ የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው፡፡
https://www.facebook.com/Newsfactnews/

15/12/2021

በደብረታቦር ከተማ የክላሽንኮቭ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
*****************

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የክላሽንኮቨ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያለው ዘለቀ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግለሰቧ ትናንት ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር የዋለችው ከህብረተሰቡ ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ በመኖሪያ ቤቷ ባደረገው ፍተሻ የክላሽንኮቭ ጥይት ተከማችቶ በማግኘቱ ነው።

ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝም ክትትል እየተደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ አካባቢውን ከህገ ወጥ ተግባራትና ሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa